በኢትዮጵያ ተጨማሪ 9 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!!!
የጤና ሚኒስቴር
* ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 65 ከፍ ብሏል!!!
ሚያዚያ 02/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 442 ሰዎች መካከል ዘጠኙ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 65 ከፍ ብሏል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፤ ዛሬ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሁሉም ግለሰቦች የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።
ከግለሰቦቹ መካከል ሰባቱ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ፤ አንድ ኤርትራዊ ቀሪዋ ደግሞ የህንድ ዜግነት ያላት ናት።
አራቱ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ መሆኑንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
ሁለቱ የቱርክና ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት:-
የእንግሊዝ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፤ ሁሉም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን አውስተዋል።
የ20 ዓመቷ ህንዳዊት የአሜሪካ እንዲሁም ኤርትራዊው ደግሞ የዱባይ ጉዞ ታሪክ ያላት ናቸው።
በጽኑ ህሙማን ክፍል ከሚገኙት ሁለት ግለሰቦች መካከል አንዱ የጤና መሻሻል በማሳየቱ ከክፍሉ መውጣቱንም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።
እስካሁን ባለው ሂደትም በኢትዮጵያ ለሶስት ሺህ 232 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ጠቁመው፤ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 57ቱ የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።
አራት ግለሰቦች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ በበሽታው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።