>

ይድረስ ለአቶ ልደቱ አያሌው አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

ይድረስ ለአቶ ልደቱ አያሌው

አምባቸው ደጀኔ – ከወልዲያ 

በኮሮና ቫይረስ ከቀን እቀን መስፋፋት ምክንያት ከመጨነቂያ ጊዜየ አጣብቤ ባለችኝ ትንሽ ጊዜ ይህችን ደብዳቤ ለወንድሜ ለአቶ ልደቱ አያሌው መጻፍ አሰኘኝ፡፡ ብዙ ሰሞነኛ ጉዳዮች መኖራቸው ደግሞ እውነት ነው፡፡ ከቻልኩ አንዳንዶቹን አሁኑኑ በድርበቡ አነሳቸዋለሁ፡፡ ለሀገራችን እንጸልይ፡፡ ዛሬ ብቻ ባልተለመደ ሁኔታ 29 ሰው ጨመረብን፡፡ በዚህ ከቀጠለ አሳሳቢ ነው፡፡ 

አቶ ልደቱ አያሌው!

ስለትውውቃችን በማንሳት ጊዜ አላባክንም – በደምብ እንተዋወቃለን፡፡ በዚህ ሰሞን ከጃዋር ጋር ሆነህ ስትናር ከሰማሁት ተነስቼ ግን ጥቂት ነገር መናገር ፈለግሁ፡፡ ወንድሜ ጃዋር ማለቴ ልደቱ፡- አንድ ሰው የፈለገውን መውደድና መጥላት የራሱ መብት ነው፡፡ ግን አንድን ነገር ለመውደድ ወይ ለመጥላቱ በተለይ ሌሎችን የሚያሳምን ምክንያት ቢኖረው ጠቀሜታው ለራሱም ጭምር ነው፡፡ ለምሣሌ አንተ ከኢሳይያስ አፈወርቂ ይልቅ ደብረ ፅዮንን እንደምትወድ ያለ አንዳች ሀፍረት በግልጽ ተናግረሃል፡፡ ይህን ነገር እኔ በበሽታ እንጂ በጤናማነት አላየውም፡፡ ሰው ነኝ የሚል ሰው ሕወሓትን ሊወድ አይችልም – ሲጀመር፡፡

ልንገርህ – ሕወሓት በተለይ አንተ ወጣሁበት የምትለውን የአማራ ብሔር እንዴት አድርጋ በሞራልም በአካልም በመንፈስም አፈር ድሜ እንዳበላችውና አሁንም ድረስ እንዳልተኛችለት ካንተ የበለጠ የሚያውቅ የለም፡፡ አንተ ግን ከዘርህና ከብሔርህ ወይም ከሀገርህ እዳሪ የሚጣለው እህል ውኃ በልጦብህ የአማራን ገዳይ ወደድህ፡፡ መብትህ ነው ብሎ ማለፍ ቀላል ነው፡፡ ግን ያማልና መናገር አለብኝ፡፡ (የቅንፍ ወግ አንዳንዴ ጥሩ ነው፡፡ በጎጃም መስመር ነው አሉ፡፡ አንድ ሹፌር አንዲት እንጨት ይሁን ውኃ የተሸከመች ሴት መኪና መንገዱ ላይ አስቸግራቸው ኖሮ “ካንቺስ አህያ ትሻላለች!” ይላታል አሉ፡፡ እርሷም የዋዛ አልነበረችምና “የሚሻልዎትን እርስዎ ያውቃሉ ጌታው!” አለችው ይባላል፡፡ አህያ ራሷም በሰውኛ ዘይቤ “አልጋ ላይ ሲሏት ዐመድ ላይ” እንደምትል የታወቀ ነውና የልደቱ ምርጫ አዲስ ነገር እንዳልሆነ መረዳት ይቻላል፡፡)  

