>

የእንሥራ ውስጥ አይጥ ...!!! (ተስፋዬ ሀይለማርያም)

የእንሥራ ውስጥ አይጥ …!!!

ተስፋዬ ሀይለማርያም

አይጧ ውሃ የሞላበት እንሥራ ውስጥ ድንገት ገባች። ከእንሥራው ለመውጣት ብዙ እየዋኘች ደጋግማ ብትሞክርም  አልቻለችም። በሙከራ ብዛት ብዙ በመዋኘቷ እየደከመች ሄደች። በመጨረሻም እየዋኘች እያለች ለራሷ እንዲህ ስትል ቃል ገባች፣
“ሁለተኛ የእንሥራ ውሃ አይለምደኝም። ሁለተኛ”
አይጧ ከገጠማት አደጋ መትረፍና አለመትረፏን ገና ሳታውቅ ሁለተኛ የእንሥራ ውሃ ማለቷ ምስኪን ወይም ሞኝ መሆኗን ያሳያል።
ህወሃትም በአሁኑ ጊዜ እንሥራው ውስጥ የገባችውን አይጥ ትመስላለች። ከታች የተለጠፈው ምስል በብዙ የህወሃት ካድሬዎችና የዲጂታል ወያኔዎች የፌስቡክ ላይ ተለጥፎ ሲንቀዋለል አገኘሁት።
አንድን ሰው ህልም እንዳያይ ወይም ቅዠት እንዳይቃዥ ልትከለክለው አትችልም። እንደፈለገው ማለምና መቃዠት መብቱ ነው።
ህወሃት ከ45 ዓመት በፊት ስትመሠረት የነበራት ህልም ኤርትራን አሰገንጥላና ከኤርትራ ጋር በመዋሃድ “ታላቋ ኤርትራ”ን መመሥረት ነበር። ያንን ያረጀ ህልም ያውም በዚህ ዘመን እነ ደብረጽዮን የጌቶቻቸውን ኤርትራ አዋህደው ታላቋ ትግራይ ወይም አባይ ትግራይን በመመሥረት ህልም አሻሽለውታል።
ሂዊ (ህወሃትን ሳቆላምጣት ነው) አራት ኪሎ ቤተመንግሥት መመለስ እንደማትችል ስታውቀው ይሄንን አዲስ ህልም አልማለች።
ሞኟ ሂዊ እስቲ መጀመሪያ ከሰመጥሽበት የእንሥራ ውሃ ውስጥ ራስሽን አድኚ። አይጥ።
Filed in: Amharic