>

አናታችን ላይ የሚያናጥረው የቻይና እዳና የሀገሪቱ የነገ እጣ ፈንታ!!! (ያሬድ ሀይል መስቀል)

 

አናታችን ላይ የሚያናጥረው የቻይና እዳና የሀገሪቱ የነገ እጣ ፈንታ!!!

ያሬድ ሀይል መስቀል
አበዳሪዎቻችን እዳችንን እንዲቀንሱልን ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይገባናል። በዚህ ረገድ ትልቋ አበዳሪያችን ቻይና ናት። በሽታውም የመጣው ከዚያ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለምንም ገደብ ሲበር ነበር። ስለዚህ ቻይና አንዳንድ የህክምና ቁሳቁሶችን ከመደገፍ ባለፈ እዳችንን እንድትሰርዝልን በአግባቡ ልንደራደር ይገባናል።
አፍሪካ 168 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ የቻይና እዳ አለባት። በነገራችን ላይ ቻይኖቹ ይሉኝታ የላቸውም። አሁን ዛምቢያ የቻይና እዳ ባለመክፈሏ የእነሱን መዳብ ማምረቻ ስፍራ ካልወሰድን እያሉ አለምአቀፍ ጫና እያደረጉ ነው።
እኛም አገር ጠበቅ አድርገን ካልያዝን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ አበድረው ከሆነ ሆቴሉን እንውሰድ ሊሉ ይችላሉ። ለባቡር፥ መንገድና ግድቦቻችን ግንባታ ያበደሩትን ካልመለስን እንደዚሁ በምላሹ ሌላ ነገር ሊጠይቁን ይችላሉ። ደግሞም ወደድንም ጠላንም ቻይና የሚቀጥለው ቀኝ ገዢ ነው የምትሆነው።
በደንብ መረዳት ያለብን ነገር ቻይናውያን የሚሰጡትን ለፅድቅ አይደለም። ቻይና ላይ ያለን ፖሊሲ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ፍቅር የተጠመደ ሊሆን አይገባም። ይልቁኑ ምክንያታዊ የሆነ ግንኙነትና የጋራ ተጠቃሚ የሚያደርገን ነው መሆን ያለበት። እኛ ካለብን 27 ቢሊዮን ዶላር ብድር ውስጥ ምንአልባት ግማሽ ያህሉ የቻይና ነው ብዬ ነው የማስበው።
ከዚህ ውስጥ ከፊሉን እንኳ ብናሰርዝ ለእኛ ትልቅ እምርታ ነው። ምክንያቱም ከወጭ ንግድ የምናገኘው ከሶስት ቢሊዮን ዶላር አይበልጥም። በመሆኑም አሁን ያለው የአገሪቱ መንግስት በዚህን ጊዜ ብድር የማሰረዙን ጉዳይ ሊያስብበት ይገባል።
ይህ በሽታ ከቻይና ስለመምጣቱ ምንም ጥያቄ የለውም፤ ምንም እንኳን እነ ዶናልድ ትራምፕ ለፖለቲካ ግብዓት ቢጠቀሙበትም፤ በእኔ እምነት ግን ቻይና ላይ ቢገደብ ኖሮ የእኛ ችግር አይሆንም ነበር። ይህ ሆኖ እያለ እኛ ወገንተኝነታችንን ለቻይና አሳይተናል። ድጋፋችን አስመስክረናል።
ከአሊባባ ማስክ ባሻገር በመሰረታዊነት ወሳኝ የሆነ የብድር ስረዛ እንዲያደርጉልን ጫና ማሳደር ይገባናል። ደግሞ አሊባባ አንድ የቻይና ባለሃብት እንጂ መንግስታቸው ያደረገው ድጋፍ አለመሆኑን ማስታወስ ይጠበቅብናል።
አሁን ያለብን ግማሽ እዳ ማሰረዝ ከቻልን በሁለትና በሶስት አመት በውጭ ንግድ የማናገኘውን ነገር ነው የምናተርፈው። በአጠቃላይ ከመጥፎ ነገር ውስጥ ጥሩ ነገር ይዘን መውጣት እንችላለን ለማለት ነው የምፈልገው። ይሁንና በዚህ ጊዜ ዝም ብለን ቻይና አንዴ ካመለጠችን ትልቁ ስህተት ነው የሚሆነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለጂ20 አገራት 150 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገናል እንደሚሉት ሁሉ ለቻይና መንግስትም የብድር ስረዛ እንዲደረግልን ደብዳቤ መፃፍ አለባቸው ባይ ነኝ።
እዚህ አገር በኖርኩባቸው ስምንት አመታት ኢምግሬሽን እንደመሄድ የሚያሳቅቀኝ ምንም ነገር የለም።ለምሳሌ የእኛ ተቋም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሰዎች ለስብሰባና ለስልጠና እናመጣለን ግን ኦን አርይቫል ቪዛ መስጠት አይቻልም።
ለሶስት ቀን ስብሰባ የመጣ አንድ የውጭ አገር ዜጋ የአምስት ቀን ቪዛ ብቻ ነው የሚሰጠው። እነዚህ ሰዎች አንድ ሁለት ሳምንት ቪዛ ቢሰጣቸውና ሌላው ይቅርና ደብረዘይትና ሃዋሳን ጎብኝተው ቢሄዱ ለአገሪቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ያስገኙ ነበር። አንድ ሰው በቀን 250 ዶላር በቀን ኢትዮጵያ ውስጥ ካወጣ አንድ ኩንታል ቡና ገዛ ማለት ነው።
በሌላ በኩል አንድ ኩንታል ቡና ወደ ውጭ ብንልከው የትራንስፖርቱ፥ የጆንያውና የሰራተኛ ሲቀነስ እዚህ አገር የሚቀረው ሃብት 30 በመቶ አይሆንም። ስለዚህ እዚህ አገር ለሚመጣው እንግዳ ልታወጪ የምትችይው ግን አንሶላ መቀየርና ሳሙና ሻምፖ አውጥተሽ 50 ብር አይሞላም።

ኢ.ፕ.ድ ለሙሉ ቃለምልልሱ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/Ama/?p=31544

Filed in: Amharic