>
5:13 pm - Tuesday April 19, 2259

ከባድ መሳሪያ አስተኳሹ ድምጻዊ!!! (ፍጹም ንጉሴ)

ከባድ መሳሪያ አስተኳሹ ድምጻዊ!!!

ፍጹም ንጉሴ
 
* …. ” አጥንቴም ይከስከስ ደሜም ይፍሰስላት…”ን ሲዘፍን ለሰማው እንኳን አየር መቃወምያ በወቅቱ የለም እንጂ ሚሳኤልም ያስተኩሳል!!!
“……በ1970 ዓ/ም በድሬዳዋ ስታድየም ላይ ጋሽ ጥላሁን እየዘፈነ ነበር ። በዘፈኑ ስሜቴን መቆጣጠር ተስኖኝ የጠላትን የአየር ጥቃት ለመከላከል የተሰጠኘን M 37 አየር መቃወሚያ አውቶማቲክ መሳሪያ ወደሰማይ አውቶማቲክ ተኮስኩ አካባቢው በድንጋጤ ተደበላለቀና የሙዚቃው ትርኢቱ እንዲቆም ተደረገ ። ሁኔታው ሲጣራ ድርጊቱን የፈጸምኩት እኔ መሆኔ ተረጋግጦ በቁጥጥር ስር ዋልኩ ።ድርጊቱን በስሜታዊ ስህተት የፈጸምኩ መሆኑን ጋሽ ጥላሁን ሲሰማ ተኳሹን አሳዩኘ ብሎ በቁም እስር ካለሁበት ቦታ አስጠርቶ ከተዋወቀኘ በኃላ የእጅ ሰዓቱን ሸለመኝ በሁኔታው ሁለታችንም ተላቀስን። ይህ ልጅ በወራሪው የዚያድ ባሬ ጦር ላይ ድልን ይጎናጸፋል እንዳታስሩት ብሎ አለቆቼን በማግባባት ከቁም እስር እንድፈታ አድርጓል።
ያለውም አልቀረም ግዙፉን ወራሪ ጠላት መክቶ ወደማጥቃት ተሸጋግረን የዚያድ ባሬን ጦር አከርካሪ ሰብረን በመጠራረግ ሉአላዊነታችንን በድል አጠናቀን በካራማራ ተራራ ላይ የኢትዮጲያን ሰንደቅ አላማን እንድናውለበልብ መደረጉ ህያው ምስክር ነው።
ጋሽ ጥላሁን በ1970 ዓ/ም ድሬ ዳዋ እስታድየም ዉስጥ ከብዙነሽ በቀለ እና ከሌሎች ድምጳዊያን ጋር ተገኘቶ በቁምጣ በባዶ እግሩ ጋሻ እና ጎራዴ ይዞ ግንባሩ ላይ የኢትዮጲያ ሰንደቅ አላማ አስሮ አጥንቴም ይከስከስ ደሜም ይፍሰስላት እያለ መድረኩ ላይ እንደአምበሳ ሲንጎማለል የተመለከተ ኢትዮጲያዊ እንኳን አየር መቃወሚያ አልነበረንም እንጂ ሚሳኤልም ያስተኩስ ነበረ”
በሱማሌ ጦርነት የተሳተፈ ሀጎስ ገ/ሕይወት የተባለ ወታደር ስለጥላሁን ከተናገረው።
*******
(ከጥላሁን ገሰሰ የህይወት ታሪክ መጽሀፋ ገጽ 202)
Filed in: Amharic