>

“መንንግስት ሹመት ሲሰጥ ‘የትምህርት ዝግጅት’ ብሎ ተሿሚውን መግለጽ ማለት ተሿሚው አልተማረም ማለት ነው” (ፕሮፌሰር  መንደርያለዉ ዘዉዴ)

“መንንግስት ሹመት ሲሰጥ ‘የትምህርት ዝግጅት’ ብሎ ተሿሚውን መግለጽ ማለት ተሿሚው አልተማረም ማለት ነው”

 

 

ፕሮፌሰር  መንደርያለዉ ዘዉዴ

 

በቅርብ ጊዜ ሰዎች ለምኒስትርነት እና ወዘተ…. ሲሾሙ “የትምህርት ደረጃቸው” ከማለት ይልቅ፣ “የትምህርት ዝግጅታቸው” ተብሎ ይነገራል።የትምህርት ዝግጅት ማለት ያልተማረ ማለት ነው።

ሰው ስለትምህርት በሁለት መንገድ ይዘጋጃል።አንድም ለመማር አንድም ጨርሶውኑ ላለመማር። የመጀመሪያው፣ እርሳስ እስክሪፕቶ መጽሀፍ ደብተር ዩኒፎርም ወዘተ አሰናድቶ ለትምህርት መዘጋጀት ነው። ሁለተኛው ፡ የትምህርት ምልክቶችን ለመግዛት የሚደረግ ዝግጅት ነው። ያም ማለት፣ የትኛውን ምልክት ልግዛ ፣ ከማልግዛ፣ የትኛው ረከስ ይላል፣ የትኛውን የትምህርት ደላላ ላነጋግር፣ ምልክቱን ከገዛሁ በሁዋላ እንዴት ከፔሮል አስርጌ ላስገባ፣ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚደረግ የወንጀል ዝግጅት ነው።

የመጀመርያው አይነት ዥግጅት ይደልዎ ይደልዎ የሚሰኝ ቢሆንም፣ ለመማር ያለንን ቁርጠኝነት ከመግለጽ አያልፍም.።  ዝግጅት ተጠናቆ ወደትምህርት ከተገባ በሁዋላ
ባጠናቀቅነው የትምህርት ወርድና ርዝመት ደረጃ ይሰጠናል።ሺ ሲዘጋጅ ከኖረ አንድ ቀን የተማረ ይበልጣል።እናም መንንግስት ሹመት ሲሰጥ ‘የትምህርት ዝግጅት’ ብሎ ተሹዋሚውን መግለጽ ማለት ተሹዋሚው አልተማረም ማለት ነውና ፣ ይህቺን ራሰ -ተፋልሶ( self contradiction) ሊያርም ይገባዋል።

Filed in: Amharic