ደብረ ፅዮንና ወንድሞቹ ሕወሓቶች ከጎጃም ይልቅ የሲና በረሃ ቢለማ የሚመርጡ ናቸው፡፡ አማራ በስቃይ እየተንቀለቀለ እንዲሞት የሚመኙና የሚሠሩም ናቸው፡፡ ወያኔዎች አማራ ለማኝ እንዲሆን የሚጥሩና ለዚያም የሚሟሟቱ ናቸው፡፡ አማራን ያመከነው፣ ወንድ አማራን በህግ ስም አስሮ ካቲካላ እየጋተ ወንዱን በወንድ የደፈረው፣ የአማራን ሴት በወንድም በሴትም ከመድፈር ባለፈ በብልቷ የጋለ ብረት የከተተው፣ አማራን ዘር እንዳይተካ በአምካኝ መርዝና በብልት ቆረጣና ቅጥቀጣ ያኮላሸው፣ አማራን በጋለ ብረት ዐይኑን እየመለጎጠ ያጠፋውና እጅግ እግሩን የቆራረጠው፣ አማራን ያደኸየውና ማይም አድርጎ ያስቀረው፣ አማራን ከርስቱና ከመሬቱ ያፈናቀለው፣ አማራን በማይወክለው ሆዳም ብአዴን ተብዬ ያሰቃየው፣ የአማራን ታሪካዊ ግዛቶች እንደፈለገው ቆራርጦ ወደፈለገው ያካለለው፣ ለባዕዳን የሸጠውና የሚፈልገውን ያህል ለራሱ የወሰደው፣ አማራን ከሀገር ያሳደደው፣ አማራን ከሌሎች ወገኖቹ እንዲቆራረጥ የዘመናት የትስስር ገመዱን የበጣጠሰው፣ አማራን ከመኖር ወዳለመኖር የለወጠው … አንተ እንደይሁዳ በገንዘብ ተገዝተህ በፍቅር ያበድክለት ወያኔ ነው፡፡ አማሮችን በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በአሰቦት፣ በደምቢዶሎ፣ በቅርቡ ደግሞ 23 የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በወለጋ አፍኖ የፈለገውን ካደረገ በኋላ ድራሻቸውን ያጠፋው ኦነግ፣ በፍቅሩ ማርኮህ ከኢሳይያስ ይልቅ ጃዋርን ከመረጥክ ዲያቢሎሳዊ ምርጫህን ከማክበር ውጪ ሌላ አማራጭ የለኝም፡፡ እዚህ ላይ ያንተ የምርጫ ሜኑ ገርሞኝ እንጂ ኢሳይያስን ወደጄው እንዳልሆነ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ – ያ ሌላ ጉዳይና በሌላ ርዕስ መታየት ያለበት ነውና፡፡ እንደተረቱ ቂጥኛም ከውርዴ ይባላልና አንተም ሆንክ ቢጤህ ጃዋር ለኢትዮጵያ እንደማትተኙ ሀገራችንንና ህዝባችንን ለተለያዩ ተቋማት በመሸጥ በምታጋብሱት የደም ገንዘብ መረዳት እንችላለን፡፡ እንደናንተ ለመሆን ቢፈልጉ ከእናንተ በላይ አቅም ያላቸው በየመንደሩ አሉ፡፡ ይሁንና ከሆዳቸው ይልቅ ኅሊናቸውን መርጠው በድህነት መኖርን አስቀድመዋል፡፡ ጽዋው ሲሞላ ግን እናንተን አያድርገኝ፡፡ ወንድማችሁ ይሁዳም ክርስቶስን የሸጠበትን ገንዘብ ሳይጠቀምበት ተሰቅሎ ሞቷልና ምንም እንኳን በሽያጩ ገንዘብ አሁን ብትምነሸነሹ የነገ ዕጣችሁ ከይሁዳም የከፋ ነው፡፡

 ሰማይና ምድር ሊሸከሙት ቀርቶ ሊሰሙት የሚከብዳቸውን ግፍና በደል ያደረሰ ድርጅት አፍቅረህ ወያኔ መሆንን ከመረጥክ ጥቁር ውሻ ውለድ፤ የኢትዮጵያ አምላክ ፍርዱን ይስጥህ፡፡ በአንተ ክህደትና በወያኔ መሠሪነት የተጨፈጨፉ አማሮች ደምና አጥንት መቆሚያ አሳጥቶ የይሁዳን መጨረሻ ይስጥህ፡፡ ዕድሉ ደርሶን መጪዋን ጠባብ ቀን ሁለታችንም ብንሻገር በሕዝብ ፊት የምናገረው ይህንን እውነት ነው፡፡ 

