>
5:29 pm - Friday October 10, 0966

ህግ ባለበት በጉልበት በሃይል መጠቀም  በጥፋት ላይ ጥፋት በውድመት ላይ ውድመት በበደል ላይ በደል ነው!!!" (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ)

ህግ ባለበት በጉልበት በሃይል መጠቀም  በጥፋት ላይ ጥፋት በውድመት ላይ ውድመት በበደል ላይ በደል ነው!!!”

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

የኢትዮጵያ ነጻ አውጭ ነን ያሉት የሓጫሉን ግድያ ተከትሎ በንጹሃን ላይ ብሄር ላይ ያነጣጠረ ግድያ ሲፈጸም ድምጻቸው በውጭም ሆነ በውስጥ አይሰማም። ዜጎች አርስቲስቱን በዐይናቸው የማያውቁት ሁሉ ንብረታቸው እንዲወድም፣አካላቸው እንዲጎድል፣ህይወታቸው በመንጋ እንዲጠፋ ሆኖ ሬሳቸው በጠላት አገር እንኳን በማይሞከር ድፍረት መሬት ለመሬት ሲጎተት ፣ይሄ ሁሉ ዘረኛ በለው በለው እያለ የጦርነት አዋጅ ሲያውጅ ይህ ነገር አያዋጣም፣ህዝብን እርስ በእርስ በማጋደል የሚመጣው ትርፍ ምንድነው ? ያሉ በጣም ጥቂቶች ናቸው ። ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ እንሟገታለን ሲሉ የነበረው ሲሉን የኖሩ ቁጭ በሉዎች የብሄር ካርዳቸው ውስጥ ተደብቀው እንደተናገርነው ውስጣቸው ሲገለጥ በዘረኝነት እና የዘር ጥላቻ ያበዱ መሆናቸውን ሰሞኑን በተግባር  አስመስክረዋል።
አቡነ ማቲያስ ግን ይጠይቃሉ ምንድነው ይሄ ሁሉ ግፍ? 
“ለጠፋው ሕይወት በግፍ ለሞተው ወንድማችን በህግ አግባብ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል እንጂ የበደለውንም ያልበደለውንም አንድ ላይ መደፈጠጥ ምን ይባላል። እስቲ ያልበደሉትን ሰዎች ሕይወታቸውን ማጥፋት እና ንብረታቸውን ማውደም ምን ማለት ነው ? ጥቅሙ ምንድነው? ትርጉሙስ ምንድነው ነው ? በጉልበት በሃይል መጠቀም እኮ በጥፋት ላይ ጥፋት በውድመት ላይ ውድመት በበደል ላይ በደል ነው::”
Filed in: Amharic