>

የተዳፈነ እሳት አትቆስቁሱ!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ፈጽሞ ልክም አይደለም!  አምርሬም እቃወመዋለሁ! አወግዘውማለሁ!!!
ዘመድኩን በቀለ 

–  የተዳፈነ እሳት አትቆስቁሱ!!!

•••
ዐማራ ማለት ሃይማኖተኛ ህዝብ ነው። አማኝ ህዝብም ነው። ለራበው ሙክት፣ ለጠገበ ጥይት አጉራሽም ህዝብ ነው። መደቡን ለቅቆ የሚያስተኛህ፣ እግርህን አጥቦ ስሞ የሚቀበልህ፣ ስንቅ ቋጥሮ የሚሸኝህ መሶበ ለምለም. ከኢትዮጵያ በቀር ይመካበት ትምክህት፣ ይሸሽ፣ ይደበቅበት
ጥግ ተለዋጭ ሃገርም የሌለው ህዝብ ነው። በአረብኛ የማይምል። በጣልያንኛም የማይፎክር በሃገሩ መሬት በሃገሩ ቋንቋ ዘራፍ ብሎ በወገኑ ፊት የሚፎክር ኢትዮጵያዊ ነው። አትንኩት ተናግሬያለሁ።
•••
ምን ዓይነት አረመኔነት ነው? ምን አይነት ጭካኔ ነው? ምን ዓይነት አረመኔነት ነው በዚህ ሰዓት፣ በዚህ ወቅት ሃገር የተወረ ይመስል፣ ምንም በሌለበት በሰላማዊ ገበሬ ላይ ብርጌድ ጦር ማዝመት? ምንድነው ጉዱ። እንደ ዜጋ ለሃገሬ፣ እንደ አማኝ ለሃይማኖቴ በሚለው አቋሜ መሠረት አሁንም
ለምስኪኑሆኖም ግን ለጀግናው፣ ለአሸናፊው፣ ለዐማራው ህዝብ እኔ ዘመዴ የሐረርጌው ቆቱው ድምጼን አሰማለታለሁ።
•••
ከዐማራ ሆዳም አክቲቪስቶች በበለጠ እኔ ዘመዴ አሳምሬ እጮህለታለሁ። በልተው ከጉያው ወጥተው በጎጥ ተሸናሽነው ወገናቸውን ከሚያስፈጁት የራበው የቀን ጅብ ከሆኑ ሆዳም የዐማራ ተሟጋቾች እኔ እበልጣለሁ። ሴትና ብር ከሚያብረከርካቸው እነሁሉ ብርቁ ሆዳም ዐማሮች እኔ ቆቱው ዘመዴ ለዐማራው እጮህለታለሁ። ያልታደለ፣ አመድ አፋሽ ለሆነው ለዚያ ዐማራ እኔ እጮህለታለሁ። ብከዳው ቀኜ
ይክዳኝ። ባላስበው ምላሴ ከትናጋዬ ይጣበቅ። የቅዱሳን ምድር፣ የሃይማኖቴ ምንጭ ለሆነው ለዐማራው ህዝብ ያልጮህኩ ለማንአባቱ ልጮህ ትፈልጋለህ? ስለ ዐማራ ስናገር ቅሽሽ አይለኝም። ዐማራ የድህነቴ ምክንያት ነው። ከክርስቶስ ጋር ያገናኘኝ ሐዋርያዬ ነው። አከተመ።
•••
* ዋልድባን የደፈረው የመለስ መንግሥት ተልቶ ሲሞት ሳምንት አልቆየም።
 * በጎንደርና በባህርዳር ወጣቶችን በጥይት
ያስፈጀው ኃይለማርያም ደሳለኝ ሲወገድ ዓመት አልቆየም።
* አሁንም የዐቢይ መንግሥት መውደቂያው፣ መፍረሻው ደርሷል መሰለኝ የማይነካውን መንካት ጀምሯል።
የማይቀረው የእርስ በእርስ ጦርነት ይነሳል፣ የኢትዮጵያ ምድር ደም በደም ትሆናለች እንጂ የህወሓቱ ፈረስ የዐብይ አህመድ አካሄድ ለማንም አይበጅም።
