>

አቶ በረከት እና አቶ ታደሰ የ6 እና የ8 ዓመታት የእስር ውሳኔ ተላለፈባቸው!!! (ባልደራስ)

አቶ በረከት እና አቶ ታደሰ የ6 እና የ8 ዓመታት የእስር ውሳኔ ተላለፈባቸው!!!

ባልደራስ
ባለፉት 15 ወራት ጉዳያቸው በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲታይ የነበረው የአገሪቱ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት የፍርድ ሂደት ዛሬ ተቋጭቷል።
አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሠ ካሣ በጥረት ኮርፖሬሽንን በቦርድ ሰብሳቢነትና በዋና ሥራ አስፈፃሚነት ሚናቸው ጋር በተያያዘ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ጥር 2011 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱ ይታወሳል።
ከቀናት በፊት በሁለቱ የቀደሞ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ መተላለፉም ይታወሳል።
ዛሬ ሚያዚያ 30/2012 ዓ.ም የዋለው ችሎትም በ1ኛ እና 2ኛ የክስ መዝገቦች ላይ ጥፋተኛ በተባሉት በ1ኛ ተከሳሽ አቶ በረከት ስምኦን ላይ የስድስት ዓመት እስር እና የ10 ሺህ ብር የቅጣ ውሳኔ አስተላልፏል።
በ1ኛ፣ 2ኛ እና 4ኛ የክስ መዝገቦች ላይ ጥፋተኛ በተባሉት 2ኛ ተከሳሽ አቶ ታደሰ ካሳ ላይ ደግሞ የስምንት ዓመት የእስር ቅጣትና የ15 ሺህ ብር የቅጣት ውሳኔ ተበይኗል፡፡
ተከሳሾች ይግባኝ የማለት መብት እንዳላቸውም ተገልጿል።
Filed in: Amharic