አቻምየለህ ታምሩ
በታላቁ አትሌት በአበበ ቢቂላን ማንነት ዙሪያ ኦነጋውያን ባለፈው ዓመት ሰላሌ ላይ ሐውልት የቆመለት ፈጠራ ይዘው ብቅ በማለታቸው የታላቁን አትሌት ማንነት አስመልክቶ በወቅቱ ባካሄድነው ምርምር ያገኘነውን ውጤት በተለይም ልጁ ጽጌ አበበ ስለ አባቷ ታሪክና ማንነት የጻፍቸውን የቤተሰብ ታሪክ እዚህ ፈስቡክ መንደር አትመን ነበር። ስለ አበበ ማንነት የአብራኩ ክፋይ ከሆነችው ከልጁ ከጽጌ አበበ በላይ እናውቃለን የሚሉት ደፋሮቹ ኦነጋውያን ሐውልት ያቆሙለትን የፈጠራ ታሪክ ከሰሞኑም በልሳኖቻቸው በሰሩት ዶክመንትሪ በመድገማቸው እኛም ባለፈው አመት የታላቁን አትሌት የአበበ ቢቂላ ማንነት በሚመለከት የጻፍነውን ታሪክ ታነቡት ዘንድ ደግመን አትመነዋል። እነሆ ታሪኩ!
የኦሮሞ ብሔርተኛነት እንቅስቃሴ ስለ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሚደረግ ትግል ሳይሆን ሰማዩንም ምድሩንም «ኬኛ» የሚል የወረራና የመውረስ መንፈስ የተጠናወተው የዝቅተኝነት ፖለቲካ ነው። አዲስ አበባን ለመውረስ እያደረጉት ያለው ማሰፍሰፍ የዚህ የወረራና የመውረስ መንፈስ የተጠናወተው ፖለቲካቸው አንድ አካል ነው።

የኦሮሞ ብሔርተኞች ታላቁን ሰው አበበ ቢቄላን ወርሰው ኦሮሞ ሲያደርጉት የአበበ ቢቄላ የቤተሰብ ታሪክ አላስጨነቃቸውም። ፖለቲካቸው የዝቅተኛነት ደዌ የተጠናወተው የመውረርና የመውረስ በሽታ ስለሆነ ትልቅ የተባለን ሰው ኦሮሞ ካላደረጉ ሰው ሆነው የሚቆሙ አይመስላቸውም። መንግሥት ነኝ በሚለው አካል ተመርቆ በተከፈተው የባሕል ማዕከል ውስጥ ኦሮሞ ተደርገው ስለቀረቡት ሰዎች ማንነትና ታሪክ በባለሞያ ለማስጠናት ሙዝ የመላጥ ያህል እንኳ ሙከራ አላደረገም፤ እንዲደረግም አይፈልግም። የማጣራት ሙከራ የማይደረገውም እውነቱ/ውጤቱ የኦሮሞ ብሔርተኞች የማይፈልጉት ሆኖ ስለሚገኝ ብቻ ነው።

