ካሳሁን ለማ
ይህንን አስተያየት ስፅፍ በዓለም ኡቀፍ ደረጃ አንድ ሚሊየን አንድ መቶ ሃምሳ አራት ሺ ስዎች ከቫይረሱ እገግመዋል ወይም ድነዋል::
መገናኛ ብዙኃን በቫይረሱ የተያዙቱንና የሞቱቱን ብቻ አጉልቶ በመዘገባቸው ለማሕበራዊ ቀውስ መፈጠር ምክንያት ሊሆን እንደሚችል በSociety ጉዳይ ላይ ጥናት ያደረጉ የመስኩ ባለሞያዎች አየሰጉ ይገኛሉ::
ሁልጊዜ አሉታዊዉን አጉልቶ በማሳየት ሚዲያዎች መሥራታቸው ከሚገኘው ጥቅም ይልቅ ውሎ አድሮ የሚያስከትለው ጥፋት ሊኖር ግድ ነው::በኢትዮዽያ ፖለቲካ ውስጥ እየታየ ያለ እውነታ ይኸው ነው !

በዚህ ያልተቀደሰ ጋብቻ ባለድሎቹ ወይም ተጠቃሚዎች በኪሳራ ወድቀው ለማንሰራራት ቆስለው ደፋ ቀና ሲል ለነበረው Jዋርና OMN ነው::ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው ከ97 ምርጫ በኃላ በደረሰበት የፖለቲካ ክስረት አፈር ልሶ ወደ ሕዝብ ጉያ በመመለስ ነጥብ አስቆጥሮ ወደ ቀደመ ቦታው እየተመለሰ ቢሆንም;በዚህ ወሳኝ ወቅት በሕዝብ በተተፋው ጅዋር ና የርስበርስ ጦርነት ናፋቂው OMN ስክሪን ላይ በመታየቱ የእስከዛሬ ጥረቱ በሰከንዶች ነጋቲቭ ዜሮ ላይ ወርዷል:: እንደሚታወቀው ጃዋር ለ86 ነብስ መጥፋት ; ልደቱ ደግሞ በ1997 ምርጫ ጋር በተያያዘ ከመቶዎች በላይ ንፁኃን ነብስ እጁ በአሉታዊ ሚናው ሲጠቀስ ቆይቷል::
የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ለመዘወር የሚነሱትና የሚወድቁት በአካልም የምናቃቸው በጣም ጥቂቶች ናቸው::እነዚህ ሊህቃን በዘርና ሥልጣን ሥር የሌለው ምሶሶ ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው::ሁለት ጣት የምትሆን ሚዲያ አላቸው::እንዲሁም ቁጥሩ ያልተገደበ የሶሻል ሚዲያ አካውንትና በፈለጉት ጊዜ የዘረፉትን ብር እየከፈሉ ዱላ ይዞ የሚወጣ ከተጨባጩ የኢትዮጵያና የአለም ሁኔታ የራቀ የፈረደበት ቄሮ አላቸው::ከዚህም በመለጠቅ በLike Shareና Subscribe በቁጥር ከሌላው ለመብለጥ የተሰለፋ Youtubers ጨምሮ ሌሎች Social mediaዎች ጩኸቱን በማጎን እያወቁ ተጠቃሽ አጨቃጫቂ ፖለቲከኞችን ድምፅ ያለቦታው ያስጮኃሉ ::ያኔ አገሪቱ ፖለቲከኛ እንደሌላት ተደርጎ በጥቂቶች ሶሻሉም መደበኛውም ይሰለባል::
በመግቢያዬ እንደገለፅኩት አሉታዊዉን በማግዘፍ ዓለም በኮረና ቫይረስ ምክንያት እንዳለቀላት ተደርጎ የተዘገበው ኢ-ፍትሃዊ የሚዲያ አቀራረብ አንድምታው በሌላ ፖለቲካዊ ጨዋታ በቁጥር እንኳን አስራአምስት የማይሞሉ ዘረኛና ሥልጣን ወዳድ አጭበርባሪዎች ባፉለጋቸው መንገድ እንዲፈነጩ ረድቷቸዋል::እነዚህ አስራ … ምናምን ሰዎች ከትግራይ ;ከኦሮምያና አዲስ አበባ መሆናቸው ልብ በሉልኝ::
ልደቱ በአንዴ OMN መስኮት የመጨረሻውን ማስተዛዘኛ ለመቁረጥ የተዘጋጀ ያህል ነው – ቃለ ምልልስ ሲጠቃለል የሚንግረን::እንደ ልደቱ ከመስከረም 30 በኃላ በኢትዮጵያ መንግስት የለም::አነጋገሩ ጃWarንና ፅንፈኞችን ለመቀላቀሉ የፊርማ ሰነድ ይመስላል::በርግጥም ነው !
