>

የጆርጅ  ፍሎይድ በዘረኝነት የተመሰረተ ድያ የአለም ህዝቦች ጸረ ዘረኝነት  አመጽ ያነሳሳ... (ክፍል  2 - ከአስገደ ገብረስላሴ)  

የጆርጅ  ፍሎይድ በዘረኝነት የተመሰረተ ድያ የአለም ህዝቦች ጸረ ዘረኝነት  አመጽ ያነሳሳ…

ክፍል  2
ከአስገደ ገብረስላሴ

  I can t breathe ( ማስተንፈስ አልቻልከም ) ጆርጅ ፍሎይድ) የጥቁር አመሪካዊ  የድሮሱልኝ  የጣረ ሞት ደምጽ   ፤ በነጭው  አመሪካዊ ፖሊስ ለደረሰ  ዘርአዊ ግፍ  የተሞላበት ግድያ ፤ የአፍሪካና የአረብ አገሮች ህዝቦች ፤መንግስታት  ኢትዮጱያም ጭምር  ሲቀሩ ሌሎች የአለም ህዝቦች ፤የአገር መሪዎች  ቀለም ፣ዘር ሀይማኖት  በማይለይ ለሰው ክብር  በመወገን የጆርጅ ፍሎይድ የጣረሞት የድረሱልኝ  ጥሪ እንደ ፤  ቀለም  ዘር ፣ሀይማኖት በማይለይ    we can t breathe(መተንፈስ አልቻልንም የሚል  መፎከር ይዘው በመላው  አለም አደባባዮች ወጥተው ለመንግስታት ፣ ለሰባአዊ መብት ተማጓቾች ( ተጣባቂ) ማህበረሰብ ፣ለአንባሳደሮች መዝግያ በማንኳኳት  የኮቪድ 19 የኮሮና ወረርሽን  አትንቀሳቀስ ፣ከቤት አትውጡ የሚለው አዋጅ  ሳያግዳቸው ለሰው ልጅ መብት መጠበቅ በማስቀደም  ለመስዋእቲ በሁለተኛ ደረጃ በማየት የተቃውሞ ሰልፍ ወጥተው   እንሆ 12 ቀን አስቆጥራል ።  እንዳው I can t breathe የሚል የጣረሞት ድሙጹ ዋቢ በማድረግ we can breathe  የሚለው የአአለማችን  ቀዋሚ ሞፎከር  ሆኖዋል ።
            የተከበራቹ ወገኖቼ በክፍል 1 ጽሁፌ እንደገለጽኩት የአውሮፓ ፣የአመሪካ ፣የከናዳ ፣የአውስትራልያ  ለሰው ልጅ ያላቸው  ክብር በሰፊው አይተናል ።በቢሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች በአደባባይ በመውጣታቸው  የሀገር መሪዎች እስከ በየቤተ መንግስታቸው ከመሬት በታች እስከ መደበቅ አድርሶዋቸዋል ።
         እጅጉን የሚያስደነቅ ግን የአመሪካ መከላከያ ምኒስቴር ትራንብ የሀገር መሪ ሆኖ  የሀገራቸው  ህገመንግስት በመርገጥ  የሚደረገው ያለው ተቃዎሞ ሰልፉ በሀገር መከላከያ ወታደር አዝምተህ በሀይል በትነው  ብሎ ትራንብ  ጥብቅ ትእዛዝ ሲሰጠው ፤ በሳላው የህገመንግስት ታማኝ  ጋርድ የሆነው ጀነራል ግን አልቀበልሞ የሀገራችን ህገመንግስት አይፈቅድልኝም ብሎ የሚደረግ ያለው የተቃውሞ ሰልፍ  ህገመንግስት መብታቸው በማለት ለፕረዝዳንት ትራንብ ሲያሳፍረው ያየንበት ዘመን ነው ። ይህ ነው የህገ መንግስት ጠባቂ ወታደር ማለት  ።
           የኛ መከላከያ ሰራዊት  29  አመት ሙሉ አስከ አብይ አህመድ የስልጣን ጊዜ  በአብይ አህመድ ጭምር ወደ ህዝብ ተኩስ ወይ ሰላማዊ ሰልፍ በወታደር በትን ሲባል ጥያቄ አንስቶ ያውቃልን ? በበኩሌ ይቅር ሰላማዊ ሰልፊ ማድረግ የዘጎች ህገመንግስታዊ መብታቸው ነው ብሎ ጥያቄ ሲያነሳ ተሰምቶ አያውቅም ።እንዳው  ሻለቃ  ፣ ብርጌድ ፣ክፍለጦር ፣ኮር ሰራዊት አንቀሳቅስ ከተባለ መካኒካል እንደ ሞቶር ተነድቶ የሚሄድ ጀነራል እንጅ አቋሙ ይዞ  እኔ የህገመንግስት ዘበኛ ነኝ   ህዝብ የሰጠኝ ሀላፍነት ነው ብሎ  ሲሟገት አላየሁም ፣ አልሰማሁም ወታደሩም እንደዚሁ ለወገኑ አይጣበቅም ።  በመላው ኦሮሞ ፣በሰሜን ሽዋ ፣በጎንደር በሁሉም አካባቢዎች ፣በሱማል በደቡብ ህዝቦች ቢሄር ቢሄረሰቦች ፣በውራጌ ፣በጌዶኦ ፣ በሲዳማ  ፣በወላይታ ፣በጉጅ ፣በሞያሌ ፣በቤልሻንጎል፣ በጋንቤላ  በሱሟል፣በዒሳና ዓፋር አሁንም በኦሮሞ የሚካየድ ያለው ጦርነት እየፈጸመው ያለው ጦርነት መካላከያ ምኒስቴ በጀነራሎቼ የሚመራ  ነው ።