•••
አሁን በእኔ ግምገማ በአሁኑ ወቅት ለክርስቲያን ኦርቶዶክሱ የዐማራ ህዝብ በዐብይ አህመድ መንግሥት ፭ ዓይነት የሞት ምርጫዎች ከፊቱ ቀርበውለታል።
፩ኛ፥ በኮሮና ጉንፋን በሳንባ ቆልፍ መሞት
፪ኛ፥ በወራሪው የሱዳን የወሀቢይ እስላም ጦር መታረድ
፫ኟ፥ በቀሽሟ ካንሰር በፀረ ተዋሕዶዋ ህወሓት ጦር መሞት
፬ኛ፥ በኦነጎቹና በፕሮቴስታንቶቹ ዐቢይ አህመድ፣ በብርሃኑ ጁላና በለማ መገርሳ የአክራሪ የወሃቢያ እስላም ጦር መረሸንና
፭ኛ፥ ከዚህ ሁላ ከሚፈጠር ትርምስ በኋላ በረሃብ መሞት።
ሞት ሞት ነው። የሞት ምርጫ የለውም። እናም መሞቱ ካልቀረ አይኑ እያየ እየታረደ ይሞታል የሚል እምነት የለኝምና ዐቢይ ሆይ አስብበት። ዐማራው ዳንኤል ክብረት ሆይ ወንድም ጓደኛዬ ዐብይን ምከረው ንገረው።
•••
በእውነት ፌር አይደለም። ትክክልም አይደለም። ሃይማኖት አለኝ። እኔ የኢየሱስ ነኝ ከሚል ከአንድ የጴንጤ አማኝ አይጠበቅም። በዚህ ወቅት በዓለም ላይ ያሉ ጦረኞች የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገው፣ ኢራንና አሜሪካ እንረዳዳ በሚሉበት በዚህ ሰዓት፣ ፍልስጤምና እስራኤል፣ ሃማስና
ሂዝቦላም ዝም ጭጭ ባሉበት በዚህ ሰዓት፣ በዚህ ወቅት ዓለም በሙሉ ከቤቱ ዘግቶ ከኮሮና መቅሰፍት ለማምለጥ ፈጣሪው እየተማጸነ በቤቱ በተቀመ
ጠበት ሰዓት፣ ኃያላኑ ሁላ ወደ ፈጣሪ በሚጮሁበት ወቅት ዐማራ ላይ፣ ኦርቶዶክሱ አማኙ ህዝብ ላይ ጴንጤ መሪ ስለሆንክ ብቻ እስላም ወታደር መርጠህ ኦርቶዶክሱን ዐማራ ለመፍጀት መራወጥ ትክክል
አይደለም። አምርሬ እቃወመዋለሁ፣ አወግዘዋለሁ። ቀኑ ሲያልፍ ያኔ ወንድነታችሁን ተፈታተሹ። ተቃውሞም የለኝም።
•••
አንተ ኦሮሞው ዐቢይ አህመድ፣ የደሴው ተወላጅ ባህርዳር ያደገው ዐማራው ጓደኛዬ የዲያቆን ዳንኤል ክብረቱ ጓደኛና አለቃ፣ ኢትዮጵያን አፍቃሪው፣ ስለኢትዮጵያ ሲያወራ እንባ በአይኑ ቅርር ይላል ተብሎ በዳኒ የተመሰከረልህ ሶዬ፣
( ይህቺ የዳኒ ምስክርነት ናት። ዳኒን በዚህ ነው የሌለ ፋውል ያሰሩት። ዳኒ በነፃ ሲያገለግል ሚዛናዊ ነበር። ደሞዝ መብላት ሲጀምር ማኖ ነካ። ፈጣሪ ይሁንህ ዳኒዬ። ) የሚስትህን የዝናሽን ዘመዶች በዚህ ወቅት ሊትረሽን መንቀሳቀስህ ፌር አይደለም። በዘመነ ኮሮና ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ቤትህ ግባ፣ በርህንም ዝጋ የሚል አዋጅ አሳወጀህ ሲያበቃ፣ ሁሉም በሩን
