>
5:18 pm - Thursday June 14, 9477

ጃ! ግርማዊ ኃይለ ሥላሴና ህያው ስራዎቻቸው በጥቂቱ...!!! (ዘኪ ሸዋ

ጃ! ግርማዊ ኃይለ ሥላሴና ህያው ስራዎቻቸው በጥቂቱ…!!!

ዘኪ ሸዋ


* ዛሬ ደግሞ ልደታቸው ነው። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሐምሌ ፲፮ ቀን  ፲፰፻፹፬ዓ.ም ከአባታቸው  ከልዑል ራስ መኮንን  እና ከእናታቸው ከወይዘሮ የሺመቤት ኤጀርሳ ጎሮ በተባለ  የገጠር   ቀበሌ  ሐረርጌ ውስጥ ተወለዱ።
 
.ቁመታቸው ከ1 ሜትር ከ 60 ሴንቲ ሜትር አይበልጥም፣ክብደታቸውም ከ 50 ኪግ የሚዘል አይደለም፡፡በጣም አጭር እና ቀጭን ነበሩ፡፡ግን ግርማ ሞገሳቸው ልዮ ነው፡፡ጃ – የሾተላይ ልጅ ናቸው፡፡ቤተሰቦቻቸው 8 ጊዜ ወልደው ከጃ በስተቀር አላደገላቸውም፡፡በእርግጥ ጃ፣እናታቸው ወይዘሮ የሺእመቤትም በልጅነታቸው ስለሞቱባቸው ያለ እናት፣በአባት ብቻ አድገዋል፡፡አባታቸው ራስ መኮንን በባዶ እግራቸው በሮም አደባባይ ኢትዮጲያን ብሎም አፍሪካን የሸመገሉ መሪ ነበሩ፡፡
ጃ! ከአባታቸውዲፕሎማሲን ተምረዋል፡፡በዓለም ላይ ከ 160 በላይ ሀገራትን የጎበኙ እሳቸው ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአሜሪካ አሸናፊነት ሲያከተም፣የሂትለር ባድማ ጀርመን ክፉኛ ዓለም ፊቱን አዞረባት፡፡ጀርመን እንደ ሲኦል መንደር ተቆጠረች፡፡ጃ ግን የተዘጋ በር ከፍተው ጀርመንን ጎብኝተዋል፡፡አስታርቀዋል፡፡አሜሪካ ከጆርጅ ዋሽንግተን እስከ ትራንፕ ድረስ 45 ፕሬዜዳንቶችን ሹማለች፡፡ እነዚህ ፕሬዜዳንቶች በሙሉ አየር ማረፊያ ድረስ ሂደው የሀገር መሪ አይቀበሉም፡፡ጃንሆይን ግን ፕሬዜዳንት ኬኔዲ መንገድ ወጥተው ተቀብለዋቸዋል፡፡ጃ – በጃይማካ ይመለካሉ፡፡የጥቁር የነፃነት አውጭ ናቸው፡፡
ጃ- ኤርትራን አዋህደዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ከግብፅ ጣልቃገብነት ነፃ አውጥተዋል፡፡የፊውዳሊዝም ስራዓትን አሻሽለዋል፡፡ ስነፁሁፍ እንዲያድግ ነፃነትን ሰጥተዋል፡፡1960 ዎቹ ወርቃማው የስነፁሁፍ ዘመን ነው፡፡
የተፃፈ ህግን፣ ህገመንግስትን ጨምሮ አሰንደዋል፡፡ ከአፍሪካ ህብረት እስከ ተመድ ድረስ እንዲመሰረት ዋና ተዋናይ ነበሩ፡፡
የኒወክርክ ታይምስ ጋዜጣ ጃን የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ንጉስ አድርጎ ከማውጣቱም ባለፈ፣የኖቤል ሽልማት ሊሸለሙ እያለ በ 1953 ዓም በተነሳው አለመረጋጋት ምክንያት ሽልማቱ አልፏቸዋል ፡፡
የአፍሪካ መስራች ቢሆኑም፣ሀውልት ለጃ ሳይገነባ ለጋናዊው ክዋሜ ንኩርማህ ብቻ ተገንብቶ ቆይተዋል፡፡በዚህ ዓመት በጋና አነሳሽነት ከመሸም ቢሆን የአፍሪካ ህብረት የጃን ሀውልት በግቢው ለማቆም ወስኗል፡፡
ለነባር ዕውቀት ዕድገት ተግተዋል፡፡በ 1920 ዎቹ የህግ ባለሙያ ሆኖ የመጣው ፕሮቻስካ የተባለ አውሮፓዊ “አቢሲኒያ የባሩድ በርሜል”የሚል መፅሀፍ አሳትሟል፡፡ፕሮቻስካ በህግ ባለሙያነት ሰበብ ይግባ እንጂ የአውሮፓውያን ሰላይ ነበር፡፡እናም ፕሮቻስካ በ 90 ገፅ በተቀነበበ መፅሀፉ ጃንሆይ ለፈረንጅ የማያጎበድዱ ይልቁንም ጃንሆይ ና ህዝቦቻቸው ለነጭ ንቀት ያላቸው ብቸኛ የዓለማችን ሰዎች ናቸው ይላል፡፡እንዳውም ፈረንጆች አማርኛ ቋንቋ እንዲናገሩ ይገደዳሉ፡፡የኢትዮጲያን ባህል እንዲላበሱ ይወተወታሉ” የሚል ይዘት ያለው ሀሳብ አስፍሯል፡፡በእርግጥም ጃ፣ሀገር በቀል እውቀት እንዲለማ ከጣና ገዳማት እስከ አክሱም ፅዮን ያሉ አብያተክርስቲያናት እንዲታደሱ እና ለታሪክ ምርምር እንዲውሉ አድርገዋል፡፡
የዓለም ስልጣኔ መነሻው ውሃ እንደሆነ በመረዳት አባይን ከመገደብ ጀምረው ጣናን እስከ ማልማት እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር፡፡ግን በነሩሲያ የፖለቲካ ጫና እና በነጣሊያን ውስጣዊ ሴራ መክኗል፡፡የባህርዳር፣ፍኖተሰላም፣የደብረዘይት፣የሀ
ዋሳ፣የዓለማያ ፣የዝዋይ፣የሆሳዕና ፣ሻሸመኔ….ከተሞች በውሃ ዳር ስለሆኑ እንዲያድጉ ጥረዋል፡፡
የአባይ ግድብ መሰረት ጣይም ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ናቸው!!!
ለሙስሊም ህብረተሰብ የሀይማኖቱን ምሁራንን ከየአካባቢው በመሰብሰብ ቁርዐንን ከአረብኛ ወደ አማርኛ እንዲተረጉሙ ታላቅ ድጋፍ እና አስተዋፅዎ አድርገዋል
ጃ ሀምሌ 16 ቀን 1884 ዓም በሀረር ተወለዱ፡፡
ሀምሌ 16 የመጨረሻው አፍሪካዊ ንጉስ የቀዳማዊ ሀይለስላሴ የልደት በዓላቸው ነው፡፡፡፡ራስታዎችም( ጃይማካዎች) የጃንን ልደት ይዘክራሉ።
መልካም ልደት ለአፍሪካዊው ንጉስ ቀዳማዊ ኃይለስላሌ!!!!!
Filed in: Amharic