>

ከ"ኦሮሚያ ቤተክህነት" በስተጀርባ ያሉ ረዣዥም እጆች...!!! (መምህር ታሪኩ አበራ)

ከ”ኦሮሚያ ቤተክህነት” በስተጀርባ ያሉ ረዣዥም እጆች…!!!

መምህር ታሪኩ አበራ

 

★ናዝሬት ገብርኤል ባስቸኳይ በግፍ የተወረሰበትን መሬት በሕግ ያስመልስ!! አሊያም ተመጣጣኝ የካሳ ክፍያ ይጠይቅ !! ★
★ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት  ከጠቅላይ ቤተክህነት ጋር በመናበብ  የቤተክርስቲያንን መብትና ክብር ጠንክሮ እንዲያስከብር እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነታችን አበክረን እናሳስባለን።★
ሁላችንም አንድ እውነት እንረዳ የአርሲ ሙስሊሞች ለኦሮሚያ ቤተክህነት ዋነኛ የገንዘብ ምንጭ ናቸው።  ጃዋር መሐመድ ከኋላ ሆኖ አይዟቹህ በርቱና ይህቺን ቤተክርስቲያን እናፈራርሳት እንደሚል የታወቀ ነው። በአሁን ሰዓት አብዛኛው ሙስሊሞች የኦሮሚያ ቤተክህነት እንዲቋቋም ከፍተኛ የገንዘብና የሞራል እገዛ እያደረጉ ይገኛሉ ።ዓላማቸው ቅድሥት ቤተክርስቲያንን ወደዋት ለኦሮሞ ክርስቲያኖች ተጨንቀው፣የወንጌል አገልግሎት ግድ ብሏቸው፣የኦሮምኛ ቅዳሴ ናፍቋቸው ሳይሆን ቅድሥት ቤተክርስቲያንን በመከፋፈል በኋላም የኦሮሞ ክርስቲያኖችን በግላጫ ለብቻቸው አግኝተው ለማጥቃት ነው።ይህ በምሥራቅ ሐረርጌ፣በዶዶላ፣በባሌና በሌሎች ቦታዎችም በተጨባጭ ታይቷል። አንዳንድ የኦሮሞ ክርስቲያኖች እስከአሁን አልነቁም በሬ ካራጁ ጋር ይወላል የሚባለውን ዓይነት ጉዞ በጭፍን እየተጓዙ ነው።
በነገራችን ላይ ዋናው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ Tv Eotc ዓመታዊ በጀቱ ወደ 60 ሚሊየን ደርሷል ይሄም ምዕመናንና ሀገረ ስብከቶች በተለያየ ጊዜ የሚረዱት ሳይቆጠር፤ ነገር ግን Tv ቻናሉ ኪራዩና የፕሮግራም ዝግጅቱ ዋጋ የትዬሌሌ ነውና በየጊዜው ከበጀቱ ውጪ እርዳታ ይጠየቅበታል።
በኦሮሚያ ቤተክህነት ስም ተገን አድርገው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ግን ይሄ ነው የሚባል አባልና ረዳት ከኦርቶዶክሱ ወገን የላቸውም ቢኖራቸው እንኳን በተአምር ከዋናው ቤ/ክ ወይም ከMK አይበልጥም ግን  Jtv ፣ Bisrat Tv ፣ Ltv የንግድ ቻናሎቹና በማስታወቂያ የሚንቀሳቀሱት ቻናሎች  የቻናል ኪራይና የሰራተኛ ደሞዝ መክፈል እያቃታቸው እየተዘጉ እያየን  እነ በላይ መኮንን ቢሮ ተከራይተው Tv ቻናል ሚሊየን ብሮችን በውጪ ምንዛሬ ኪራይ እየከፈሉ ፕሮግራም ጀምረዋል ፤ ይጀምሩ መልካም ነው። ለወገኖቼ በቋንቋቸው  የሚሰብኳቸው ከሆነ እሰየው ነው። ግን አላማው ያ አይደለም! እንተዋወቃለን። ሀሳቡ ይህችን ቤተክርስቲያን ከፋፍሎ ለመምታትና ለማጥፋት ነው። ይሄን ደግሞ ከማን ጋር እንደሚሰሩና ከህብረታቸው መረዳት ይቻላል። ግን ጠይቁ ይሄ ሁሉ ሚሊየን ብር ከየት መጣ?
አዎ! በዋናነት ሳውዲ አረቢያና በተለያዩ ዓለማት ያሉ የአርሲ የሀረርጌ ሙስሊሞች ባለሀብቶች ቢሮ ተከራይተው የቻናል ኪራይ ከፍለው ፣ ለነ  በላይ መኮንንና ለነ ሀይለሚካኤል ለመሳሰሉት ሰዎች የገንዘብ ምንጮች ናቸው።
….
