>
5:13 pm - Saturday April 19, 8504

በፍርድ ገምድል ስርአት በግፍ ወህኒ ለተጣሉ የህሊና እስረኞች ሁሉ...!!! (ሜሮን ጌትነትና አርሴማ እናቴ)

በፍርድ ገምድል ስርአት በግፍ ወህኒ ለተጣሉ የህሊና እስረኞች ሁሉ…!!!

 
 

ፌስታልህን ስጠኝ… 

ሜሮን ጌትነት
ከጠቆረው ገፅህ ከቆዳህ ላይ ውይብ
ከከሳው ሰውነት ከግንባርህ ሽብሽብ
በፅናት ውሃልክ ይታያል ተሰምሮ
ለቃል የመታመን፣ ላመኑት
የመኖር የአላማ ቋጠሮ።
እኔማ…
ከአንተ ጨለማ ውስጥ
በወሰድኩት መብራት
ከአንተ ሰንሰለት ስር ካገኘሁት ፍ’ታት
በአንተ አለመበገር ባገኘሁት ብርታት
ወግ ደርሶኝ ጀግኜ ጬኸቴን ብለቀው
ደርሶ የፈሪ ዱላ
እንደ እያሪኮ ግንብ ተናደ ጭቆና።
እናም ታዲያ ዛሬ…
ወልዶ ላሳደገ ምጥ እንደመካሪ
ቀን የሰጠኝ ቅል ሆንኩ ዞሮ
አንተን ሰባሪ
እርግጥ ገብቶኝ ቢሆን የአላማህ ውጤቱ
መች ያስፈራኝ ነበር ያንተ ብዕር
በልጦ ብረት ካነገቱ
ፍርሃት ባይሆን ኖሮ ስጋት
የሆነብኝ ‘ካፍረቴ እያላጋ
መቼ እዘነጋለሁ የከፈልክልኝን
መራር ትግልና የነፃነት ዋጋ።
አንተ ማለት… ፅናት! መንገድህ አላማ!
ለሌሎች ደህንነት ራስን የመስጠት-
የድምፅ የለሽ አርማ።
ያልከው ዲሞክራሲ …ያለምከው ነፃነት
እስኪመጣ ድረስ…የታገልክለት ቀን
የታሰርክለት ዕለት
በከፍታህ መጠን የሞራል
ልዕልናን እንዳስታውስበት
ፌስታልህን ስጠኝ ሙዚየም
ሰቅዬ ራሴን ልውቀስበት!
ታሪክ ልንገርበት!
ፅናት ልስበክበት!
__________________________________
< ይች ቢጫ ፌስታል  እስክንድር የያዛት
የነፃነት ሰነድ ነው የቋጠረበት  ፡ ፡       
አርሴማ እናቴ
 
የፌስታሏን ምስጢር  ሳያውቁ በቅጡ
የጎሪጥ ያዩታል እነነውር ጌጡ   ፡፡
በኩንታል በኬሻ ሌቦች ሐብት ሲአሸሹ
ጀግኔ ትግል ቋጥራል ነጻነት መራሹ፡፡
ወገኑ ከበደል አርነት ሳይወጣ
እስክንድር ምንጊዜም አይፈልግም ሻንጣ፡፡
ለአርነት ነው እንጅ ለወገን ነፃነት፡
ለእርሱ ብርቁ አይደለም ምቾትና ድሎት፡፡
በዕርና ወረቀት በፌስታሉ ቋጥሮ
ይታገላል ገናም ለፈተሕ አምርሮ፡፡
ሽገጥ አልታጠቀ በጁም የለ ጥይት
ምንደር ነው? ምስጢሩ እሰክንድር መፍራት፡፡
ሰዉን በብሔሩ የማይለይ በዘሩ፡
በሰላም በፍቅር እንዲኖር በአገሩ፡
ይህንን ለሹሞች ቆሞ በመምከሩ ፡
እውን እንዲሆንም ሲታገል ከምሩ
የስክንድር መዋከብ ምንደር ነው?ነገሩ፡፡
እውነተኛ ፈራጅ ቢገኝማ ደኛ
ለአደረገው ትግል አደርገው አንደኛ፡
አለማዝ ወረቅ ሸልመው የምናየው እኛ   ፡
ይደረግ ነበረ ከሰው ሀሉ ማኛ፡፡
ዓለም ሲአጨበጭብ ቆሞ በጽናቱ
ወገኑ እንደገና ሆነበት ጠላቱ፡
Filed in: Amharic