የአበበ ቢቄላን እውነተኛ ማንነትና ታሪክ ልጁ ጽጌ አበበ መጽሐፍ ጽፋ ነግራናለች። መጽሐፉም በእጄ ይገኛል። መጽሐፉ እ.ኤ.አ. በ1996 ዓ.ም. በእንግሊዝኛ ቋንቋ የታተመ ሲሆን ርዕሱ “Triumph and tragedy: A history of Abebe Bikila and his marathon career» By: Tsige Abebe ይሰኛል።
የአበበ ቢቂላ ልጅ ጽጌ አበበ ስለ አባቷ ታሪክ ባሳተመችው መጽሐፏ እንደነገረችን የአበበ እናት የመዝን ተወላጅና የቄስ ልጅ የሆኑት ወይዘሮ ውድነሽ ሲሆኑ በሕይወት ዘመናቸው ሶስት ባሎችን አግብተዋል። የመጀመሪያው ባላቸው ቢቂላ ይባላሉ። ወይዘሮ ውድነሽ ከአቶ ቢቂላ የመጀመሪያ ልጃቸውን ኮሎኔል ክንፈ ቢቂላን ወልደዋል። ኮሎኔል ክንፈ የክቡር ዘበኛ አባል የነበረ ሲሆን አበበ ቢቂላን ክብሩ ዘመኛ እንዲቀጠር ያደረገው የአበበ የእናት ልጅ ነው። [ምንጭ: Tsige Abebe (1996)Triumph and tragedy: A history of Abebe Bikila and his marathon career, Page 6]
ወይዘሮ ውድነሽ አቶ ቢቂላን ፈትተው ሁለተኛ ባላቸውን አቶ ደምሴን አገቡ። ከአቶ ደምሴ አበበን ወለዱ። አበበን በወለዱ በሶስት ዓመቱ የአበበ አባት አቶ ደምሴ በእድሜ ወጣት ስለነበሩ እሳቸውን ፈትተዋቸው ሶስተኛ ባላቸውን አቶ ተምትም ከፈለውን አገቡ። ጽጌ ያባቷን ታሪክ በጻፋችበት መጽሐፏ ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ ትለናለች፤
“When he[Abebe] was three, his mother, Wudinesh Beneberu divorced Abebe’s father and married her third husband Temtime Kefelew. Wudinesh maintained that she divorced her second husband Demissie (Abebe’s father) because he was too young for her”. [ምንጭ ፡ Tsige Abebe(1996), Triumph and tragedy: A history of Abebe Bikila and his marathon career, Page 1]
ከዚህ ጽጌ አበበ ስለ አባቷ የጻፈችው ታሪክ የአበበ አባት አቶ ደምሴ እንደሆኑ በግልጽ ይታያል። አቶ ደምሴ የወይዘሮ ውድነሽ በነበሩ የትውልድ ቦታ የመዝን ሰው እንደሆኑም ጨምራ ጽፋለች።
ስለዚህ ቢቂላ የአበበ እናት የመጀመሪያ ባል እንጂ አበበ ከተወለደ በኋላ እናቱ ያገቡት የእንጀራ አባቱም አይደሉም። የአበበ እንጀራ አባት እናቱ ወይዘሮ ውድነሽ ሁለተኛ ባላቸውንና የአበበን አባት አቶ ደምሴን ፈትተው ያገቡት ሶስተኛው ባላቸው አቶ ተምተም ከፈለው ናቸው። አበበን እስከ ሰባት ዓመቱ ድረስ ያሳደጉትና አበበም ከአዲስ አበባ ወደ ጅሩ እየተመላለሰ ይጎበኛቸው የነበሩት የእንጀራ አባቱን አቶ ተምትም ከፈለውን እንደነበር ጽጌ አበበ ያባቷን ታሪክ በጻፈችበት መጽሐፏ ነግራናለች።
አበበ ደምሴ የአባቱ ስም ቢቂላ ተደርጎ እንዲጠራ የተደረገው አበበ ክቡር ዘመኛ ሲቀጠር እናቱ ከአበበ አባት በፊት ካገቡት ከመጀመሪያ ባላቸው ከአቶ ቢቂላ የወለዱት ወንድሙ ኮሎኔል ክንፈ ቢቂላ ክቡር ዘበኛ ሲያስቀጥረው “ወንድሜ ነው” ብሎ ሲያስመዘግበው ነው። ይህንንም የምትነግረን የአባቷን ታሪኩ የጻፈችው የአበበ ልጅ ጽጌ አበበ ናት። የአበበ ታሪክ ይህ ነው። ከዚህ ውጭ አበበና አቶ ቢቄላ የሚያገናኛቸው አንዳች የአባትና ልጅ ግንኙነት የለም። አቶ ቢቂላ የአበበ የእንጀራ አባት እንኳ አይደሉም።
እንግዲህ! የኦሮሞ ብሔርተኞች አትሌት አበበ ደምሴን የማያውቃቸው የቢቂላ ልጅ አድርገው ሙዚያም ውስጥ ኦሮሞ አድርገው ያስገቡት የአቶ ደምሴን ልጅ ያለ አባቱ የቢቂላ ልጅ አድርገው ነው። ኦነጋውያን አበበ ደምሴን የማያውቃቸውና የእንጀራ አባቱ እንኳ ያልሆኑት ሰው ልጅ አድርገው ኦሮሞነት አላብሰው የኦሮሞ ሙዚዬም ውስጥ ሲያስገቡት ልጆቹ፣ ቤተሰቦቹና ዘመዶቹ ምን ይሉን ይሆን የሚል ነገር አያስጨንቃቸውም። የፈጠራ ታሪካቸውም የሚጋለጥባቸው አይመስላቸውም።

ሆነው ግን የኦሮሞ ብሔርተኞች የተጠሩት ኢትዮጵያ ጠሎች ሆነው ስለሆነ ስለ ኢትዮጵያ ሟች የሆኑትን እነ ራስ ጎበናንና ጀኔራል ሙሉጌታን ማስታወስ አይሹም ፤ «ባሌና አርሲን ገሎጥዬ ከሃይማኖት ወንድሞቼ ከሶማሌዎች ጋር እዋሃዳለሁ» ብሎ ሞቃዲሾ የሸፈተውንና ለዚህም አላማው ዚያድ ባሬ የጄኔራልነት ማዕረግ ሰጥቶ በኢትዮጵያ ላይ ያሰማራውን ዋቆ ጉቱን በመማረክ ዘመቻውን ያከሸፈውንና ዋቆ ወደ ሶማሊያ ሪፑብሊክ ሊጠቀልላቸው የነበሩትን ባሌና አርሲ የታደገውን ጀኔራል ጃጋማን ማንሳት አይፈግሉም። አበበ ቢቂላ ራሱ በሕይዎት ቢኖር ኖሮ እንኳን ስሙን ሊያነሱና መታሰቢያ ሐውልት ሊያቆሙት አማራ በመሆኑ ብቻ በላቡ ያፈራውን ንብረት ልክ በኃይለ ገብረ ሥላሴ ላይ እንደሚያደርጉት “ነፍጠኛ” እያሉ ያወድሙበት ነበር።
እነ ሰማዩም ምድሩም የኛ ውሸት ማምረታቸውን ወደፊትም ይቀጥላል! እኛ እንዲህ እየተከታተልን ውሸታቸውን ራቁቱን ማስቀረቱን እንቀጥላለን!
⇑ከላይ የታተሙት ሶስት ገጾች የአበበ ቢቄላ ልጅ ስለ አባቷ ታሪክ ያሳተመችው መጽሐፍ ሽፋን፣ ስለ አበበ አባትና የእናቱ ሁለተኛ ባል ስለሆኑት ስለ አቶ ደምሴና ስለ አበበ እናት የመጀመሪያ ባል ስለ አቶ ቢቂላ የጻፈችውን ታሪክ የሚያሳዩ ናቸው።