>

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጃዋር መሀመድን አስጠነቀቀ!!! (አዲስ ማለዳ)

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጃዋር መሀመድን አስጠነቀቀ!!!

.አዲስ ማለዳ

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጃዋር መሀመድ የክልሉን ሰላም እና መረጋጋት ለማደፍረስ በተለያዩ የማህበራዊ ድህረ-ገፆች ከሚለጥፋቸው የተዛቡ መረጃዎች እንዲታቀብ በማስጠንቀቅ እስከአሁንም በለቀቃቸው ከእውነታ የራቁ መረጃዎች በህግ የሚጠየቅ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ፖሊስ ኮሚሽኑ በትናንትናው እለት ሰኔ2/2012 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው
“የኦሮሚያ ፖሊስ ወንጀልን ከመከላከል፣ የክልልሉን ሰላም እና ፀጥታ ከማስከበር እንዲሁም ህግ እና ስርዓትን ከማስከበር የዘለለ ተግባር የለውም፡፡
በዚህም መሠረት ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ልዩ ኃይሉን በማደራጀት የሕዝቡን ሰላም እና የክልልሉን ፀጥታ በማስጠበቅ ላይ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን የክልልሉን ሰላም እና መረጋጋት የማይሹ አንዳንድ ግለሰቦች እና ቡድኖች የህዝብ መከታ የሆነውን ኃይል ሥም በማጠልሸት የፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
በዚህም መሰረት ከአሁን በኋላ ማንኛውም ግለሰብ ወይንም ቡድን የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን መልካም ስም እና ዝና ዝና እንዲያጎድፍ እንዲሁም ለፖለቲካ ትርፍ እንዲጠቀምበት አንፈቅድም፡፡
 ከዲንሾ ጋር ተያይዞ የሚሰራጨው ተራ አሉባልታም ሊገታ ይገባዋል፡፡ መነሻው የግለሰቦች ፀብ ሲሆን ጉዳዩ በህግ ተይዞ በመጣራት ላይ ይገኛል፡፡
ቢሆንም ግን እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አንዳንድ ግለሰቦች በተለይም ጃዋር መሀመድ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ የተዛባ መረጃን በመለጠፍ ብዙዎችን የማሳሳት ተግባሩን የቀጠለ ሲሆን በእንግሊዘኛ የለጠፈውን እንዲሁም ሌሎች ተጨባጭ መረጃዎችን በማያያዝ በህግ አግባብ የምንጠይቅ መሆኑን እንገልፃለን”
 ማለቱን ከፖሊስ ኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

https://www.facebook.com/AbbayMedia/videos/564211727628572/

Filed in: Amharic