>

ግብጽን በማኪያቬሊስታዊ እይታ...!!! (መስቀሉ አየለ)

ግብጽን በማኪያቬሊስታዊ እይታ…!!!

መስቀሉ አየለ

ዘላለም ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ሆነህ  እየደማህ መኖር ከሰለቸህ መፍትሔው የማኪያቬሊን ቀመር መሬት ላይ ማውረድ ነው። ከቅኝ ግዛት ነጻ ከሆነችበት ማግስት ጀምሮ  በምስራቁ የአገራችን ክፍል በኩል ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ ስታደማ የነበረችውን ሶማሊያ ከማፕ ላይ ሰርዞ ድራሿን ያጠፋት መንግስቱ ኃይለማርያም ሲሆን “ማኪያቬሊ” የተባለ መፍትሔ ስራይ ጽፈው የሰጡት ደግሞ ፕሮፌሰር እሸቱ ጮሌ እና ጥቂት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ነበሩ። በሶማሊያ ላይ የሆነውን የሚያውቀውና የሱማሌ ዜግነት ተሰጥቶት በሱማሌ ፓስፖርት እየዞረ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ሁሉ ኢትዮጵያ የምትፈርስበትን ሴራ ሲሸርብ የኖረው መለስ ዜናዊ ግን ልክ እግሩ አራት ኪሎን በረገጠ ማግስት የውጭ ጋዜጠኞችን ሰብስቦ እንዲህ አለ። “ለሶማሊያ መጥፋት ተጠያቂዋ ኢትይዮጵያ ናት።”
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግድቡ ለኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ሊሆን ይገባል። ባለፉት አንድ ሽህ አመታት ሰላም በማጣት የከፈልናቸው ዋጋዎች አብዛሃኛዎቹ ምንጫቸው ግብጽ ነበር ። በመቀጠል በ1960ዎቹ የተቀጣጠለውን የፓን አረቢያኒዝም ንቅናቄ በማስታከክ ምንም አይነት የአረብ ዝርያ የሌላቸውን ሶማሊያ፣ ጅቡቲንና ሱዳን እስላም ስለሆኑ ብቻ እንደ ወደ አረብ ሊግ እንዲገቡ የተደረገበት ሴራ ይሄንኑ ኢትዮጵያን ከቦ የማዳከም የግብጽ የረጅም ግዜ እስትራቴጅ አካል ነበር።
ዛሬ ደግሞ ግብጽ በጸረ ኢትዮጵያዊነት የሰከሩ የትግራይ ብሄርተኝነት አቀንቃኞችና ባለፈው ሃያ ስምንት አመት በወያኔ መልካም ፈቃድ የተፈለፈሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የውሃቢዝም፣ የእስላሚክ ብራዘርሁድ አክራሪዎችን፣ ሊቢያ ውስጥ ተወልዶ የበሰበሰው የሙሃመድ ጋዳፊ “ሰርድ ዩኒቨርሳል ቲዌሪ” አቀንቃኞች በልዩ ልዩ ስኮላር ሽፕ ሽፋን ከግብጽ እስከ አፍጋኒስታን ድረስ በተዘረጉ የአካሪዎች መፈልፈያ ካምፖች እየተላኩ ራዲካላይዝድ ሆነው  የተመለሱትንና “ድምጻችን ይሰማ” በሚል ጭምብል የተሸፈኑትን ሚሊዮኖችን ተስፋ በማድረጓ ጋዜጦቿ “ኢትዮጵያ ከሰሞኑ አመጽ አገግማ እንደ አገር አትቀጥልም” እያሉ የሚደነፉት በእነ አህመዲን ጀበል ፊንጢጣ ውስጥ ያጠመዱትን የቦንብ መጠን ስለሚያውቁት ነው።
ስለዚህ ዛሬ ኢትዮጵያን እመራለሁ የሚለው ሃይል ማወቅ ያለበት አንድ እውነት  ኢትዮጵያ በአካባቢዊ ጅኦፖለቲካ ላይ የነበራት የሃይል ሚዛን ቀይ ባህርን በማጣቷ ብቻ ክፉኛ መዳከሙንና ዛሬ እጇ ላይ የቀራት ካርታ የአባይ ካርድ መሆኑን፣ ስለዚህም ከላይ በዘረዘርናቸው ምክንያቶች የተነሳ አባይን ከሃይል ምንጭነቱ በላይ ጅኦፖለቲካዊ ጥቅሙ የሚያመዝን በመሆኑ እዛ ላይ አበክሮ መስራት እነደሚገባው ማወቅ አለበት። ይህ ማለት በተዘዋዋሪ መንገድ አባይን በመጠቀም ግብጽን አንቆ መግደል የሚችለበትን ግራንድ ስትራቴጅ ለመተግበር እንደ መንግስቱ ዘመን ሶማሊያ የማኪያቬሊን ቀመር የሚግተው ሰው ያስፈልገዋል። ቁርጠኝነት ካለ አባይና ማኪያቬሊ የትላይ እንደሚገናኙ መስመሩን መጠቆም እንችላለን። በዚህ በኩል ዶር ዳኛቸው አሰፋ ባለፈው ሰሞን ስለማኪያቬሊ ትንሽ መንገድ ሊያሳየው ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ሰውየው ግን “መደመር” በሚል የተንሳፈፈ ፋንታሲ ውስጥ ገብቶ ጆሮውን ለመስጠት አልፈቀደም። አሁንም አልረፈደም።ደግሞም  ፓስተርነቱን ቀንስና እንደ መንግስቱ ኃይለማርያም ወታደር ሁን።
Filed in: Amharic