>

የአነግ መስራቾቹ ሲሻላቸው ጀማሪዎቹ አገረሸባቸው (ድልባቶ ደጎዬ)

የአነግ መስራቾቹ ሲሻላቸው ጀማሪዎቹ አገረሸባቸው 

ድልባቶ ደጎዬ

 

* የኢትዮጵያ አምላክ የተዘባበቱባትን ጡት ነካሾች ሁሉ እንዲህ የማርያምን ብቅል እንደበላች ፍየል ያስለፈልፋል፡፡ኢትዮጵያዊነት ስትሸሸው ጠፍንጎ የሚስብህ መግነጢሳዊ ሀይል ነው፤ለ50አመታት ለኦሮሞ ነጻነት የታገለው ሌንጮ ለታ ኢትዮጵያዊ እንሁን ሲል ተማጸነ…!!!”
“የኦሮሞ ብሔርተኛ ወንድሞቼ ግራ ይገቡኛል። ወያኔ ሲገዛ ጩኸት፣ ኦሮሞም ሲገዛ መከራ። ጭራሽ ወያኔን መናፈቅ።”
በወጣትነቴ ነፃ ኦሮሚያ ብዬ ትግል ገባሁ። ዕድሜዬም ሲገፋ፣ ፈራሁ መሰለኝ ሀሳቤን ተውኩት። ከሌላው ብሔር የተዋለደ፣ ድብልቅ ኦሮሞን ከማን እለያለሁ? በዚህ እምነቴ መቼም አልፀፀትም።
•ገፅ1__ከሰሞኑ_በድንቁ_ደያስ_ዶክመንተሪ_ተሰራ
መሽቶ ሲነጋ ሀጫሉ በOMN ተጠየቀ። ስለ ሚኒሊክና ፈረስ ታሪክም አወራ። OMN ለምን ሀጫሉን ጠየቀ? የድንቁን ዘገባ አልወደደውም።
አጀንዳ ለማስቀየርና ሌላ የሁከት ሰፈር ለመፍጠር ነበር የሀጫሉ ኢንተርቪው። ድንቁ ካጠፋ ለምን አይጠየቅም? ከድንቁ የተራጩት ውስኪ እንጂ የተፈናቀሉት ገበሬዎች ቁብ አይሰጣቸውም ጠያቂዎቹ።
•ገፅ2__ሚኒሊክ_ለምን_ተጠላ?!
ሚኒሊክ ከተጠላ ኦሮሞም ይጠየቃል። ጎበና የጦር አዛዡ ኦሮሞ አይደለ? ከሚኒሊክ ሚኒስትሮች አራት ኦሮሞ፣ ሁለት ከጉራጌ፣ ሶስት ከደቡብ፣ ሁለት ከአማራ መሆናቸውን ማንም አያነሳም።
•ገፅ3__የሚኒሊክ_ትረካ_የወያኔ_ጥበብ_ናት
 ወያኔ ለኦሮሞ አስቦ አይደለም፣ የሸዋው ንጉስ ሚኒሊክ ከአፄ ዮሐንስ ሊዋጉ ነበር። በድብቅ ቄስ ላኩ፣ ሚኒሊክን ተውና ሱዳንን ተዋጉ እንዲሉ። ዮሐንስ በሱዳን ተገደሉ። ሚኒሊክ ንጉሰ ነገስት ሆኑ።
ወያኔ ይህችን ቂም ለመበቀል ነው፣ የአማራ መደብ፣ የቡርቃ ዝምታ፣ የጡት ቆረጣ። የአኖሌ ሀውልት ለኦሮሞ በማሰብ ነው?
ሁሉም ገድለዋል። ቴድሮስም በሸዋ እጅ ቆርጠዋል፣ ዮሐንስም ወሎን ጨፍጭፈዋል። ወያኔ ጨፍጫፊውን መንግስቱ አይደል የተዋጋው? መለስስ አልገደለም? ለምን ለነዚህ ሀውልት አይሰራም? ሂትለር የአይሁድን ዘር ፈጀ። የታል የአይሁድ ሀውልት? የታል የናዚ ገዢ መደብ ታሪክ? የታል የኦሽዊትዝ ዝምታ? ታሪክን ትተው፣ በይቅርታ ሰርቶ መለወጥ እንጂ የማያልቅ ወሬ አልነበረም የአይሁድ ቀጣይ ስራ።
