>

አዲስ አበባ ላይ የሆነው እንዲህ ነው...!?! (ሰላም ሞላ)

አዲስ አበባ ላይ የሆነው እንዲህ ነው…!?!

ሰላም ሞላ

ሀጫሉ የተገደለ እለት በርካታ ቄሮዎች ቆንጨራ ገጀራ እና ብረት ይዘው ወደ አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ። ግርር ብለው ያገኙትን መሰባበር ጀመሩ። ጥቃቱን የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች አልተቆጣጠሩትም። 7 ቤተክርስቲያን  ለማቃጠል እና ለማውደም ሙከራ አደረጉ። ከቤተክርስትያን በተደወለው ደወል የአካባቢው ህዝብ ወደቤተክርስቲያኑ ተመመ። ቄሮን አባረረ። ሌላውም በየሰፈሩ ራሱን እያደራጀ አካባቢውን ከውድመት ጠበቀ።
አንድ ሰውየ ቄሮ ግርር ብሎ ሊያጠቃው ሲመጣ ጥይት ወደ ሰማይ ተኩሶ በታተናቸው። ወዲያው የመንግስት ታጣቂዎች ደርሰው ሽጉጡን ቀምተው ልጁን ለመንጋው ትተውት ሄዱ። መንጋውም አንበሳ ገድሎ እንደሚፎክር ጀግና ገድለውት ሬሳውን በአዲስ አበባ ጎዳና ጎተቱት። ህዝቡ ያንን አየ። ፖሊስ እንደማያስጥለው ሲያውቅ ራሱን አደራጀ።
ይሄ ፍጹም የተቀናጀ ጥቃትን መመከት እነ ታከለ እና አብይን አላስደሰተም።  አዲስ አበባዎችን ለማሸማቀቅ ጅምላ እስር ውስጥ ገቡ። እነ እስክንድርና ስንታየሁን አሰሩ። ራሳቸውን እና ህዝቡን የተከላከሉት አመጽ ቀስቃሽ ተብለው የሀሰት ፋይል ተመዘዘባቸው። እቅዳቸው አንገት አስደፍቶ ቄሮን እየላኩ ህዝቡን እያሸበሩ ስልጣን ላይ ለመወዘፍ ነው ። የአዲስ አበባ ወጣት ተደራጅቶ መከተ እና እንደጥፋተኛ ተቆጠረ። ማንን እንደሚያታልሉ አይታወቅም። እስክንድር ጠላታቸው የሆነው ህዝቡን በማንቃቱ ነው። ቄሮ የተባለ መንጋ አዲስ አበባን እንደሻሸመኔ ሊያደርጋት ሲል ከተማውን የጠበቀው ወጣት ጥፋተኛ ተብሎ ተወነጀለ።
Filed in: Amharic