>
5:13 pm - Friday April 19, 7107

አጀንዳዬንማ አልቀይርም...!!!   (ዘመድኩን በቀለ)

አጀንዳዬንማ አልቀይርም…!!!

ዘመድኩን በቀለ
 መልካሙን ሥራ ለማድነቅ ቅሽሽ እንደማይለኝ ሁላ ከፉውን፣ አረመኔያዊውን፣ ፋሽስታዊዉን፤  የጄኖ ሳይዱን ተግባርም ለመቃወም ቅሽሽ አይለኝም! ከኑመ ጋ ዱቢን!!!
•••
 በ1988 ዓም መሠረቱ ተጥሎ የተጀመረውን እንጦጦን የማስዋብ ፕሮጀክት በሚገባ በሥነ ሥርዓት እያስፈጸመ በመሆኑ ለዐቢቹ ምስጋና ማቅረብ ንፉግነት ነው የሚሆነው። ያምራል። ደስስም ይላል። ለዚህም ገለቶሚም እላለሁ። ቆሜም አጨበጭባለሁ። ደግሞም ዛሬ 44 ተኛ ነው 45 ተኛ የልደት በዓልህ ነው ተብሏልና እንኳን አደረሰህ ለማለትም እወዳለሁ። ነገር ግን አባው ከዚሁ ጎን ለጎን በእጅህ፣ በአስተዳደር ዘመንህ ኦርቶዶክሳውያን ላይ እየፈጸምከው፣ እያስፈጸምከው ያለውን የዘር ማጥፋት ልረሳልህ አልችልም። ምስጋናውን ለመውሰድ እንደምትንሰፈሰፈው ሁሉ ወቀሳውንም ለመቀበል አትንቀጥቀጥ። የጊዜ ጉዳይ እንጂ የፍትህ ዘመን ሲመጣ በዘር ማጥፋት መጠየቅህ አይቀርም። ዛሬ ሽመልስን በግልጽ በሥልጣን ያስቀጠልከው፣ ጊዜው፣ ገንዘቡና ሥልጣኑ በእጅህ ስላለ ነው። እናም ለወቀሳውም ተዘጋጅ።
•••
አውቃለሁ የዶር ዐብይ አሕመድ ተራሮችን ችግኝ በመትከል ማስዋብ የሚለው አጀንዳ ከየት የተቀዳ እንደሆነ ማየት አይቸግርም። ችግኝ እየተከሉ ሰው መንቀል ግን ኃጢአትም ነውርም፣ ወንጀልም ነው። የችግኝ መትከሉን ያህል ሃገር ለማዳን፣ ሕግም ለማስከበር ለምን አትለፋም? ከንግግህ ውስጥ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ከፍታ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ነው የሚል ነገር ትጠቀማለህ።  ይህን ቃል ከየት እንዳመጣኸውም እኮ ይታወቃል። ከፓስተርህ ከቀሲስ በሊና ሳርካ “የከፍታው ዘመን በኢትዮጵያ” ከሚለውና ከ18 ዓመት በፊት ከተጻፈ መፅሐፋቸው ቃል በቃል የተቀዳ መሆኑንም እናውቃለን። በዚህ መጽሐፍ ገፅ 60 ላይ “… በኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን ላይ ሲደርስ ተራራዎች ከረብቶች ሁሉ ዛፍ ይተከልባቸዋል። ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች። የሚለውን በመያዝ የብልጽግና ወንጌልን በብልጽግና ፓርቲ ቀይረህ ልክ እንደ አውሮጳና አሜሪካ ምድርን በአበባ በመሸፈን ኦርቶዶክሳውያንን በማጽዳት ኢትዮጵያን አሳድጋለሁ ብለህ እንደተነሣህ አይጠፋንም። ለዚሁም ከምድሪቱም፣ ከሥልጣኑም ሥፍራ ሁሉ የተዋሕዶ ልጆች እንዲጸዱ መደረጋቸውንም እንታዘባለን። የበሊናን ትንቢት መፈጸምህ መልካም ቢሆንም ግን ዛፍ ተክለህ ሰው ንቀል በሚለው ሰይጣናዊ ድርጊትህ ግን ነቃፊህ ነኝ።
