>

ያማል እጅግ ያማል ! (እንግዳ ታደሰ)

ያማል እጅግ ያማል !

እንግዳ ታደሰ

ይህን ውይይት ከማየቴ በፊት በዚሁ አባይ ሚድያ ላይ ካሜራችን በሚለው ስር የተካሄዱትን የቤት ቃጠሎችና፥ የግፉሃንን እንባ በቀጥታ በምከታተልበት ወቅት ከስር የሚጻፉ አስተያየቶችን አነብ ነበር ።
ሁሉም የሙስሊም ስም ያላቸው እና የአረበኛ ጽሁፍ መለያ ያደረጉ ሰው መሳይ አራዊቶች ገና መች አለቃችሁ ነፍጠኞች ፥ አማራዎች የሚሉ ጸያፍ ቃላቶችን ሲጽፉ እመለከት ነበር።
የእስልምና ሃይማኖት በአገራችን ከነሙሉ ቅድስናው ከትክክለኛው አስተምርሆቱ ጋር በሰሜኑ ኢትዮጵያ ለዘመናት ከክርስትያኑ እና አበሻ ብለው ከሚጠሩት  ህዝብ ጋር ሳይገዳደል በሰላም ኖሯል ።
ለምን ምስራቅ ሸዋ ፥ ለምን አርሲ ፥ ለምን ባሌ ፥ ለምን ሀረር ያለ የኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ ይህ ጭካኒያዊ ድርጊት ተካሄደ ? መንግስት ይመልስ ይህን ጥያቄ ! የአኖሌ ሃውልት እንዲሰራ በኦህዴድ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ወቅት አብይ አህመድ የሃውልቱ ማሰርያ ገንዘብ ያዥ ሆነው አገልግለዋል ሲባል ከአንድ ሚድያ ላይ በቅርብ ቀን ሰምቻለሁ ።
ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ እንደጅብራ ተገትሮ የሚታይን የጡት ሃውልት ታከው ሲሄዱና ፥ በተስፋየ ገብረአብ የተረት ተረት መጽሃፍ የተሳሉ ህጻናት ሰው ቢያርዱ ለምን ይፈረድባቸዋል? አብይ አህመድ ቤተ መንግስቱን አሰርቶ ሲያስመርቅ ፣ያኮረፉት አማካሪዎቹ በብሽሽቅ መልክ ሌንጮና ጃዋር እኮ ያን እለቱን ወደ አኖሌ ሃውልት ጉብኝት ነው የሄዱት። ኦህዴድ ጠርቶ የማይጠራ ድርጅት ነው። አራጅ ህጻናትና ወጣቶች ቢበዙ አይግረመን። የጥላቻ ሃውልት አቁመውላቸው ነው ያደጉት።
ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድ እና ብርሃኑ ተክለያሬድ ውስጣችሁን በደንብ ተረድቻለሁ። ከፍተኛ የልብ ስብራት ደርሶባችኋል። መአዛ እናት ስለሆንሽ ደግሞ የበለጠ ህመሙ ይሰማሻል።  የዲያስፖራውንም ህዝብ የወቀስሽው ወቀሳ በትክክል ነው ። አማራ መጨፍጨፉ አይነሳ ፥ የስክንድር ስም አይነሳ፥ ለጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ድጋፍ ብቻ እንስጥ የሚል ቀላዋጭ ፖለቲከኛን ብትወቅሽው ትክክል ነው። ሰሞኑን ከተቃዋሚዎች ጋር ጠቅላይ ሚንስትሩ ባደረጉት ውይይት 20 አመት አስመራ ተደብቀህ አንድ ወረዳ ነጻ ሳታወጣ እኛ በሰጠንህ ምህረት ነው እዚህ የተገኘኽው ሲሏቸው ትክክል ነው።
በጨበጣ ገንዘባችንን ሲዘርፉን ኖረው ፣ ጃክፖት ሎተሪ ወጥቶላቸው ሳይዋጉ ስለገቡ ምንተፍረታቸውን ዝም ብለው ለመንግስት ጀሌ ገብተው ቁጭ ብለዋል። አብይ ግን አልተዋቸዉም ከፊት ለፊታቸው አስቀምጠዋቸው በቃላት ጢብ ጢብ  ሲጫወቱባቸው አይተናል። እነኝህ መርዘኞች በውጭው አገር ያለውን ዲያስፖራ ለሁለት እንዲከፈል እያደረጉ በሚገደለው አማራ እና ኦርቶዶክስ ስም ቁማራቸውን ይጫወታሉ ። አበስ ገበርኩ ! ለአድርባዮች ።
Filed in: Amharic