>

እስክንድር ነቅቶ ባያነቃ አዲስ አበባ በአንድ ምሽት የሶሪያዋን አሌፖ በሆነች ነበር - እልቂት፣ ውድመት ስደትና ዕንባ ...(አህመድ ሱሌይማን)

እስክንድር ነቅቶ ባያነቃ አዲስ አበባ በአንድ ምሽት የሶሪያዋን አሌፖ በሆነች ነበር – እልቂት፣ ውድመት ስደትና ዕንባ ….

አህመድ ሱሌይማን

ሻሼ ላይ የደረሰዉ ዉድመት አዲስ አበባ ላይም የታቀደዉ ነበር። ሻሸመኔን ያወደመዉ የሽብር ቡድን አዲስ አበባ ላይም ተመሳሳይ ዕልቂት ለመፈፀም ዝግጅት ነበረዉ። ነገር ግን የአዲስ አበባ ህዝብ ወጣት ሴት ወንድ ሳይል የቻለ ወጥቶ የሰፈሩን መግቢያና መዉጫ በተናበበ መልኩ በመጠበቁ ሻሼ ላይ የደረሰዉ ዕጣ ፋንታ በአዲስ አበባ እንዳይደገም አስችሏል። አንድ ወጣት በቲቪ ሲጠየቅ እኛ ሰፈር እናቶች ሳይቀሩ ዘነዘናና ሙቀጫ ይዘዉ በመዉጣት ሲጠብቁ ነበር፣ ፖሊሶችም እየዞሩ ዉጡ ሰፈራችሁን ነቅታችሁ ጠብቁ እያሉን ነበርና የቻልን ወጥተን ነበር። ያም በመሆኑ ነዉ ከተማዉን ከትርምስና ከዕልቂት የጠበቅነዉ አለ።
ለዚህ ህዝቡ ከተማዉን ከምንግዜዉም በላይ በባለቤትነት ስሜት፣ በሚገርም መናበብና ንቃተ ህሊና ለመጠበቅ እንዲችል ትልቁን አስተዋፅኦ የተወጣዉ ደግሞ እስክንድር ነጋ ነዉ። ይሄ ጥያቄ የለዉም። ላለፉት አንድ ሁለት አመታት የከተማዉ ህዝብ ማንነትና ርስቱን ለማንም አሳልፎ መስጠት የሌለበት መሆኑ ላይ እስኬዉ የሰራዉ ያላሰለሰ የማንቃትና የማደራጀት ስራ፣ በአንድ ምሽት የአፍሪካ መዲናና የኢትዮጲያ ዋና ከተማ የሆነችዉ አዲስ አበባ ወደ ሶሪያዋ አሌፖ ተለዉጣ እንዳታድርና ዛሬ ሻሼ ላይ እንደሆነዉ እልቂት፣ ስደትና ዕንባ እንዳታስተናግድ አድርጓል። እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ላይ በእንዲህ አይነት የዘረጋዉን አስገራሚ የነፍስ አድን መዋቅር በሐረር፣ በድሬዳዋና መሰል የሽብር ቡድኑ አደጋ ባንዣበበባቸዉ ከተሞች ዉስጥ ለመዘርጋት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነበር። ለዚህ ነዉ ድሬዳዋና ሐረር ላይ የተፈራዉን ያህል አደጋ ያልደረሰዉ። በትንሹም ቢሆን ነዋሪዉ በመደራጀቱ ነዉ።
ሁሉ ነገር ከቁጥጥር ዉጭ ሆኖ የማንወጣበት አዘቅጥ ዉስጥ ከመግባታችን በፊት፣ ይህንን ህዝብን ለሰላሙ ሲባል ዘብ የማቆሙና የማንቃቱ ጅማሮ እስኬዉ ከእስር ሲወጣ በሁሉም የኢትዮጲያ ከተሞች በተለይ ደግሞ በኦሮሚያ ዉስጥ ከግብ እንደሚያደርሰዉ ወይንም የእርሱን ፈለግ የተከተሉት እንደሚያደርሱት ጥርጥር የለኝም።
Filed in: Amharic