አንድ ሰው ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን በአንድ ጊዜ ልውደድ ቢል የሚገጥመው የአንተ ዓይነት መጥፎ ዕድል ነው፡፡ ሀብትንም፣ ሥልጣንንም፣ ዝነኝነትንም… ወደድክ፡፡ ለነዚህ ስትል ደግሞ ብርሃንም ጨለማም መሆንን አሰኘህ፡፡ የክህደት ሥራህ በጊዜ እርዝማኔ የሚረሳ መስሎህ ከዓመታት መሰወር በኋላ እንደጅቡ ቁርበት አንጥፉልኝ ብለህ ከተደበቅህበት ዋሻ ወጣህ – ሀፍረት የሚባል ነገር የለህም፡፡ ለነገሩ እንዳንተ ዓይነቶቹ የአጋንንት ልጆች ሀፍረትንና ይሉኝታን አያውቁም፡፡አንተን የተጣባው ሰይጣን ከነወ/ሮ ስንዱ (ትግስት) ሰይጣን የሚበልጥ እንጂ አያንስም፡፡ ኢትዮጵያን ሸጠህ መናጢ ድህነትህን ጣልክና አሁን ሚሊዮነር ሆንክ – የገንዘብ ክብረትህ በራሱ ምንም ማለት አይደለም – መነሻው እንጂ፡፡ ፈጣሪ ግን መጥፎዎችን በሆነ ነገር ይይዛቸዋልና እኔ በንጹሕ ድህነት የማጣጥመውን ትዳር መሥርቶ ልጆችን ወልዶ የልጅ ልጆችን የማየት ፀጋ ፈጣሪ ከለከለህ፡፡ ይህም ሲያንስህ ነው፡፡ ገና ብዙ መጥፎ ነገሮችን ታያለህ፡፡ ምርጫ አጥቼ ክፉ በመሆኔ አዝናለሁ፤ ግን እንኳንስ እኔ ደካማው ፍጡር ክርስቶስም በጭንቁ ወቅት በመሳም አሳልፎ የሰጠውን እንዳንተ ዓይነቱን ከሃዲ ሰውዬ በአንገቱ የወፍጮ መጅ ታስሮ ወደጥልቁ ባህር ቢወረወር እንደሚሻለው ተናግሮ ነበር፡፡ የምትችል ስለመሆንህ እጠራጠራለሁ እንጂ ብትችል ተጸጽተህ ወደ ቀናው መንገድ በቶሎ ብትመለስ ደስ ይለኛል፡፡ ፈጣሪ ቢፈቅድልህ ጥሩ ዕውቀት አለህና ትጠቅመን ነበር፡፡ ዕውቀት ብቻውን ግን ዋጋ የለውም – ወደ ጥበብ መለወጥ አለበት፤ አባትህ ሰይጣንም እኮ በዕውቀት አይታማም፡፡ ጥበብ ደግሞ በጣም ውድ ናት፤ የክብሯ መገለጫም እንዳንተው ዕውቀት ፋንዲያ ሣይሆን ዕንቁ ነው፡፡ ስላንተ አበቃሁ፡፡