ሲዘጋ፣ ቤቱም ሲቀመጥለት ቀን ጠብቆ ዐማራን ከላይ ከታች ለመውጋት መነሳት ከምር ነውር ነው።
•••
ኦሮሞው ለማ መገርሳ የወላጆቹን ሰፈር ሀገሩ ወለጋን ከጦርነት ባሳረፈበት በዚህ ሰዓት፣ የስልክም የኢንተርኔትም ኔትወርክ ባስከፈተበት በዚህ ሰዓት፣ ጤናችሁን ጠብቁ፣ በኮረናም እንዳታልቁ ብሎ ለወገኖቹ ለኦሮሞ ሸኔ ወታደሮች ተቆረቁሮ ምህረት በሰጠበት በዚህ ሰዓት ኦሮሞ ኦሮሞን መግደል የለበትም በሚባልበት በዚህ ሰዓት፣ እሱ ጴንጤ
ስለሆነ ብቻ የጎንደር ኦርቶዶክስ ዐማራ ላይ ጦር ማዝመት ነውርም ኃጢአትም፣ ወንጀልም ነው።
•••
ፀረ ዐማራ ኦሮሞው ጄነራል ብርሃኑ ጁላ፣ የአለቃውን
የጌታቸው አሰፋ ትእዛዝ ተቀብሎና አክብሮ ሲያበቃ ወገኑን የኦሮሞ ነፃ አውጪ ኦነግ ሸኔን ይቅር ባለበት በዚህ ሰዓት፣ ከእስራቱም ፈትቶ፣ በውጊያእንዳይሞት በትም ለኦነግ ምህረት አድርጎ፣ ከመከላከያ ግምጃ ቤት አዳዲስ የጦር መሣሪያም ከነሙሉ ትጥቁ፣ ከነዝናሩ ሰጥቶ፣ በዐልመዳ ጨርቃጨርቅ የሚያመርተውን የወታደር ዩኒፎርም ከነ ጫማው ከነመቀየሪያው ሰጥቶ ሽክ አድርጎ ሲያበቃ ለጎንደር
ዐማራ ገዳይ ሠራዊቱን አላህ ወአክበር እያለ በደም ፍላት እልሁን ለመወጣት ኦርቶዶክሳዊውን ክርስቲያን ዐማራ ለማረድ፣ ለመጨፈር የተቁነጠነጠ ጦር በዚህ ሰዓት መላክ ነውርም ኃጢአትም፣ ወንጀልም ነው። እቃወመዋለሁ።
•••
ኦሮሞው ሽመልስ አብዲሳም ለወገኑ ለኦሮሞው የኦነግ ሸኔ ሠራዊት በኮሮና እንዳያልቅበት የአፍ መሸፈኛ ማስክ፣ የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘርና ሳሙና በካርቶን በካርቶን አሽጎ ወለጋ ድረስ ልኮለት ሲያበቃ በቅርቡ ያስመረቀውን የኦሮሞ ሠራዊት ለወረራ ጎንደር መላክ ነውርም ኃጢአትም፣
ወንጀልም ነው። [ “ተደመሰሰ የተባለው የኦነግ ሸኔ ጦር “ግን እንዴት አባቱ ነው ያማረበት በእመቤቴ ]
•••
ለዐማራ አስገዳዩ በድኑና ሲፈጥረው በባህሪው አሽከር፣ አድርባይ አድርጎ የፈጠረው ቀድሞ የህወሓት አሁን የኦህዴድ አሽከር የሆነው ብአዴን ነው። ይኸው በዚህ ወቅት፣ በዚህ ጭንቅ ሰዓት፣ አራሽ ገበሬውን ፋኖ የዐማራ ጠባቂ የሆነውን
ራሱ ብአዴንን ነፃ ያወጣውን ለወገኑ ተቆርቋሪ፣ ደንበር ጠባቂውን በኦነግ ጦር ሊያስፈጀው የሞት ኩፖን ቆርጦ እየተንቀሳቀሰ ነው።
•••
አሁን አሳምነው ጽጌ የለም። አስቻለው ደሴ የለም።
