>

የፖለቲካችን ቅርቃር...!!! (ሀብታሙ አያሌው)

የፖለቲካችን ቅርቃር…!!!

ሀብታሙ አያሌው

የለውጥ ጊዜ መጣ ብለን እጅ ነስተን የደገፍነው መንግስት በቅጡ ስድስት ወራት ሳይሻገር ሃዲዱን እየሳተ የተረኞች መነኸሪያ ሲሆን ባለንበት ፍሬን ይዘን ባቡሩ ሃዲድ እየሳተ ነው የሚል ሙግታችንን ቀጠልን።
በግልፅ እንደታየው የዳውድ ኢብሳ ኦነግ ፣ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ እና የለማ መገርሳ ኦዴፓ፣ የዶ/ር መረራ እና የበቀለ ገርባ ኦፌኮ፣ የነ ሌንጮ ለታ እና
የዲማ ነጋኦ ኦህዴግ፣ የከማል ገልቹ ኦነግ፣ የኃይሉ ጎንፋ ኦነግ፣ የጀዋር OMN ፣ የመከላከያው ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ተጠራርተው ተደምረው “ቶኩማ ኦሮሞ”
በሚል ስያሜ የጀመሩት ጉዞ “አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት” የሚል መገለጫ እስከማውጣት ሲደርስ እረ ተው መስመር ሳታችሁ አልን።
የኦሮሙማ አዝማቾቹ የፀጥታ ተቋማትን ቁልፍ የፖለቲካ ስልጣናትን የፋይናንስ ተቋማትን ያለ ይሉኝታ ተቆጣጠሩ። ብዙ ሳይዘገዩ ሃብታም ኦሮሞ የመፍጠር ፕሮጀክት ነድፈው ለማ ይመራው ጀመር። OMN ጡንቻው በባለ ሃብት ገንዘብ ዳጎሰ ኦነግ ሸኔ ወለጋ ነፃ ቀጠናው እንዲሆን ተተወ።
ኋላ ከማል ገልቹ ሲጣላ እንዳጋለጠው በተጠና ታክቲክ የዳውድ ኢብሳ ኦነግ ሸኔ 21 ባንክ ዘረፈ፣ የአማራ ተወላጆችን መንጥሮ ንብረታቸውን እያወደመ ከምዕራብ ወለጋ ከባሌ አሰደደ። ከሞት የተረፉት ንብረታቸው ወድሞ ጎጃምና ወሎ ደረሱ።
የኦሮሙማ ካርታ በየቢሯቸው በይፋ ተሰቀለ ከዚያም በላይ ተጉዘው ጀዋር ለካርታው መሰረት ድንጋይ አስቀመጠ። በአጭር ጊዜ የተስፋፋው የኦነግ ሸኔ
ሰራዊት ተልዕኮ ወስዶ:-
 አንዱ ክንፍ ወደ ሸዋ በመዝመት ደራን ፣ ከሚሴን፣ አጣዬን ለመውረር ተፋለመ። በኦሮሙማ አዝማቾች እቅድ ወሎን “ሰሜን ኦሮሚያ ብለው እንደሰየሙ የሚዘነጋ አይደለም።
ሁለተኛው ክንፍ ወደ ቤንሻንጉል ዘምቶ ከብሔረሰቦች ጀርባ በመቆም የአማራ ተወላጆችን ንብረት እያቃጠለ በቀስት እያስገደለ ዘር የማፅዳት እና ቤንሻንጉል የወለጋ ክፍል መማድረጉን እንቅስቃሴ ያጣድፍ ጀመር። በዚህ ሂደት በሁለት ዙር
የቤኒሻንጉል አመራሮችን መግደሉ ይታወሳል።
ሦስተኛው ክንፍ ወደ ደቡብ በማቅናት አንድ ሚሊዮን ገደማ የጌዲዮ ተወላጆችን አፈናቅሎ መሬታቸውን ወረረ ንብረታቸውን ወረሰ። አሁንም ድረስ አካባቢው የኦነግ ቀጠና ሆኖ መቀጠሉ በይፋ የሚታወቅ ነው።
አራተኛው ክንፍ ወደ ምስራቅ አቅንቶ አራት የሶማሌ ወረዳዎችን ለመጠቅለል ተደጋጋሚ ግጭቶች አካሄደ በለስ አልቀናውም። ቦታው አሁንም በመከላከያ የሚጠበቅ ቀጠና ነው።
