>

ሓጫሉ - የገደሉህ ሰዎች አንተን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያንም አምርረው የሚጠሉ ናቸው...!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ሓጫሉ – የገደሉህ ሰዎች አንተን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያንም አምርረው የሚጠሉ ናቸው…!!!

ያሬድ ሀይለማርያም

በእኩለ ለሊት የኦሮምኛ ሙዚቃ ዘፋኝ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት ተሰማ… ጉዳዩን ከሞት በላይ የሚያደርገው…
1..ሀጫሉ በጥይት ተደብድቦ መሞቱ
2 በበርካታ ኦሮሞዎች ዘንድ እንደ ኮከብ ድምጻዊ የሚታይ በመሆኑ
3.አወዛጋቢ እና አቧራ ያስነሳ ቃለ መጠይቅ በሰጠ በጥቂት ቀናት ውስጥ መገደሉ.
4 .በጣም ወጣት መሆኑ
5.ለውጡ ተግ ብሎ በተጋጋመበት ወቅት መድረክ ላይ በድፍረት ለውጡን የሚያጋግል ሙዚቃ በማቀንቀኑ
እና በሌሎችም ምክንያት ሞቱ ብዙ የሚያባብልና ብዙ መዘዝን ይዞ ሳይመጣ አይቀርም።
ልክ እንደ ስመኘው መጨረሻ
ልክ እንደ ጀነራል ሰአረ መጨረሻ
ልክ እንደ አምባቸው መጨረሻ
ልክ እንደ አሳምነው ፍጻሜ
ጉዳዩ ቀን እየጠበቀ የሚፈነዳ time bomb የሚቀብር ግድያ ይመስለኛል።
አሁን የፖለቲካውን ንፊፊት ይበልጥ የሚወጥረው ገመድን የሚጎትት አንድ ነገር ሆነ።የታዋቂ ሰዎች ግድያ።
እውነተኛ ገዳዮቹን ለፍርድ አቅርቦ ጉዳዩን በግዜ ካልቋጩ በቀር የበቀል እርምጃው አስፈሪ ነው።
..
የሚነቅፉትም የሚደግፉትም በሁለት ነገር ይስማማሉ።
..-የለውጡን ፍም ካጋጋሉት ግንባር ቀደም አርቲስቶች አንዱ መሆኑን የዚህን ታዳጊ አርቲስት ህይወት የቀጠፋ ሰዎች ተራ ታጣቂዎች ብቻ ሊሆኑ አይችሉም። ይች አገር በብዙ አደጋዎች በተከበበችበት በዚህ ወቅት ይህን አይነት አሰቃቂ ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎች ግባቸው ከአጫሉ ህይወት ማለፍ ጀርባ በሚፈጠረው ትርምስ ላይ እንደሚሆን ምንም አያጠራጥርም።
አርቲስቱ አነጋጋሪ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በነጻነት የሚሰጣቸው አስተያየቶችን በማስታከክ በሕዝብ መካከል ቅራኔዎችን ለመፍጠር፣ አገሪቱን ወደ ትርምስ ለመክተት፣ በመንግስት ላይ ጫና ለመፍጠር እና አገሪቱ ወደ ሌላ ዙር የፖለቲካ ቀውስ እንድትገበ ቀዳዳ ይፈልጉ የነበሩ ኃይሎች ያቀነባበሩት ይመስላል። ሃዘናችን ጥልቅ ነው።  በሓጫሉ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በአገር ላይ እንደተፈጸመ ጥቃት በመቁጠር ጉዳዩን በጥንቃቄ መከታተል እና መመርመር ይገባል።
መንግስት ወንጀለኞቹን በቶሎ በቁጥጥር ስር አውሎ ለፍርድ እንደሚያቀርብ እና እውነታውንም ለሕዝብ እንዲሚያሳውቅ ተስፋ አደርጋለሁ።
ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ፣ ለዘመዶቹ እና ለመላ አድናቂዎቹ ሁሉ መጽናናቱን እመኛለሁ።
Filed in: Amharic