ነገር ግን በዋናነት  የመንግስት መኪና ሹፌር በዃላም ባለ ውቃቢ አባቱ በገዙለት ትንሿ ቶዮታ መኪና ከሰል ይነግድ የነበረና አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉት ቢሊየነሮች መካከል ግንባር ቀደሙ የዋቄፈታ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዩ ተአምረኛው ባለሀብት ”ዲንቁ ደያስ” ከፊት ተሰላፊና የሀሳቡ ጠንሳሽ ሰው ነው። ሌላው ቀርቶ እኛ የምናውቃቸውን ሊቀጳጳስ ምን አርጎ እጁ ላይ አንዳስገባቸው ሳይታወቅ  እጁ ላይ ይዞ የሚያሾራቸው እንደፈለገ የሚያዛቸው ይሄው ሰው ነው። አቶ ዲንቁ ያለማቋረጥ የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ የነበረና ያለ ሰው ነው። ይህችን ቤ/ክ በብሄር ከፋፍሎ ለመምታት በዋናነት ከተሰለፉት መካከል አቶ ድንቁ ደያስ ከፊት ሆና ገንዘብ መልቀቅ ብቻ ሳይሆን ትእዛዝና አካሄድ ሁሉ እየሰጠ ነበር፤
ቤ/ክርስቲያኗን አውቃታለሁ የሚለው ይሄ ሰው ፥ አዳማ ላይ መሬቷን ለመንጠቅ የልማት ኮሚቴ ውስጥ የሆነ ሰሞን ከመግባት ባለፈ የዋቄፈታ እምነት በደባል የሚከተል ሰው ነው። በሌሎችም ቦታዎች እንዲሁ። በተለይ ግን አዳማ ከተማ ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ላይ ላግዛቹህ ብሎ የልማት ኮሚቴ ውስጥ ይገባል ፥ ቀጥሎም ይሄን ቦታ ከፋፍለን ለቤተክርስቲያኒቷ የንግድ ቦታ እናርገው ብሎ በምን ተአምር እንደሆነ ሳይታወቅ ተሯሩጦ ቦታውን በስሙ አዙሮ በጉልበት የቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ”ናፍያድ” ት/ቤ ገንብቶ መሬቱን ከቤተክርስቲያን ላይ ያለማንም ጠያቂነት ወስዶ ቁጭ ይላል። አገልጋዮች የብሄር አሰላለፉን አይተው ትተውት ነበር፤ ይባስ ብሎ የደብሩ ሱቅ ያለበትን ስፍራም ጠቅልሎ ወስዶ ደብሯን እንዲሁ አስቀርቷታል። አቤቱታ ቢያሰሙም ሁሉ በእጁ የሆነ ባለሀብት ነበረና ምንም መፍትሄ ሳይገኝ ቀረ። አሁን ሬፍትቫሊ ዩኒቨርሲቲ ያለበት ቦታ ሁሉ ቀድሞ የቤተክርስቲያኒቱ ነበር።
አቶ ዲንቁ በላይ መኮንን የመሰሉ ሰዎች ከዃላ በገነንዘብና በሆዳቸው ይዞ ቤ/ክ ሲያሳዝን ዓመት አላለፈውም። በተከበረበት በተፈራበት ሌላው ቀርቶ ባለስልጣናትን እያንጰረጰረ በሚገዛበት ከፍ ሲል state capture ለማድረግ ክንዱ ፈርጥሞ የመንግስትን እጅ አንድ ሰሞን መጠምዘዝ የቻለው ሰው በሚሊየኖች ፊት ነውሩ ተገልጦ ተዋርዷል መንግስት በ400ሚሊየን ብር ግብር ማጭበርበር ሀብቱን ሊወርሰው እያሟሟቀ ነው፣ ሰረቀን አጭበረበረን ገፋን ነጠቀን ያሉ የኦሮሞ ገበሬዎችና ሌሎች አብረውት ይሰሩ የነበሩ ሰዎች ሊፋረዱ ፍርድቤት ቆመዋል፤ ቤተክርስቲያን ላይ የለኮሰው እሳት እገዛ የራሱ ቤት ገብቶ ይለበልበው ጀምሯል። ሌሎቻችሁም እንዲሁ ቤ/ክ ላይ በፈጸማችሁት ገና ዋጋ ትከፍሉበታላችሁ። እሳቱ በየቤታችሁ በኑራቹህ ላይ ይነዳል።
እባካችሁ ለሌሎችም ሼር አድርጉት
ይህንን መልዕክት ለምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤትና ለናዝሬት ቅዱስ ገብርኤል ሰበካ ጉባዔ ጽ/ቤት አድርሱት።
Filed in: Amharic