አምስተኛው ክንፍ እዛው ምስራቅ ከአፋር ክልል ሦስት ወረዳዎችን ለመውረር ሦስት ጊዜ ደም አፋሳሽ ግጭት አድርጎ በሽማግሌዎች እንዲረግብ ከተደረገ በኋላ ለጊዜው የሁለቱም ክልል ልዩ ኃይል የሚጠባበቁበት ቀጠና ሆኗል።
ስድስተኛው ክንፍ በታከለ ኡማ የሚመራው የአዲስ አበባ ዴሞግራፊ ቀያሪ ክንፍ ነው። ይሄ ክንፍ በጣም ስልታዊ ሆኖ ህዝቡን በፕሮፓጋንዳ ወጥሮ ቅርስ እየናደ መሬት እየዘረፈ ጭምር የሚድያ ድጋፍ የሚያሰባስቡ ጭፍራዎች ጭምር ያደራጀ ቡድን ነው። ጠቅላዩ ከዚህ ቡድን ጋር ያላቸው ጉድኝት ቢቀርብም አላመነውም የሚያሰኝ ፈተና ውስጥ የሚከት ነው።
የጃዋር ክንፍ የሲዳማን መገንጠል እና ሐረርን የመጠቅለል ዘመቻ በስኬት አስፈፅሞ የድሬዳዋ ኦፕሬሽንን ማሳካት ግን ቀላል እንዳልሆነለት ይልቁንም ድሬዳዋ ላይ ያለው ግብግብ አሁንም ያልበረደ መሆኑንም በርካታ የሚዲያ አውታሮች እየዘገቡት እንደሆነ ልብ ይሏል።
ከዚህ ሁሉ በኋላም በቅርቡ ከወራት በፊት የኦሮሞ ድርጅቶች አንድነት “ጋዲሳ ኦሮሞ” ሲመሰረት በቶኩማ ኦሮሞ ስሌት ጀዋር አፈራራሚ ሆኖ ሌሎች
በፈራሚነት ያደረጉትን ትብብር አንዘነጋም። ይህ ሁሉ ሲሆን እልፍ ዘግናኝ ወንጀሎች ሲፈፀሙ ለጋራ አላማ “ለጋዲሳ ኦሮሞ” ሲባል ትንፋሽ ያሰማ የለም።
ሁሌም እንዳማረበት የሚኖር የለምና የአቶ ለማ ከልክ ያለፈ የጠቅላይነት ጉዞ ሽፍንፍናቸውን ገልጠው በይፋ “ኦሮሞ ፈርስት” እስከሚሉ አደረሳቸው። አራት ኪሎ ያለው ጠቅላይ ሚንስትር ፣ ወለጋ እና አዲስ አበባ ሆኖ የሚናበበው ኦነግ ፣
ለማ መገርሳ ከጀርባ የተሰለፈበት በጃዋር የሚመራው ክንፍ (የቄሮ መንግሥት)
የስልጣን ፍልሚያ ውስጥ ገቡ…ጋዲሳ ኦሮሞ ችግር ገጠመው።
በአብይ የሚመራው ኦዴፓ (ኦሮሞ ብልፅግና) መንግስትነቱን ለማስከበር ተነሳ፤ ከሃዲዱ የሳተውን ባቡር ወደ ሃዲዱ ለመመለስ ከረፈደ የጀመረው ትግል ከባድ ፍልሚያ ገጠመው። አሁን ነገሮች ግልጽ እየሆኑ መጡ በቶኩማ ኦሮሞ ስሌት
“ጋዲሳ ኦሮሞ” ብሎ ከሰበሰበው ኃይል ይልቅ ለሱ የቀረበው ትክክለኛ የሃይል ሚዛን ማስጠበቂያው በተሳሳተ ስሌት የፈረካከሰና ያዳከመው የአዴፓ (አማራ ብልፅግና) ፣ ተራማጅ የሆኑት የኦዴፓ (ኦሮሞ ብልግና) እና በተሳሳተ ስሌት ለመበታተን እንዲበቃ ያደረገው ደህዴን (ደቡብ ክልል ብልፅግና) ፤ አጋር
ክልሎች መሆናቸው እጅግ ዘግይቶ የተገለጠለት ይመስላል።
አሁን ጠቅላዩ እንደ ከዚህ ቀደሙ ወደ ኋላ የመመለሻና በሬ እያረዱ ታርቀናል የማለቱ ፖለቲካ አንዳች ትርፍ እንደሌለው የገባው ይመስላል። በየደረጃው በርከት ያሉ የእርምት እርምጃውች ከመውሰድ ተሻግሮ በቶኩማ ስሌት በጋዲሳ
ፖለቲካ ሲያስታምመው የከረመውን ቡድን ቆርጦ ለመጣል ፊት ለፊት የመጋፈጡን ምልክት እያሳየ ነው። አሁን ወደ ኋላ እስካልተመለሰ በጥንቃቄ
የተሞላ ድጋፍ የሚያስፈልግበት ሳት ሲል ተመለስ የሚባልበት ጊዜ ሊባል ይችላል።
ለማንኛውም ትላንት በቶኩማ ስም የሸፈኑትን የሸኔን ከፊል ገፅታ እንዲያሳይ ዛሬ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሚዲያ OBN እንዲህ አጋልጦ ማስጣት ጀምሯል።
