
በመርህ ላይ ቆመን እንዲህ እናስታውሳለን !!

ሀብታሙ አያሌው
የልደቱ ስህተት እነሱን ልክ አያደርግም የነሱ ከጉተና የከበደ ሴራ እና ፖለቲካዊ ውስልትና በልደቱ ደም ሊነፃ አይችልም።
ልደቱ ጀዋርን የኢትዮጵያ ችግር የመፍትሄ አካል አድርገህ በማሰብ ዱካ ጎትተህ ከጎኑ እየተቀመጥክ የአብይ ዙፋን እድሜው ይጠር እያልክ መራገም በየትኛውም መመዘኛ ልክ ሊያሰኝ አይችልም። የማሰብም ሆነ የመናገር መብትህ ግን ሊጠበቅ ይገባል። እንኳን ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ቀርጥፎ የበላው የጎረቤት አገር መሪው ኢሳያስም በኢትዮጵያ ፖለቲካ እየተንቧቸ ነው።
ለማንኛውም ከወዲያ ወገን የቆምከውም ቤተመንግስት በር ላይ ተንበርክከህ ደጅ የምትጠናበት የጉልበትህ ቁስል ሳይጠግግ ልደቱ ላይ ሐጢያት ፍለጋ ወደ ኋላ 97 ድርስ ሂደህ አትንፏቀቅ አይበጅህም።
ለጃዋር የሚቀርበው ማነው ??
የእትዮጵያ ህዝብ ይረሳው ዘንድ እሩቅ አይደለምና ይሄንን ላስታውስ …
1. ከ21 ባንኮች ላይ ዘረፋ በተደረገ ኦነግና ኦዴፓን ኮርማ አርዶ ያስታረቀው ሽማግሌ ጀዋር ነው የሚል ዜና ጆሯችን ሰምቶ አይናችት አይቷል
2. አማራ መጤ ነው በማለት እርጉዝ እናቶች እና ህፃናትን ሳይቀር ከነነፍሳቸው ገደል እየከተቱ ከጨረሱት ከነ ዲማ ነጋኦ፣ ሌንጮ ለታ ጋር የጋራ ድርጅት ፈጥሮ መቀመጥም ፅድቅ ነው ተብሎ ከበሮ ሲመታ ነበር።
3. በቅርቡ (ኦሮሞ ጋዲሳ) የኦሮሞ ድርጅቶች አንድነት ሲመሰረት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና ድርጅቶቹን አፈራራሚ ጀዋር መሐመድ ሆኖ በአደባባይ አይተናል።

5. የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን 86 ዜጎች በተገደሉ ማግስት ባወጣው መግለጫ “ጃዋር የኦሮሞ ህዝብ አይን ነው”ማለቱ አይዘነጋም።
6. ጠቅላይ ሚንስትር አብይ 86 ዜጎች በታረዱ ማግስት ወደ ሐረር አቅንቶ ባደረገው ንግግር “ኢስኮርት ያልኩት ጃዋርን አይደለም ጃዋር ወንድሜ ነው አብረን እየሰራን ነው” ማለቱን እናስታውሳለን።
7. የአብን አመራር እነ ደሳለኝ ጫኔ ከዳውድ ጋር ተጨባብጠው በአገር ጉዳይ እንመክራለን ያሉት በቅርቡ ነው።