ገፅ4_የኦሮሞ_ብሔርተኛ_ወንድሞቼ_ግራ_ይገቡኛል
ወያኔ ሲገዛ ጩኸት፣ ኦሮሞም ሲገዛ መከራ። ጭራሽ ወያኔን መናፈቅ። አማራ ለለውጡ ዋጋ ከፍሏል። ድምፁን ለኦሮሞ ሰጥቷል፣ መሪዎቹን በጥይት አጥቷል፣ በዚህም የወያኔን ቂም አትርፎ ሰላሙን አጥቷል። ይህም ተዘንግቷል። ኦሮሞ ስልጣን ስለያዘ ምን ይሁን? አማራ ይጥፋ? ብድር ይመለስ? ጋሞ ይገደል? ደቡብ ይሰደድ? ይህ ከሆነማ ለህዝቡ ወያኔ ይሻለዋል። ለምን ኦሮሞ ገዝቶት ስቃዩን ያያል?
ከአማራ አትግዙ፣ አትጋቡ፣ በኦሮምኛ ብቻ አውሩ ወዘተ ወዘተ። ይህን የሚያዝ ኦሮሞ ብሔርተኛ ማንን ሊመራ?
•ገፅ5_አብይ_የዘመናት_የጎሳ_ሴራን የክፋት ድርሰት ዘግቶ አስቀመጠ። 
የአንድነት ህብረትን መረጠ። ዘርን ትቶ ሀገር አስቀደመ። እናም የኦሮሞ ደም የሌለው ተባለ። ኦሮሞው አብይ ሲገዛ ሶማሌ አጋር አይባልም። ጋምቤላም ሚኒስትር ይሆናል። ሙስጠፌስ የኦሮሚያ ፕሬዚደንት፣ ሽመልስ የጉሙዝ አስተዳዳሪ ቢሆን ምን ችግር አለው? ሁሉም የሁላችን አገር አይደለ? በወያኔ የሰፈር አጥር ታጥረን ስንት ዘመን ልንኖር ነበር። አንድነት ለኛ ይበጀናል።
የናዚዎቹ ጀርመኖች አንድ ላይ ተቀላቅለው የለ? ምዕራባውያን በአውሮፓ ህብረት በአንድ ፓስፖርትና ገንዘብ ሲጠቀሙ፣ እኛ መታወቅያችን ላይ ብሔር እንፅፋለን፣ መርጠን ዘር የወሰድን ይመስል። አብይ የሌባን ቡድን፣ የሴራን ክለብ፣ የከፋፍሎ ገዢን ጋንታ፣ የሀገር አፍራሽን ደባ አፍርሶ ስጋት የሌለባትን የእኩልነት ሀገር ለመፍጠር ይጥራል፣ ሌላው ሚኒሊክ ሚኒሊክ ይላል።
ሸኔ በወለጋ ሰውን ሲያቃጥል ዝም ይላል፣ ወለጋ ኔት ሲጠፋ ይዘፍናል። ከሰው ነፍስ ይልቅ ኔት ወርክ ሲጠፋ ያመዋል። ለብሔርተኞ እንዲህ መክራለሁ፣ ልጅ ሳለሁ እንደልጅ አስብ ነበር፤ ዕድሜ ገፋና ሩቁን አያለሁ። ንፁህ ሀገር ለልጆቻችን እንፍጠር፣ በዘር አንከፋፈል፣ በኦሮሞ ሀገር ተረፈ መባሉ ራሱ ጥሩ ስም ነው። የሚያልፍ ቀን የማያልፍ ስም ጥሎ ያልፋል። ለአብይ ግዜ ስጡት።
.
እኔም በተራዬ ሁሉም እየተነሳ ምኒልክን ካልሰደባችሁ ገነት አትገቡም እንደተባሉ ሁሉ በሌለና ሰው በቀደደላችሁ ቦይ ከመፍሰስ ተቆጥባችሁ የታላላቅ አባቶቻችሁን ምክር ስሙ ለማለት እፈልጋለሁ። ኦቦ ሌንጮ በመጨረሻ ከእውነት ጋር ስለኖሩ ሊከበሩ ይገባልና እውነት ዋጋዎን ትክፈልዎት።”
Filed in: Amharic