አይሆንም ብለው የሚከራከሩት እነ ዶክተር አምባቸው የሉም። እናም ያሉት አሽከሮቹ፣ ገዳይ ሆነው የተሾሙት ስለሆኑ ከግራ በኩል ሱዳን፣ ከአናት እስከ ቀኝ ወገቡ ታፋው ድረስ ህወሓት፣ ከእግሩ እስከ ጭንቅላቱ ድረስ ደግሞ የብርሃኑ ጁላ፣ የዐቢይ አህመድና የለማ መገርሳ ጦር ዐማራውን ከቦታል።[ ወያኔና ዐብይ ተጣልተዋል የሚለውን
ቀልድህን ታቆምልኛለህ ] ጉምዝም በቀስት መግደሉን ጀምሯል።
•••
ዐማራው በኮሮና እንዲያልቅም የተፈለገ ይመስላል።
ዐማራው ግን ከምር ደግሞ ሳስበው የሚገርም ህዝብም ነው። ጠንካራ፣ አቻዮ ህዝብ ነው። በጤና ጣቢያ ዕጦት፣ በኪኒን በመርፌ፣ በረሃብ፣ በመሰረተ ልማት፣ በመልካም አስተዳደር፣ በዕዳ፣ በበሽታ እንዲያልቅ አውሬው ከድሮ ጀምሮ በብዙ ቢደክምም ዐማራ ግን ጠንካራ ነው። ጸሎተኛም ነው።
ሃይማኖተኛም ነው። ጀግናም ነው። ሁሉንም በጸጋ ተቀብሎ እስከዛሬ ድረስ በጽናት የቆመህዝብም ነው።
•••
አምናለሁ፣ ብዙ ደም ይፈስ፣ ግርግርም ይፈጠር ይሆናል እንጂ፣ እንኳን የዐቢይ አህመድ እስላማዊ ጦር የብርሃኑ ጁላ፣ የለማ መገርሳ በኦሮሞ ስም የሚነግደው የኦነግ ሠራዊት፣ የባንዳው ብአዴን የወሀቢይ እስላሙ ፀረ ኦርቶዶክሱ ደመቀ መኮንን ሤራ፣ የተመስገን ጥሩነህ ጉራና ፉከራ፣ ፋሽስት
ኢጣልያም አላሸነፈውም።
የደርጉ መላኩ ተፈራም ረሽኖ አልጨረሰውም። የፓስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሞት ዐዋጅ
ስናይፐሩም ረፍርፎ አልጨረሰውም። ክው ብሎ ደንግጦ የሞተው የመርዘኛው መለስ ዜናዊ ኪንና መርፌ ስናይፐርም አልቻለውም። መለስ ገድሎ፣ ገድሎ ድክም ሲለው ዐማራው ሳያልቅ በቁሙ አልቆ ነው የሞተው። ወደ ሲኦልም ነው የተሸኘው። ያውም ሟምቶ። የዐቢይ አህመድም መንግሥት ዕጣ ፈንታው ይሄው ነው። እመነኝ ዐማራን ነክተህ
መንግሥትህ አይፀናም።
•••
በለላው በኩል ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድም ደግሞ ግድ ነው። “ የወረርሽኝ በሽታ፣ የእርስ በርስ ጦርነትና ጽኑ ረሃብ ” ለኢትዮጵያውያን በሙሉነት ለመግረፊያነት፣ ለመቅጫነት እንደተላከም አስቀድሞ የተነገረ ሃቅ ነው። ትንቢት ደግሞ መፈጸሙ ግድ ነው። መከራውም እንደ ልባችን መመለስ ሊያጥር ሊረዝም ይችላል እንጂ አይቀርም። ያለ ደም ስርየት የለም እንዲል መጥሐፉ። ራያና ጎንደር ላይ ደም ይፈሳል።
ኢትዮጵያም ነፃ ትወጣለች። [ ዐቢይን ለማገዝ በሁለት ኃያላን ሃገሮችና በ7 የዐረብ ሃገሮች የሚመራ ጦር የሚመጣው አሁን ይሆን እንዴ? ትንቢቱ ፈጠነብኝሳ?