እንደ ኦሮሞ ክልል መረጃ”
*********************
በኅዳር ወር 2012 ዓ.ም የተገደሉ
1. አቶ ረጋኔ ከበበ [በምዕራብ “ኦሮሚያ” የጀልዱ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ]
2. አቶ ተስፋዬ ገረመው [ በምዕራብ “ኦሮምያ” የጎጆ ከተማ የፖለቲካ ዘረፍ ኃላፊ]
3. ኮማንደር ጫላ ደጋጋ [ የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ኃላፊ]
4. አቶ ቶላ ገዳ [ “የኦሮሚያ” ክልል መስተዳደር የመንገዶች ባለስልጣን ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ]
5. አንድ ስሙን ለጊዜው ያላጣራሁት የምዕራብ ሸዋ ዞን ባለስልጣን፣
6. ሌላ ስሙን ያላረጋገግጥሁት የምዕራብ ሸዋ ዞን
ባለስልጣን፣ በጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም. የተገደለ
————————————————–
7. አቶ ገመቺስ ደስታ [የኢትዮ ቴሌኮም የምዕራብ ዞን ኃላፊ]
በመስከረም 2012 ዓ.ም የተገደልለ
———————————————
8. አቶ አበበ ተካልኝ [የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ ]
በግንቦት 2011 ዓ.ም.
—————————–
9. ስሙ ለጊዜው ይፋ ያልሆነና ከአርሲ ወደ ወለጋ ለወረዳ አስተዳድርነት ተመድቦ በመጓዝ ላይ ሳለ ኦነግ መንገድ ላይ አስቁሞ መጀመሪያ ምላሱን ቆረጡት፤ ከዚያ አይኑን አወጡት ከዚያ እጁን ቆረጡት፤ በመጨረሻ ሊያቃጥሉት ሲሉ ልዩ ኃይል ደረሶ ከመቃጠል አድኖት ሆስፒታል ውስጥ ይገኛል።
በሰኔ 2011 ዓ.ም በጥይት የተደበደበ
———————————————-
10. አቶ ታደለ ገመቹ [የደምቢዶሎ ከተማ ከንቲባ፤ በጥይት ተመትቶ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኝ]
በመጋቢት 2011 ዓ.ም. የተገደሉ፤
——————————————
11. በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ ሁምነ ዋቀዮ በተባለ ቀበሌ ሦስት ኢትዮጵያውያን፣ አንድ ጃፓናዊ እና አንድ የሕንድ ዜግነት ያላቸው ሰንራይዝ ለሚባል የማዕድን አውጪ ተቋም ይሰሩ የነበሩ ሰዎች ተገድለዋል
ታኅሳስ 2011 ዓ.ም
————————-
12. ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ውስጥ መነ ቤኛ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ላይ በጥይት ተመተው ተገድለዋል።
* * *
ድጋፋችን ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ኋላ እንዳይመለሱ ይሁን !
Filed in: Amharic