ወያኔ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሰሞኑን ሞተች፡፡ ዘመድ አዝማድ ካለ ወያኔዎች የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ብዙ ወጭ በማያስከትል መልኩ ቢፈጸም ደግ ነው፡፡ በዚያ ላይ በኮሮና ምክንያት ከአራት ሰዎች በላይ ቀባሪ እንዲኖር በህግ አይፈቀድምና ወያኔ ከዚህም በላይ ሳትበክትና ሳትግማማ በቶሎ ትቀበር፡፡ ኢሣይያስን ለማስገደል የተከናወነውን ሁሉ ከሚዲያዎች ተረዳን፡፡ የሚገርም ነው፡፡ ሃያ ሚሊዮን ዶላር ወይም 700 ሚሊዮን ብር አንድን ሰው ለማስገደል ወጪ ማድረግ እጅግ የሚደንቅ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት የነዚህ “ሰዎች” ሀብትና ንብረት የትዬለሌ ነው ማለት ነው፡፡ ቀደም ሲል ወያኔዎች ከኢትዮጵያ መብራት እያጠፉ ጭምር ቀን ከሌት እንደዐይጥ በሚያጓጉዙት የኢትዮጵያ ሀብት ትግራይ ልትሰምጥ ነው ሲባል ለአንዳንዶቻችን ቀልድ ይመስለን ነበር፡፡ ከዚያም ባለፈ “ትግራይ እስክትለማ ሌላው ሀገር ይድማ!” እየተባለ በየጋዜጣው ሲጻፍ ብዙዎች አያምኑም ነበር፡፡ እውነትነቱ ግን አሁን ተገለጠ፡፡ “እሳት በሌለበት ጭስ የለም” የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ ይበለን፡፡ ወደንና ፈቅደን ነው፡፡ ጥቂት ተምቾችን ተባብረን ከማስወገድ ይልቅ በዘርና በሃይማኖት እንድንከፋፈልና እንድንጫረስ በመልቲዎች በተተለመልን መንገድ ስንጓዝ ዋጋችንን አገኘን፡፡ ወያኔ ካልተቀበረች ገና ወደፊትም ብዙ አሳር ያገኘናል፡፡ ምክንያቱም የሀብታቸው ምንጭ ተዝቆ የሚያልቅ አይመስልምና፡፡ ተራው ትግሬ ቁልማንቁሉን ይዞ ይሰደዳል – እነሱ ግን አንድን ሰው ለማስገደል ስንትና ስንት ትምህርት ቤትና ሜካናይዝድ እርሻ የሚመሠርት ገንዘብ በከንቱ ያባክናሉ፡፡ ከዚህ በላይ መረገም ደግሞ የለም፡፡ ይህ እንግዲህ ለፈንጠዝያና ለቸበር ቻቻ እንዲሁም ለእነእንኮዬ ከሚነሰንሱት የተሰረቀ የሀገር ሀብት የተቀነጨበ መሆኑ ነው፡፡ ገንዘቡ ብቻም ሳይሆን የዳቦ መጋገሪያ መሽኖችን ጨምሮ ብዙ ንብረት እንደተዘረፈም እናውቃለን፡፡ ወያኔ እኮ ከዓለም በልክስክስነትና በወራዳነት አንደኛ ናት፡፡ የሀኪም ቤት ጄኔሬተርና የሕዝብ ሱቆችን መዝረፍ ይቅርና የተቦካ ሊጥ የሚሰርቁ ቅሌታሞች እኮ ናቸው፡፡

ወያኔ የራሷን ምርጫ ለማካሄድ መወሰኗን ሰማን፡፡ ያድርጉ፡፡ ከፈለጉም እንደሚቀላምዱት ይገንጠሉ፡፡ ቢገነጠሉ ማን እንደሚጎዳ እናያለን፡፡የጎጃምን ነጭ ጤፍ እያነከቱ፣ የወሎን ሴት እያቀፉ ከጎጃም ይልቅ የሲናን በረሃ መልማት የሚናፍቁ ውለታቢሶች መጡ ሄዱ ለውጥ የለውም፡፡ የበሉበትን ወጪት መስበር ደግሞ ዛሬ አልተጀመረም፡፡ ለነገሩ እነሱ ባሉት መንገድ የሚሄድ ታሪክ አላነበብንም፤ ይልቅስ ለራሳቸው ይዘኑ፡፡ በደረቅ አበሳ እርጥብ መቃጠሉ ያሳዝናል እንጂ በሠፈሩት ቁና የሚሠፈሩበት አበቅቴ እየተቃረበ ይመስላል፡፡