           እንግዲህ የአፍሪካውያን ያለው  ለሰው ልጅ ክብር  ተቆርቋሪነት ይቅርና በአጠቃላይ ይቅርና የራሳቸው  ወገን የሆነው ጥቁር ዘር  እንካን ስልጣን ከያዙ ለዜጋቸው ልክ ከእንስሳ በታች በማየት የራሳቸው ክብር የገደሉ ናቸው  ይህ ደግሞ ደንቅርና  ነው ።
            ወደ ኢትዮጱያ ሀገራች እንሞጣ  በኢትዮጱያ ሀገራችን የነበረው እና አሁን ያለው በክፍል አንዴ  ጽሁፉ ነካ ነካ አድርጌው ነበር ። ግን አሁንም ለማየት እሞክራለሁ ። እንግዲህ በዘመነ መለስ ዜናዊና ሀይለ ማርያም ደሳለኝ  ህዝቦች እምቢ ለመብታችን ብለው  ሰልፍ ሲወጡ በሀገር መከላከያ  በጀነራሎች የሚመራ ወታደር ቁንጮው በለው ካለው  በጅምላ  ይረሸናል።ይህም በኦሮሞ ፣በሱሟል ፣በአዲስ አበባ በሌሎች ከተሞች አእላፍ አልቀዋል ።ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ አፍኖ ማሰር ለአመታት ያህል ደብቆ ማቆየት ፣ማጥፋት በወታዶሮቹ አይን ወንጀል አይደለም ።ታስሮ ተገርፏል ፣ተገዶ በሀሰት ምስክር ኢፍትሀዊ ውሳኔ መፍረድ ፣ለዜጎች በዱላ ደብድቦ መግደል ፣ በህቡእ እሱር ቤቶች  ዜጎች  ለረጅም አመታት ታስረው በጤና እጦት ፣በጭንቀት ቀጭጨው ለሞት  ተቃራርበው ይወጣሉ ።እነዚህ እድሎኞች ናቸው ። ከጠፉት ይሻላሉ ።  በመሁኑም  ወቅት የኢትዮጱያ መከላከያ ምኒስቴር ጦር አዛዞች ፣ወታዶሮቻቸው ከአመሪካ ጦር ጀኖራሎች ቢማሩ መልካም እላለሁ ።እኔም የዝህች ጽሁፌ መልእክትም ለሀገራችን ጀነራሎች ጭምር ናት
            ይህ ሁሉ ሲደረግ  አንድ አንድ ፖለቲኮኞች ሚዲያ ካገኙ ትንሽ ይተነፍሱ ነበሩ እንጅ ሌላው ግን በኦሮሞ ይህ ያህል ሰው ሞተ ፣ታሰረ፣ተገደለ ለስሟል ለኣማራ ምኑ አይደለም   የትግራይ ህዝብ ይህን ያህል  ተገደሉ ፣ታሰሩ ፣ጠፉ ለራሱ የትግራይ ህዝብ ፣ለአማራው ወይ ለደቡብ ፣ለጋንቤላ ምናቸው አይደለም ፣በተለይ ደግሞ ሙሁራን ፣ተማሪዎች ይህ ሳይማር አስተምሮ ሰው ያደረጋቸው ህዝብ በጅምላ ሲገደል  ፣ሲታሰር ፣ሲሰደድ ተንፍሽም  አይሉም ።
              የኢትዮጱያ ህዝቦች በአንዱ ክልል  ዜጎች ሲገደሉ  ሌላው  ክል እሰይ ወይ ዝም ብሎ የሩቅ ተመልከች መሆኑ፤  የኢትዮጱያ ገዥዎች ህዝብ ተፋቅሮ  ተስማምቶ ተሳስቦ ከተባበረ  ለስልጣናቸው አስጊ ስለሆነ  ሆን ብሎው ሆድና ጀርባ ሊሆን ስላደረጉ አይደናቀጥም አድማ አያነሳም ።ሌላ ቀርቶ እነዚህ ሰዎች ይቅርና የክልል ህዝቦች መጣላት ተውት የሚገርመው ነገር እኮ ባልና ሚስት ፣አባት ከልጅ ፣ጎረቤት ከጎረቤት በመጣላት  እስከ ቤሄር ከቢሄር  ሰብ  እንዲጣላ አድርገውታል  ስለዚህ የኢትዮጱያ ህዝቦች ወዳጃቸውና ጠላታቸው ማወቅ አለባቸው ።በህዝቦች መካከል ጠብ መኖር የለበትም ።
