>

"ለአንድ ሐጫሉ ግድያ ይህ ሁሉ ሰው መታረዱ ንብረት መውደሙ ልክ ነው!" ይለናል - ድምጻዊ አሊ_ቢራ ...?!? (መስከረም አበራ)

ለአንድ ሐጫሉ ግድያ ይህ ሁሉ ሰው መታረዱ ንብረት መውደሙ ልክ ነው!” ይለናል – ድምጻዊ አሊ_ቢራ …?!?

መስከረም አበራ

* በዚህ አዛውንት  አስተሳሰብ የሰው እንቁ እና መዳብ አለ፣ አንድ እንቁ ሲሞት እልፍ መዳብ መታረዱ ልክ ነው እያለ ነው! እንዴት መግባባት እንደሚቻል አይገባኝም…..
 
አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚወዳቸው እና የሚያደንቃቸው የኦሮሞኛ ዘፈን አቀንቃኝ የሆኑት ድምጻዊ አሊ ቢራ በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋ እና የዘር ማጥፍት ልክ ነው የሚል ይዘት ያለው ቃለ-መጠይቅ ከPrime media ጋር አድርገዋል።
በቃለ-መጠይቃቸውም “የኦሮሞ ሕዝብ ያጣው ውዱን እና እንቁ ልጁን ነው። በዚያ ስሜት ውስጥ ያደረገው ነገር #ልክ_ነው። አንድ ሰው ዘሎ ኪስህ ገብቶ ቦርሳህን ሲወስድብህ ዝም ብለህ ቆመህ አታይም። React ታደርጋለህ፤ ስለዚህ ችግሩ የሚሆነው እንቁህን ሲነጥቁህ ዝም ብለህ ካየህ ነው። ያጣነው እኮ ሀጫሉን ነው። መንግሥትም ከዛ በኋላ ሕዝቡ እንዲህ አጠፋ፣ እንዲያ አደረገ ብሎ የሚያወራው ነገር ስህተት ነው” በማለት፣ ከጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ጋር በማያያዝ ኦሮሞ አላጠፋም ብለዋል።
እግዜር ያሳያችሁ እንግዲህ፣ ገና ለገና ሐጫሉ ተገደለ ተብሎ፤ ብሔራቸውን መርጠው ያልተውለዱ ንጹሃንን በሃይማኖታቸው እና በማንነታቸው እየለዩ “በገጀራ ማረድ፣ በድንጋይ ቀጥቅጦ መግደል፣ አማራ አይወልድም ብሎ የ9ኝ ወር ነፍሰጡር ሴት ሆዷን ቀዶ መግደል፣ አማራ መሬታችን ላይ አይቀበርም ብሎ አስከሬኑን በጅብ ማስበላት …ይህን ሁሉ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ለሀጫሉ ሲባል መፈጸም፤ በአሊ ቢራ እይታ ልክ ነው።
እንግዲህ እነሱ በዚህ ልክ ነው የሚሳቡት፣ ጥላቻቸው ዘመን ያስቆጠረ ነው። ተቋም መሥርተው  ሲያብሰለስሉት እና ሲያቅዱት የኖረ ነገር ነው። የሐጫሉ ግድያ ማሳበቢያ ነው።
(ኦሮሞኛ ቋንቋ የምትችሉ ሰዎች ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ማድመጥ ትችላላችሁ)
Filed in: Amharic