ሥልጣን የያዛችሁ አክራሪ ኦሮሞዎች ለራሳችሁ ስትሉ አደብ ግዙ፡፡ ይህ ጊዜ ማለፉ አይቀርም፡፡ አንድ ሰው ከአንድ ሰው ጋር ሲጣላ እንደሚታረቅ ሆኖ ቢጣላ ይመረጣል፡፡ እንደወያኔ ለዕርቅ የሚያስቸግር ጠብ መጣላት ገደብ ያጣ ዕብሪተኛነት ወይም በራስ የወፍጮ ቋት እንደመጸዳዳት የሚቆጠር ጅልነት ነው፡፡ በጅልነት ከቀጠሉ ደግሞ ታሪክ ራሱ ጨካኝ ነውና የማያወላውል ፍርዱን ይሰጣል፡፡ ወያኔ አማራ ላይ ባደረገው ግፍና በደል ዋጋ ሳያገኝ የሚቀር የሚመስለው ሰው ካለ የመጨረሻው ገልቱ ነው፡፡ ስፍሩ አይቀርም፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ብልኅ ሰው ቢኖር ግን መሀል ገብቶ ይቅርታና ምሕረት እንዲፈጠር በማድረግ የትንቢቱን ሸክም በተወሰነ ደረጃ ሊያቀለው ይችላል – ከጸሎት ጋር፡፡ ያልተሰማ አይነገርም – የተሰማ ደግሞ አይደበቅም፡፡ ከወያኔ ተዓምራዊ መንኮታኮት ቅንጣት ያልተማሩት በአማሮች ደንደስ ድል የተጎናጸፉት ኦሮሞዎች አሁን እያደረጉት ያለው የማንአለብኝነት ጀብድ መዘዙ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ብልጦቹ ያልቻሉትን ሞኞች ሊቋቋሙት አይችሉም፡፡ በፈለጋችሁት ተርጉሙት ወያኔዎች ብልጦች ነበሩ፡፡ በሠላሣ ዓመታት ውስጥ ያከናወኑትን ግፍና በደል እንዳለ ኮርጆ በሁለት ዓመት ውስጥ እውን ለማድረግ መሞከር በትንሹ ሞኝነት ነው – ከፍ ሲል ደግሞ የለዬለት ዕብደት፡፡ ስለዚህ በተለይ አማራን ከየመሥሪያ ቤቱ የማፈናቀልና ከአዲስ አበባና ሌሎች ቦታዎች የማስወጣት የጅልነት ሥራችሁን ቆም ብላችሁ አስቡበት፡፡ በተለይ በአሁኑ የኮሮና ወቅት የአማሮችን ቤት እያፈረሳችሁ ኦሮሞዎችን የምትተኩበት አካሄድ እጅግ አደገኛ መሆኑን መረዳት አለባችሁ፡፡ በዚህን የችግር ወቅት ቤት አይፈርስም፡፡ መፍረስም ካለበት ይደርሳል፡፡ አሁን ቤት ማፍረስ ማለት የእግዜርን ዐይን እንደመውጋት ነው፡፡ በሽታውንም ሆን ብሎ ማስፋፋት ነው፡፡ የመንግሥትን መጠለያ ሠርቶ ዜጎችን የማስጠለል ግዴታ በራሳቸው ውሱን አቅም የተወጡ ዜጎችን በዚህ የጭንቅ ወቅት ማፈናቀል ማለት ቫይረሱን ለኦሮሞውም፣ ለትግሬውም፣ ለከምባታውም… ለማዳረስ እንደመጣር ነውና ብታርፉ ይሻላል፡፡ ድንቁርናችሁን ወሰን አብጁለት፡፡ ከፈለጋችሁም ቀጥሉበት፡፡ መጨረሻውን ግን አትችሉትም፡፡ (በዘር መሥፈሪያ ስናገር ይሰቀጥጠኛል፤ ከሰውነት ደረጃም የወረድኩ ይመስለኛል፡፡ ግን ምርጫ አጥቼ ነውና ይቅርታ፡፡ አንሶ ከሚያሳንስ ይሰውራችሁ፡፡) … ደግሞ እባካችሁን ኮሮናን የገንዘብ (ማግኛ) ምንጭ የምታደርጉ የመንግሥት የፀጥታ አካላት ከዚህ ዕኩይ ተግባራችሁ ተቆጠቡ፡፡ ወገናችሁን በገንዘብ አትግደሉ፡፡ ብዙ የሚዘገንን ነገር ይሰማል፡፡