           በአዲሶቹ የለውጥ ሀይሎች በሚሉን  በዘመነ ጠ/አብይ አህመድ የሁለት አመት  የአገዛዝ ዘመናት  ስለ ሰብአዊና ዲሞክራሲ መብት ጥበቃ  ፣ስለ የሰው  ልጅ ክብር
ማፈን  በምን ደረጃ አለ ለሚለው ጥያቄ ? በበኩሌ በነዚህ መሪዎች የትግራይ መሪዎች  ጭምር የሁሉም ክልሎች መሪዎች አሮጌው ኢህአደግ በ27 አመት የጨረሰውና ያስጨረሰው ፣ ያፈነው ህዝባችን ሳዋዳድረው በሁሉም መልኩ ወደ እኩል መሆን ተጠጋግተዋል ።በመሆኑም ለእኔ የአንባገነኑ አፋኙ አሮጌው ኢህአደግ  እና የአሁኑ የለውጥ ሀይል ነኝ የሚል አዲሱ  አፋኙ ኢህአደግ ልዩነታቸው ፤ አሮጌው ኢህአደግ የኃላኃላ ፈረሰበት እንጅ በተራቀቀ አሰራር  ተንኮል ልማትም እያሳዬ ፣ስጋት በመፍጠር ጸጥታ በማስከበር አሮጌው ኢህአደግ ይሻላል ። ወጣቱ ኢህአደግ ግን መጀመሪያ ሲመጣ ተሰፋ ሰጭ ምልክት ሰጥቶን መላው ህዝባችን ብሩህ ተስፋ አግኝቶ ነበር ።ነገር ግን ረጅም ሳይጓዝ ሁሉም የለውጥ ሀይሎች   ራሳቸው እየጠሩ  ያሉ ድሮውም በገርነታችን ነው እንጅ በሙሉ ለማለት ይቻላል በዘመነ ኢህአደግ የወጣላቸው በዜጎች ክፉስራ ሲፈጽሙ የነበሩ እንዳው በህሪያቸው  ፣ተግባራቸው  ከነባሩ ኢህአደግ አይለዩም ። ትልቋ ነገር ደግሞ አሮጌ ኢህአደግ በሀገር ውስጥ ሞት ግጭት ፣የዜጎች ሞት መፈናቀል ሲያጋጥም እያጠፋ ያለው በራሱ ወንጀልም ቢሆን ሁኔታ ሲፈጠር በቅርበት ይከታተል ነበር ። ለተፈናቀሉም ፣ለሞቱትም ሳይውል ሳያድር ምግብ ፣መጠልያ 24 ሰአት ሳይሞላው እርዳታ ይሰጣል ለተራበው ህዝብ ገድለውት እያሉ በግዚያዊ እርዳታ ደለለው ጸጥ ያድርጉትና ፣ቆየት ብለው አነሳሽ ነበር ያሉትን  ተከታትለው ይዘው ያከስሙታል ።
            ወጣቱ ኢህአደግ ግን በሀገራችን አደጋ ሲፈጠር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች እርስ በእርሳቸው ተጫርሰው ተፈናቅለው ለበሸታ ለሞት ሲጋለጡ አንድ ጊዜ አረብ አገሮች ፣ወደ አፍሪካ ይሮጣሉ በሀገራችን በየቀኑ በአስርሽ የሚቆጠሩ ሲታሰሩ ካገር ፈርሰው በህር አቋርጠው ሲሰደዱ ፣ሲሸጡ   በቅርበት ሆኖው  እንደመምራት ፈንታ ከቢኔ ፣ፓርላማ ሳያውቃቸው ወደ  ውጭ አገር ጉብኝት ይሄዳል  ኃላ ጠፍቶ ሰንብቶ ሁሉሞ ነገር እንደማያውቁ ልክ እንደማኬቤሊ በሞፎከር ለግማሹ ባለስልጣናት ከሰልጣን አውርደው የራሳቸው ታማኝ ያስቀምጣሉ ።በአጠቃለይ ለኢትዮጱያ ህዝቦች ነባሩም ወጣቱ ኢህአደግ በስልት ይለያዩ አሉ እንጅ ሁሉም አፋኖች  ናቸው ።
            በመሆኑሞ  የጆርጅ ፍሎይድ   ድምጽ we can t breathe  ( መተንፈስ አልቻልንም) የሚል ሞፎከር ሞፎከራችን በማድረግ በመያዝ እርስ በእርሳችን መናናቅ መጣላት አቁመን መተንፈስ ላሳጡን ገዥዎች  እንታገላቸው እንደ የአለም ህዝቦች  በአንድ ጥቁር አፍሪካ አመሪካዊ ወግነው አለምን እንዳንቀጠቀጡት እኛም ለመተንፈስ እንታገል
 we can t breathe (መተነፈስ አልቻልንም !
          በተግራይ በአጠቃላይ በሰሜን  ኢ/ጱያ ያለው አፈና ፣በመንግስትና በግሊ ሚዲያዎች የጸጥታ ሀይሎች ገለልተኛ አለመሆን  ያለው አፈና በክፍል  3  ይቀጥላል ።
Filed in: Amharic