>

ለፈንቅል የትግራይ ወጣቶች ትግል የቀረው ኢትዮጵያዊ የሰጠው ድጋፍ የሕወሓት. ሰዎችን ክፉኛ አስደንግጧል !!!`` (ታምሩ ገዳ - ሕብር ሬዲዮ)

ለፈንቅል የትግራይ ወጣቶች ትግል የቀረው ኢትዮጵያዊ የሰጠው ድጋፍ የሕወሓት. ሰዎችን ክፉኛ አስደንግጧል !!!“

ታምሩ ገዳ – ሕብር ሬዲዮ
🛑 “  የህዝብን ጥያቄ ለመደፍጠጥ  የሚያስቡትን ሕወሓቶችን ብቻ ሳይሆን ፤የዲጂታል ወያኔ እና ከሕወሓት መሪዎች ጋር የስልት ቁርኝት የፈጠሩ ትግሉን ጠልፈው ስልጣን ለማራዘም ለሚሞክሩም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ  ነው “ 
የትግራይ ወጣቶች በሕወሓት መንደርተኛ አመራሮች እየደረሰ ያለባቸውን ግፍ ተቃውመው አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ ከሌላው ኢትዮጵያዊ የተሰጣቸው የሞራል ድጋፍ ህወሓት መሪዎችን እና አባላት እና ደጋፊዎቻቸውን ማስደንገጡን በተለያዩ መንገዶች እያስተዋልን ነው።
ሕወሓት እኔ ከሌለው ያጠፉሃል የሚለው ለዓመታት የደከመበት ቅስቀሳና የትግራይ ህዝብን ነጥሎ ባሪያ አድርጎ ረግጦ መግዛት የሚያበቃበት ጉልህ ምልክት መታየት መጀመሩን ተከትሎ ክስ ትግራይ ትገነጠላለች፣የፌደራል መንግሥት ለወረራ ተዘጋጅቱዋል የሚሉና ጠላቶቻችን ተባበሩ በሚል ግልጽ ጥላቻቸው ከማህባራዊ ሚዲያ እስከ ታች አደረጃጀት ቅስቀሳ መጀመራቸው እየተስተዋለ ነው።
ፈንቅል ተጋሩ በትግራይ ያልጠበቁትን የተቃውሞ ማዕበል ፈጥሮዋል። ወጣቶች ብቻ ሳይሆኑ ልጆቻቸውን ለትግል ገብረው የህወሓት መሪዎች በመንደርተኝነት ፣አምቻ ጋብቻ ከሚዘርፉበት የጭቆና ስርዓት ምንም ያልተጠቀሙ የወረዳ ጥያቄውን ለማዳፈን የተሞከረውን በመቃወም እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን አድርገው የፈጸሙትን ርሸና ያንገፈገፋቸው ባልተጠበቀ ሁኔታ በአደባባይ የትግል መሪዎቻቸውን ይፋ እስከማድረግ ደርሰዋል። የቀረው ትግሉን አፋፍሞ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ማህበራዊ ርቀት ጠብቆ እንዲካሄድ እና ጥያቄውን በስልት እንዳያዳፍኑት መህፋት ነው።
የዲጂታል ወያኔ እና ከሕወሓት መሪዎች ጋር የስልት ቁርኝት የፈጠሩ የሚያወሩት ጫጫታ በቀላሉ የህዝቡን ትግል የሚቀለብሰው አይመስልም። ሕወሓት ዛሬ ድረስ የዘለቀው የሀይል እርምጃ የበለጠ ትግሉን ያግለው እንደሁ እንጂ እንደማያደክመው የመቀሌውን ወጣት ግድያ የተከተለውን መታዘብ ይቻላል። ጥያቄው የፈንቅል መሪዎች የሕወሓት ግድያ ጉያቸው ስለገባ ፈንቅል ለመጣል ብቻ ሳይሆን ተቀናቃኞቹን በድርድር እና ስምምነት፣ሽምግልና እና የሀሰት ተስፋ እየሰጠ እንዴት እንደሚያጠፋ መገንዘብ ይገባቸዋል።
የትግራይን ሕዝብን በጠላት እንደተከበበ አድርገው ሲዘርፉት የኖሩት መሪዎች ለፈንቅል ተጋሩ የቀረው ወገን የሰጠው የሞራል ድጋፍ ማስደንገጡ ብዙ አያስገርምም።መቀሌ ላይ ወጣቱ አፓርታይድ ያለውን መንደር የገነቡ፣ልጆቻቸውን ውጭ የሚያስተምሩ፣ስልጣን በአንድ ጎጥ የበላይነት ተወስኖ እንዲቀር ሲሰሩ የነበሩ ይፈራናል ያሉትን ወጣት ሲያስደነብራቸው ማየት ትልቅ እርምጃ ነው።
ደርግ የለ ሻዕቢያ የለ አብይ የለ አረብ የለ ትምክህተኛ ጽንፈኛ ቀርቶ ሺህ ውንጀላ ቢደረድሩ ጥያቄው በፈንቅል የቀረቡ ሰባቱን የህዝቡን ጥያቄ ትመልሳላችሁ አትመልሱም ነው። የህወሓት ባህሪ ድግሞ ይህን አይፈቅድም። መፍትሄው በእርግጥም ፈንቅል ተጋሩ ስኬታመ ትግል መርቶ ዳር ማድረስ ብቻ ነው። የቀረው ወገን ይህን የወገኖቹን ህዝባዊ ጥያቄ መደገፍ የህዝብን ጥያቄ ለመደፍጠጥ የሚያስቡትን ሕወሓቶችን ብቻ ሳይሆን ትግሉን ጠልፈው ስልጣን ለማራዘም ለሚሞክሩም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ የለውጡ እሳት ከትግራይ አልፎ ምሳሌ መሆን እንዲችል የፈንቅል ተጋሩ መሪዎች ትልቅ ሀላፊነት ነው። የቀሩትም ወጣቶች ባሉበት ሊደግፉ ይገባል።
ፈንቅል ተጋሩ እስከ ድል ይደገፍ ለማለት እንወዳለን።
Filed in: Amharic