የኢትዮጵያ ንገድ ባንክ ፕሬዝደንት አቢ ሣኖ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ ልጅም ይውጣልህ፡፡ ብዙዎች ሠራተኞችህ እንደሚወዱህ ተረዳሁና ቢሮህ መጥቼ ላመሰግንህ ወደድኩ፡፡ ግን “ጊዜየ ገና” በመሆኑ ሳልሞት አንተን የማገኝበትን ብልኃት ፈጣሪ እንዲሰጠኝ እየተመኘሁ ፍላጎቴን ፊት ነሳሁት፡፡ ኦሮሞነትን፣ አማራነትን፣ ትግሬነትን … የተሻገረና ሰው ለመሆን የሚሞክርን ሰው መውደድ ቢለመድ መልካም ነው፡፡

በል እንግዲህ ልደቱዬ፡- ሞት አንዴ ነው፡፡ ልደትም አንዴ ነው፡፡ ቢቻል ሠርግም አንዴ ነው፡፡ ሁለቱን ጨርሰሃል፡፡ የሚቀርህ ሠርጉ ብቻ ነውና በርሱ በርታ፡፡ ሞትን ግን ደጋግመህ ለመሞት አትሞክር፤ ሰውም ይስቅብሃል፡፡ ከርስህ አንዲት ናት፡፡ እኔ የምኖረውን ኑሮ ብታይ ባለህ ትጽናናና ከብዙ መቅበዝበዝ ታርፍ ነበር፡፡ ለጊዜው የወጡን ነገር እንተወውና ለአንዲት እንጀራ ብለን እንደ እስስት መቀያየር ለታሪክም ለትውልድም አይበጅም፡፡ በኔ ይሁንብህ ይህን ቅምድምድ አንደበትህን ለሌላ ጉዳይ አውለው – የዕድር ወይም የዕቁብ ሊቀ መንበር ሁንና የመናገር አራራህን በዚያ ተወጣ፡፡ ከፖለቲካው ግን በተቻለ ፍጥነት ውጣ! አይዞህ አትሞትም ወንድማለም፡፡ በፈረንጆች ብሂል “ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች ባንድነት ይበራሉ” እንደሚባለው አንተው እንዳልከው መመዘኛህ ግልጽ ባይሆንልኝም ከኢሳይያስ ጃዋርን መረጥህ አይደል? ከሩቁ ኢሳይያስ የቅርቡን ደብሪፅን ወደድክ አይደለም? እውነቴን ነው የምልህ እኔ በበኩሌ ከሕወሓት ይልቅ ሰይጣንን እመርጣለሁ፡፡ ከኦነግ አስበልጬ ሉሲፈርን እወዳለሁ፡፡ ከልምድም ከንባብም እንደተማርኩት ሰይጣን ከአንተም ሆነ አንተ ከምታፈቅራቸው ወያኔዎች የበለጠ “ሰብኣዊነት የሚሰማው” ፍጡር ነው፡፡ ከርሱ ጋር መደራደር ይቻላል፡፡ አቋሙም ግልጽ ነው፡፡ ከአንተና ከወያኔ ግን መነጋገርና በድርድር መግባባት በፍጹም አይቻልም፡፡ እንዴ! ለድርድር ጠርተው እኮበተኙበት ጓደኞቻቸውን የሚያርዱ ናቸው፤ ያ ጠባይ አሁን ድረስ አልለቃቸው ብሎ የፈጣሪያቸው ያህል ይሰግዱለትና ያመልኩት የነበረውን ሰውዬ እኮ ነው ሊያስገድሉት የሞከሩት፡፡ በተንኮል ተጸንሰው በተንኮል ተወልደው በተንኮል ያደጉ ናቸውና ይህ ከደም ሥራቸው ጋር የተጣባቸው ተንኮል እስኪሞቱ አይለቃቸውም፡፡ እንደውነቱ አንተና አንተን መሰሎች ይህ ነው የሚባል የሚነገር ጠባይ የላችሁም፤ ባሕርያችሁ ሆዳችሁን እየተከተለ በእጅጉ የሚለዋወጥ በመሆኑ ከእናንተ ጋር መግባባትና መስማማት በጭራሽ አይታሰብም፤ አይቻልምም፡፡ ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውምና ጠባያችሁ ካላስቀበራችሁ አይለቃችሁም፡፡ በቃኝ፡፡

 

 EMAIL: martyrof2011@gmail.com

Filed in: Amharic