>

ኢትዮጵያ ውስጥ  ኦሮሞ ባልሆኑ ዜጎች ላይ እየተካሄደ ያለው የዘር ፍጅት የኦሮሞ ብሔርተኛነት ውጤት ነው!  (አቻምየለህ ታምሩ)

ኢትዮጵያ ውስጥ  ኦሮሞ ባልሆኑ ዜጎች ላይ እየተካሄደ ያለው የዘር ፍጅት የኦሮሞ ብሔርተኛነት ውጤት ነው! 

አቻምየለህ ታምሩ

ኦሮምያ በሚባለው ክልል ኦሮሞ ባልሆኑ በተለይም የአማራና ጉራጌ ተወላጅነት ባላባቸው ኢትዮጵያውያን ላይ እየተካሄደ ያለው የዘር  ፍጅት በሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ምክንያት የተፈጠረ ክስተት አይደለም። የሐጫሉ ግድያ በአማራና ጉራጌዎች ላይ ለሚካሄደው የዘር ፍጅት ሰበብ እንጂ ምክንያት አይደለም። ቄሮ የሚባለው ኦሮሞ ያልሆኑ ነገዶችን ለማጥቃት የሰለጠኑ ወጣቶች ድርጅት በአማራና ጉራጌዎች ላይ እያካሄደው ያለው የዘር ፍጅት መንስዔው ዘር ማጥፋትን እንደ ዋና ዓላማ የያዘው የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካ ነው።
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደጻፍነው የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካ ስለ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሚደረግ ትግል ሳይሆን  ኦሮሞ ካልሆነ ሰው የጸዳ አገር ለመመስረት «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» በሚል መርኅ ላይ የተመሰረተ የዘር ማጥፋት ፖለቲካ ነው። «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚለው የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካ ትርጉም «ኦሮምኛ የሚናገር ወገናችን ነው ይገብር፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ”» እንደ ማለት ነው። ኦሮሞ ያልሆኑ ነገዶችን ለማጥቃት የሰለጠኑ ወጣቶች  ድርጅት የሆነው ቄሮ ዛሬ እያስፈጸመው ያለውን ይህንን የኦሮሙማ ፖለቲካ ነው።
የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካ  ስለእኩልነትና ዲሞክራሲ ቢሆን ኖሮ ክልላችን በሚሉት ውስጥ የሚኖረው ሰላማዊ ሕዝብ ሁሉ በሕይወቱ ወይም በንብረቱ ላይ የኃይል ጥቃቶች እንዳይፈጸሙበት ከማንኛውም ጥቃት የመጠበቅ መብቱን ያስከብሩለት ነበር። ሆኖም ግን ትግላቸው ኦሮሞ ካልሆነ ሰው የጸዳ አገር መመስረት ስለሆነ ኦሮሞ ባልሆነው ሰላማዊ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋትን እንደ ዓላማ ይዘው የዘር ፍጅት እያደረጉ ይገኛሉ። ለዚህም ነው አዲስ አበባ ላይ ለተገደለ ሰው ምንም በማያውቀውና ዝዋይ፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ፣ ሐረር፣ ወዘተ በሚኖረው ንጽሐን ላይ በማንነታቸው ላይ ያነጣጠረ የዘር ፍጅት ሲያካሂዱ የሚውሉት።
ባጭሩ የሐጫሉ ግድያ የዘር ማጥፋትን እንዳላማ ለያዘው የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካ  ባለፈው ጥቅምት ወር ኦሮሞ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ እንደተካሄደው  አይነት የዘር ፍጅት  እንዲካሄድ  ሰበብ ሆነ እንጂ  ምክንያት አይደለም። የዘር ፍጅቱን  በዋናነት እየመሩት ያሉት ደግሞ  ኦሮምያ የሚባለው ክልል ልዩ ኃይል አባላት ናቸው። ኦሮምያ የሚባለው ክልል ልዩ ኃይል ዩኒፎርም የለበሰ ቄሮ ነው።  በ32 ዙር የሰለጠነው  ቁጥሩ ከአምስት መቶ ሺህ  በላይ የሚሆነው  ልዩ ኃይል ለተመሳሳይ አላማ የሰለጠነ ነው። የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ኦሮምያ በሚባለው ክልል  ኦሮሞ ባልሆኑ ነገዶች ላይ የዘር ፍጅት ያካሄዱ ቄሮዎችን በልዩ ኃይል እያስጠበቀ  ሕዝቡ ከቄሮ ፍጅት ራሱን እንዲከላከል ቀሰቀሱ የተባሉትን የአዲስ አበባ ወጣቶች እያደነ  በማሰር ላይ ያለው የዘር ፍጅቱ እየተካሄደ ያለው በአፓርታይድ አገዛዙ መዋቅር ለመሆኑ ሌላ ማሳያ ነው።
አሁን ላይ የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ እየተጨነቃ ያለው ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ ራሳቸውን ቄሮ ነን የሚሉ ኃይሎች ኦሮሞ ባልሆኑ ነገዶች ላይ  እያካሄዱት  ስላለው የዘር ፍጅት ሳይሆን አዲስ አበባ ውስጥ የከፋ የዘር ፍጅት አለመካሄዱ ይመስላል።  ለዚህም ነው  አዲስ አበባ ውስጥ የተሰማራው ኦሮምያ ክልል የሚባለው ልዩ ኃይል ራሳቸውን የሚከላከሉ ሰዎችን የሚከላከሉበትን መሳሪያ እየቀማ ለቄሮዎች አሳልፎ እየሰጠ ያለው።
አሁን እንደገባኝ በፋሽስት ወያኔ ዘመን ያ ሁሉ ተቃውሞ ይካሄድ በነበረበት ወቅት ኦሮሞ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ ካሁኑ አኳያ ሲታይ  የከፋ የዘር ፍጅት ያልተካሄደው በኦሮሞ ብሔርተኞች ዘንድ  አሁን እንደሚያደርጉት የዘር ፍጅት  የማድረግ ፍላጎት ስላልነበረ ሳይሆን ወያኔዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ በዘረፋ ያካባቱትን ሀብት ለማስጠበቅ ያሰማሩት ሠራዊት የተሻለ ጥበቃ ያደርጉ ስለነበር ነው። ኦሮምያ በሚባለው ልዩ ኃይል ማደፋፈሪያና ድጋፍ  ኦሮሞ ያልሆኑ ነገዶችን ለማጥቃት የሰለጠኑ ወጣቶች ድርጅት የሆነው ቄሮ ያለ ተከላካይ የዘር ፍጅትና ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎችን ንብረት በእሳት እያጋየ ያለው  ወያኔዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ በዘረፋ ያካባቱትን ሀብት ለማስጠበቅ ያሰማሩትን ሠራዊት ያህል እንኳን  ኦሮሞ ላልሆኑ ዜጎች ጥበቃ የሚያደርግ መንግሥታዊ ኃይል ባለመኖሩ ነው።
Filed in: Amharic