>

ስቶክሆልም ሲንድረም....!!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ስቶክሆልም ሲንድረም….!!!!

 

ቬሮኒካ መላኩ
ለበቀለ ገሪባ ከጌታቸው አሰፋ ይልቅ መርሃቤቴ ወይም መንዝ የሚያርስ ታታሪ ገበሬ ጠላቱ ነው፡፡  እዚህ አርሶ አደር ፊት ቢቀርብ “ይንቀኛል!” ብሎ ጥላቻውን ይጀምራል፡፡ በቀለ ገሪባ inferiority complex ሲደመር Stockholm syndrome ተረባርበው የሚያሰቃዩት የሚታዘንለት ሰው ነው!!!
 
አሳሪህን መውደድ፡ ጀርባህ እስኪተላ የገረፈህን ማፍቀር፡ ብልትህ ላይ እንስራ ውሃ ያንጠለጠለብህን መናፈቅ አድስ ነገር አይደለም፡፡ የዚህ በሽታ ተጠቂዎች በአለም ላይ አሉ፡፡በዚህ ሲንድረም የተለከፉ ሰዎች  የደረሰባቸውን በደል ሽምጥጥ አድርገው መካድ ብቻ ሳይሆን ገራፊያቸውን ልባቸው እስኪጠፋ ያፈቅራሉ፡፡ይህ ሲንድረም ስቶክሆልም ሲንድረም ይባላል፡፡
በቀለ ገሪባ  በ2010 ለፍርድ ቤት ሳይቀር ፊቱ ቲማቲም እስኪመስል ምራቃቸውን እየተፉ የገረፉት መሆኑን የተናገረውን ቪኦኤ ዘግቧል፡፡ በቄ ግን በመአከላዊ ገራፊዎች ፍቅር እየተብሰለሰለ ነው ፡፡ በቀለን ዛሬ ላይ “ማን ነው የገረፈህ ? ” ብለው ቢጠይቁት ” አፄ ምኒልክ ነው ” ከማለት አይመለስም፡፡
Stockholm syndrome  የሚለው የሲንድረም አይነት የታወቀው ከ44 አመታት በፊት  በሲዊዲን ነው፡ ፡ በ1974 ሁለት በከባዱ የታጠቁና የሚፈነዳ ፈንጅ  ሰውነታቸው ላይ ያጠመዱ ሁለት አጋቾች ሲውዲን ዋና ከተማ ስቶኮልም የሚገኝ ባንክ ይገቡና ታጋቾችን ለ131 ሰአታት ያሰቃዮቸዋል፡፡ በመጨረሻ በፖሊስ ጥረት አጋቾቹ በቁጥጥር ስር ይውላሉ፡፡ በመጨረሻ ግን ስቃይና መገረፍ በደረሰባቸው ታጋቾች ላይ የሚስተዋለው አድስ ባህሪ ሁሉንም ግራ አጋባ፡፡
ሁሉም ታጋቾች  131 ሰአታት እየገረፉ ካሰቃዮቸው አጋቾች ጋር ፍቅር ከመያዝ አልፎ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በተፈረደባቸው አጋቾቻቸው የሚሆን የጠበቃ ገንዘብ እስከማሰባሰብ ደረሱ፡፡ ከዛ በሗላ Evolution psychologist ይሄን ክስተት Stockholm syndrome በማለት ይጠሩታል፡፡
በቀለ ገሪባ የስቶኮልም ሲንድረም ተጠቂ ነው፡፡ ለበቀለ ከጌታቸው አሰፋ ይልቅ መርሃቤቴ ወይም መንዝ የሚያርስ ታታሪ ገበሬ ጠላቱ ነው፡፡  እዚህ አርሶ አደር ፊት ቢቀርብ ይንቀኛል ብሎ ጥላቻውን ይጀምራል፡፡ በቀለ ገሪባ inferiority complex ሲደመር Stockholm syndrome ተረባርበው የሚያሰቃዩት የሚታዘንለት ሰው ነው፡፡
Filed in: Amharic