•••
አሁን ዘንዶው የሚዋጋው ዐማራን ከመሰለህ ተሳስተሃል። ዘንዶው የሚዋጋው ሰሜን ጎንደርን ከመሰለህም ተሳስተሃል። ወሎም፣ ጎጃምም፣ ሸዋም ምልክቱን አይተሃል። የቀን ጉዳይ እንጂ አይቀር ልህም አባቴ። ዘንዶው የሚዋጋው መስቀሉንና
የመስቀሉን አማኝ ህዝብ ነው። ዐማራ ከሚለው ስምም ጋር ነው ጠቡ። እስከ አሁን አውሬው የገደላ ቸውና ለመሥዋዕት ያቀረባቸው በሙሉ ተመልከት በሙሉ ኦርቶዶክሳውያን ናቸው።
•••
ኢንጅነር ስመኘው በቀለ = ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ×
ዶ/ር አምባቸው መኮንን = ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ×
አቶ እዘዝ ዋሴ = ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ×
አቶ ምግባሩ ከበደ = ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ×
ጀነራል አሳምነው ጽጌ = ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ×
ጀኔራል ሰዓረ መኮንን = ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ×
ጄነራል ገዛኤ አበራ = ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ×
ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ = ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ×
አስቻለው ደሴ = ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ×
•••
አሁንም ዘመቻው በኦርቶዶክሳውያኑ ላይ ነው። ነጣጥለው ያወድሙሃል። ወሎ፣ ጎጃም፣ ሸዋ ጎንደር ሲረሸን ተራውን ጠብቀው ይመጡልሃል።
•••
የመስቀል ዕለት ታራጅ ዶሮ ይእንቁጣጣሽ ዕለት
በምትታረደው ዶሮ ትስቃለች ይላል አጎቴ ሌኒን ሲተርት።
ልዩነቱ እኮ በመስቀልና በእንቁጣጣሽ መካከል የ15 ቀን ብቻ ነው። ለእሷም አይቀርም። ለአንተም አይቀርልህም። ምረጥ በየትኛው መሞት ይሻልሃል?
፩ኛ፥ በኮሮና ጉንፋን በሳንባ ቆልፍ መሞት
፪ኛ፥ በወራሪው የሱዳን የወሀቢይ እስላም ጦር መታረድ
፫ኟ፥ በቀሽሟ ካንሰር በፀረ ተዋሕዶዋ ህወሓት ጦር መሞት
፬ኛ፥ በኦነጎቹና በፕሮቴስታንቶቹ ዐቢይ አህመድ፣ በብርሃኑ
ጁላና በለማ መገርሳ የአክራሪ የወሃቢያ እስላም ጦር
መረሸንና
፭ኛ፥ ከዚህ ሁላ ከሚፈጠር ትርምስ በኋላ በረሃብ መሞት።
•••
ማስታወሻ | ~ እኔ ዘመዴ ዐማራ አይደለሁም። ልክ ትናንት ለኦሮሞው፣ ለትግሬው፣ ለጌዲኦው፣ ለጋምቤላው፣ ለወላይታው፣ ለዶርዜው፣ ለሱማሌ ለአፋሩ፣ ለጉራጌው፣ ለፍልስጤም ህጻናት፣ ለግብጽ ክርስቲያኖች፣ ለየመን ረሃብተኞች፣ ለደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፣ ለሊቢያ ታራጆች እንደጮህኩት ነው የምጮኸው።
በስጋ የሚዋለደኝ የእናቴ ልጅ የለም። ከኢትዮጵያውያኑ ጋር ሃገር ነው አንድ የሚያደርገኝ፣ ሌሎቹን ደግሞ እምነትና ሰብአዊነት።
•••
እኔ ዘር የለኝም። ለሚጨቆን ዘር ግን እሪ ብዬ እጮሃለሁ። ዐማሮቹ ታማኝ በየነ፣ ሄኖክ የሺጥላ፣ ሙሉቀን መለሰ፣ ታደለ ጥበቡ፣ አያሌው መንበር፣ ጌታቸው ሽፈራው፣ ሚኪ ዐማራ በላይ ግን ለዐማራው መጮህን ማንም አይከለክለኝም።
መብቴ ነው።
• በዘመነ ኮሮና ዐማራ ላይ የተከፈተውን ጦርነት አወግዛለሁ። እቃወመዋለሁም።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
መጋቢት 24/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic