በኢትዮጵያ በቢጫ ወባ በሽታ 86 ሰዎች ተያዙ 4 ሰዎች ሞቱ!!!
50 ሰዎች ከኮሮና በሽታ አገግመዋል!!!
የጤና ሚኒስቴር
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን አነሞር እና ኢነር ወረዳ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ የበሽታው ምልክት መታየቱን ሪፓርት መደረጉን ገልፀዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዪት ከክልሉ ጤና ቢሮ እና ከዞኑ ጤና መምሪ ጋር በመሆን የምላሽ አሰጣጡን ሲደግፍ እንደነበረም ተናግረዋል።
የካታት 24 እንደጀመረ ያስታወቁ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ በበሽታው የተያዘ ሰው ሪፓርት የተደረገው መጋቢት 20 እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ አጠቃላይ 50 ሰዎች ከኮሮና በሽታ አገግመዋል!!!
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ943 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርማራ ተደርጓል፤ በአንድ ሰው ላይም ቫይረሱ መገኘቱ ተረጋግጧል፡፡ የጤና ሚኒስቴር በማኅበራዊ ገጹ እንዳስታወቀው ቫይረሱ የተገኘባቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊ እንግሊዛዊ የ45 ዓመት ጎልማሳ ናቸው፤ ከእንግሊዝ ተመልሰው በለይቶ ማቆያ የነበሩ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት በኢትዮጵያ ተጨማሪ 9 ሰዎች ከኮሮና በሽታ ማገገማቸውም ተነግሯል፤ ስምንቱ ከአዲስ አበባና አንዱ ከባሕር ዳር መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡ በዚህም በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 50 ደርሷል፡፡ 69 ሰዎች ደግሞ በሕክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ፡፡
የጤና ሚኒስቴር ኅብረተሰቡ አሁንም ጥንቃቄውን እንዲያጠናክር አሳስቧል፡፡ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ እንጅን አዘውትሮ በውኃና ሳሙና መታጠብ፣ የፊት መሸፈኛ መጠቀም ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስቧል፡፡
አዲስ ሚድያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) ሚያዝያ 19/2012