>

* ለመሆኑ ጌታቸው ረዳ፣ድጅታል ወያነ ንግግር የጤናማ ሰዎች አባባል ነው ?  (አሰግድ ገብረ ሥላሴ)

“በሽምግልና ሀገር አይመራም!”

ጌታቸው ረዳ
 

* ለመሆኑ ጌታቸው ረዳ፣ድጅታል ወያነ ንግግር የጤናማ ሰዎች አባባል ነው ? 

  አሰግድ ገብረ ሥላሴ

 ሰሙኑን ከአዲስ አበባ የአብይ አህመድ ቡዱን ከህዋሓት ቡዱን የሚያስታርቁ ሽማግሌዎች  መቐለ  ይመጣሉ የሚል ወሬ ከህዋሓት ቡዱን  ከተናፈሰ በኃላ ጌታቸው ረዳ በሚያስተባብራቸው ( አዲስ መመሪያ እያወጣ ) የሚያሽከረከራቸው ድጅታል ወያነ ፤ገና ለገና ሽማግሌዎች  ከመምጣታቸው በፊት ከአዲስ አበባ  ተባርረው  ተነድተው  መቐለ  የገባ የህዋሓት ቡዱን ተመልሶ አዲስ አበባ ለመግባት ፈልጎ በየት ልግባ እያለ ሲያስብ ፣ሲያሳላስል  ፣ሲጨነቅ ከርሞ ፤ ባለፈው ሳምንታት የህዋሓት ማ /ከሚቴ ፤ኃላም የክልል ምክርቤት ሰብሰቦ  አዲስ አበባ ተመልሶ ለመግባት ይሳካለት ዘንድ ታሳቢ በማድረግ ኢትዮጱያ ፈረሰች በመሆኑ ኢትዮ ጱያ የምትባል አገር ከፈረሰች ቀይ ባህህ  ሌሎች ባህሮች በሽብርተኝነት ቁጠጥር ከዋሉ የአለም ገበያ መተላለፍያ ከተያዘ የአለማችን የጸጥታ ድህንነት ፣ የኢኮኖሚ ቀውስ  ተፈጥሮ የአፍሪካ እና የመካከለኛ ምስራቅ አገሮች  ቀጠና አደጋ ላይ ስለሚወድቁ  ኢትዮጱያ አንድነታና ሉአላውነታ የተጠበቀች እንዳትሆን የአብይ አህመድ መንግስት እያፈረሳች ስለሆነ ኢትዮጱያ ለማዳን የአለም አቀፍ መንግስታት ህዝቦች እጃቸው ያስገቡ በማለት አለም አቀፋዊ ጥሪ በማቅረብ  እሪታ አሰምተው ነበር ።
           ለዚሁ አዋጅ ለማወጅ ያስገደዳቸው  በእውነት ስለ ኢትዮጱያ አንድነት ሉአላውነት ፣ስለ የአፍሪካ ቀጠና ድህንነት ለመረጋገጥ ተቆርቁረው እንቅልፍ አጥተው ሳይሆን ከላይ እንደጠቀስኩት አዲስ  አበባ ተመልሰው በ27 አመት የግፍ አገዛዝ እንደገዙን  ትግራይ ጠበበቻቸው መሰለኝ መደበቂያ ያለው አዲሳበባ ለሜድ ነው ።በመሆኑም ኢትዮጱያ አናድናት በማለት ፤ለአፍሪካ ህብረት ፣ ለአውሮፓ ህብረት ሌሎችም አህጉሮች ፤ ራሱን ለማዳነ ማኸል ያደረገ ሲለምን እንዳልሰነበተ ፤አሁን ተመልሶ ጌታቸው ረዳ በሽምግልና ሀገር አይመራም ማለቱ ያች ወደ ዜሮ ዲግሪ ወርዳ የነበረች የበታችነት ( ሞራል )መልሰው ከፍ ለማድረግ እና በህዝብ ታማኝነት ለማግኜ  ንችል ይሆን ከሚል እሳቤ ለመግደርደር ነው እንጅ አሁን እርቅ እንደማይቀበሉ  እነ ጌታቸው ሲጎሮኑ ውሼታቸው ነው ። በእኔ እምነት እነዚህ ሰዎች መግደርደሩ የተሸነፈ ሰው የሚያሳዬው  ባህሪ ነው እንጅ በውስጣቸው ደስ ብሎዋቸው ሊቀበሉት አይናቸው የማያሹ ናቸው ።
         የተከበርከ የትግራይ ህዝብ ሆይ ይህዝብ ድሮውን የኢትዮጱያ መፈጠሪያ ከድሮ ጀምሮ  የኢትየጱያ ህዝብም ሀገርም ባለቤት በመሆን ከሰው በላዎች የባእድ ወራሪዎች ጀምሮ ጠብቋት የመጣ ህዝብ እንደሆነ      መገንዘብ  አለብን ።
           የህዋሓት መሪዎች ፤ጥቂት ተጠቃሚ ካድሬዎቻቸው እንዲሁም ሌባ ሸሪኮቻቸው ከማኸል ሀገር ተገፍተው ከመጡ በኃላ ግን ምርጥ ልጆችህ ከፍለህላት ጠብቀሀት  የመጣህ ኢትዮጱያ ሀገራችን በመክዳት ትግራይ ለመገንጠል የሚያቀነቅኑ መሰሎቻቸው በመሰባሰብ በየአዳራሹ ትግራይ ለመገንጠል እየተንጫጩ ሲያስተጋቡ ይታያሉ ። በመሆኑም ራሳችን ዘብ ንቁም ።የሚጠቅምን በእኩልነት የተመሰረተች የኢትዮጱያ  አድነት  ብቻ ነው ።
  አስገደ ገብረስላሴ ፤
     መቐለ፤
Filed in: Amharic