ኢትዮጵያ የፖለቲከኛ ደሃ እይደለችም::የኢትዮዽያን ተጨባጭ ሁኔታ ተንተርሰው አፊሪካና ዓለምን ተንትነው በዝርዝር የሚያስቀምጡ አዕላፍ ፖለቲከኞች ከዳር እስከ ጥግ አላት::ጥቂት ባለ ጊዜ ብሔርተኞችና የአቋራጭ ሥልጣን ናፋቂዎች ሚዲያን ተሸሽግው ሊደፍሯት ሞከሩ እንጂ !
ልደቱ አያሌው ስለ ጃዋር “ፖለቲካዊ ተጠያቁይዊነት” የተንገረውን መጥቀሱ ጊዜ መፍጀት ነው;;ጃዋርም በአሽሙር የተናገረውንም ማቅረብ ይቻላል::በእነዚህ ሽምጥ ጋላቢዎች ላይ ብዙ መናገር ይቻላል::የመልዕክቴ ነጥብ ግን ያ ! አይደለም::
ፖለቲከኞች ስግብግቦችና ራስ ወዳዶች ናቸው::በተለይ ሚዲያ ካገኙ የሚናገሩትን አያውቁም::ልደቱ አያሌው ፖለቲከኛ መሆን ከጀመረበት አንስቶ እስከ OMN ያለውን ቃለ መጠይቅ Perspective ፈፅሞ ረስቶታል ወይም ሥልጣን ከመመኘት ራዕዩ አኳያ ሲታይ “ደንዝዟል” ብል ትክክልኛ አቀራረብ ነው ::
ችግሩ የኢትዮዽያ ሚዲያ ዜና ወይም ታሪክ እመራረጥ ነው;;ባጭሩ ሚዲያዎች ለአገር; ለሕዝብና ለመጪው ትውልድ ከመጨነቅ ይልቅ ለዕለቱ ላይክ;ሼርና ሰብስክራቭ ሲጨናነቁ ተስተውሏል::
በጣም ጥቂቶችን ከፍ አናድርጋቸው::ባለ ራዕዮችን ከፍ እናድርጋቸው::Jዋርና ልደቱ እንደ ኮረና ተጠቂዎቾና ሟቾች ለማገንን የምትሞክሩትን ያህል ;
ኢትዮዽያ በማንኛውም ቅፅበት ተሯርጠው ከተጠቃሽ አንድ ፍሬ ጥሬዎች የበለጡ ፈጥኖ ደራሾች አሏት!
… ይሁንና አሁን ደግሞ የጃዋር ሲገርመን የልደቱ አዲስ ትርክት የኢትዮዽያ መፃኢ በማጨለም ተጀምሯል::በፖለቲካው አቋም ረገድ ጃዋርና ልደቱ ማዶ ለማዶ ናቸው::ስልጣንን በአቋራጭ ለመያዝና ሕዝብን ለማንሳሳት በዕኩይ የሴራ ፖለቲካ በአንድ ላይ መሰለፍ አማራጭ የሌለው ጋብቻ እንደሆነ አምነውበት ወደ አደባባይ ዉጥተዋል::እዚህ ላይ ችግሩ ሚዲያዎች ሁኔታውን ( በተለይ ዩ ቲዩብ ) በማራገብ ሁለት ፍሬ የማይሞሉ እፍኝቶችን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ወሳኝ እንደሆኑ በማስመሰል ሁኔታውን ማጮሁ ተገቢ አልነበረም:መልካምና ለአገር ግንባታ ጠቃሚ የሆኑ ታዋቂ ፖለቲከኞች ; አክቲቪስቶችና የማሕበራዊ ሚዲያ አቀንቃኞችን ድምፅ ማጉላት ለሁለንተናዊ ዕድጉትና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት አስተዋፅኦቸው በአረንጏዴ ቀለም መሠመር አለበት::
እንደኔ የኮረና ቫይረስ አዲስ ተጠቂና ሟች እየተለየ የሚጮህለትን ያህል ከህመሙ የተፈወሱና ቫይረሱን ለማጥፋት ፊት ለፊት የገጠሙ የህክምና ሳይንቲስቶች;ዶክተሮችና ነርሶች ገድል እምብዛምብ አይፃፍም ወይም አይወሳም::በኢትዮዽያ ሚዲያዎች የሚስተዋለው ነጭ ሃቅ ይኸው ነው ::
ኢትዮዽያ በአሁኑ ሰዓት አሁን ያለውን የአገራቱን ፖለቲካና ህገ መንግስት የሚተነትኑ በርካታ ፖለቲከኞችና ተንታኞች አሏት::ዕድሉ ሊሰጣቸው ይገባል!
ለሁለት ፍሬ ሥልጣን ናፋቂዎች ያን ያህል መንጫጫት ተገቢነቱ አይታየኝም::ኢትዮዽያ ትልቅ አገር ናት::
የኢትዮዽያ ሕዝብ ያለ;የሚኖርና የሚቀጥል ታሪክ ያለው ሕዝብ ነው::ከመስከረም ሰላሳ በኃላም ጥቅምት አንድ ነው::
ለሀገር በጎ ራዕይ ያላቸው ድምፃቸው ይሰማ !