
ለወገኖቼ!

ጌታቸው አበራ
…ነገደ ኩሽ ወ ሴም፣ ..’ኦሞቲክ፣ ናይሎቲክ’ …
የእግዚአብሔር ፍጡራን፣
የሰው ልጅ ዘር ግኝት ጥቁር ኢትዮጵያውያን..፤
አያት ቅድመ-አያቶች፣.. ጥንተ-ኢትዮጵያ ልጆች..
በገነቧት ሀገር፣ ሜዳ..ሸንተረሩ፣
ከሰሜን .. እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ ወ ምስራቅ.. በሰላም ስትኖሩ፤
ያለ ስማችሁ ስም፣ ያለ ግብራችሁ ግብር.. ‘ቅጽል’ ተሰጥቷችሁ፣
በአረመኔዎች እጅ፣ በጨካኞች በትር፣ በግፍ ያለፋችሁ፣
በዘላለም ሕይወት መንግስተ-ሰማያት ይሁን ማረፊያችሁ!
••••••
* ሕይወታቸው ተርፎ በከባድ የአካል ጉዳት የሚሰቃዩ፣ ቤት ንብረታቸው ወድሞ መጠለያ በማጣት በየሜዳው የተበተኑ…፣በወገኖቻቸው ላይ በደረሰው አሰቃቂ ጭካኔያዊ ድርጊት ውዶቻቸውን ላጡና የሰው ልጅ አእምሮ ሊሸከመው በማይችል የህሊና መታወክ ውስጥ ላሉ፣ የእግዚአብሔር ቸርነትና ጥበቃ አይለያቸው፤ ጽናቱን ያጎናጽፍልን።
* ህሊና ያለን የዚያች ሀገር ሰዎች ሆይ! ይህን በወገኖቻችን ላይ የደረሰ፣ ለመስማትና ለማየት የሚዘገንን ጭካኔና ግፍ… ከዳር እስከዳር በማውገዝ፣ የዚህ አይነቱ ጸያፍና አሳፋሪ ከንቱ ድርጊት ዳግም በምድሪቱ ላይ ስፍራ እንዳይኖረው የበኩላችንን አስተዋጽኦ ከማበርከት ባሻገር፣ በጭንቀትና በችግር ላይ ለሚገኙ ወግኖቻችን እንድረስ!