•••
አሁን እንዲህ ያማረችዋ ከተማ እንደ ሻሸመኔ ሶሪያ ለመምሰል ሰከንድ አይፈጅባትም። በኦሮሚያ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል፣ ሆቴሎች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ አብያተ ክርስቲያናት፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ፋርማሲ፣ ጤናጣቢያ፣ ክሊኒኮች፣ የትራንስፖርት መኪኖች፣ ሱቆች፣ ህንጻዎች፣ ፋብሪካዎችን የኦርቶዶክሳዊያን ብቻ ስለሆኑ አውድመህ፣ አስወድመህ ስታበቃ አሁን አዲስ አበባን እንዲህ አደረኩላት ምናምን ብትል ያው ሚሞሪ ሾርቱን መንጋ ትሸውድ ቢሆን እንጂ ልባሞችን ለመሸወድ አይመችም። መልካም አስተዳደር ከሌለ፣ ፍትህ ከሌለ፣ መከላከያ ሠራዊቱ፣ ፌደራል ፖሊስና የከተማ ፖሊሱ በአክራሪ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች የሚመራ ከሆነ ያየነውን ለማውደም ሰከንድ አይፈጅባቸውም። ደግሞም አዲስ አበባም በሀጫሉ ሞት ምክንያት ልክ እንደ ሻሸመኔ ኢሪሊቫንት ለመደረግ ተሞክሮ እድሜ ለእስክንድር ነጋና ለሸገር ልጆች ቢታሰሩም ማማሰያ፣ መወልወያና መጥረጊያ ይዘው ታድገዋታል። እናም ብዙ ባይዘለል ሸጋ ነው።
•••
እኔ ዘመዴ አጀንዳዬን አልለውጥም። 11 ሺ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ከእነ ቤተሰቦቻቸው በራሱ በአቢቹ አስተዳደር ተፈናቅለው በዝናብና በብርድ በውርጭም፣ በረሀብም እየተሰቃዩ እያየሁ አጀንዳዬንማ አልቀይርም። መከላከያ ሠራዊቱ እያያቸው፣ ፖሊስ እየተመለከታቸው፣ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች እንደከብት ተጋድመው በሚስት፣ በልጅ፣ በባል ፊት “አላህ ወአክበር” በሚል አክራሪ በአሩሲና በባሌ፣ በሀረርጌና በጅማ አራጆች እጅ ከታረዱ እኮ 40 ቀን አልሞላቸውም። እናም አጀንዳዬን አልቀይርም።
•••
የባለማዕተቦች ቤት ተመርጦ የተቃጠለው፣ የወደመው፣ የነደደው፣ ወደ ዐመድነት የተለወጠው እኮ የዛሬ 40 ቀን አካባቢ ነው። ካህናቱ የተደበደቡት፣ ቤት ንብረታቸው የተቃጠለው እኮ አሁን በቅርቡ ነው። እናም እኔ ሞኝ አይደለሁም። እኔ ፋራም አይደለሁም። ንክር ሁላ። በአንድ ጀንበር በብልጭልጭ ነገር የምሸወድም ጀዝባ አይደለሁም። አጀንዳዬን በፍጹም አልቀይርም። በፍጹም። ፍትህ እጠይቃለሁ። የተጠቁትን እደግፋለሁ። እጮህላቸዋለሁ። ብረሳቸው ቀኜ ትርሳኝ። ባላስባቸው ምላሴ ከጉረሮዬ ይጣበቅ።
•••
መንጋው መኖህለል መብቱ ነው። እኔ ግን በመናፈሻ አበባ፣ በብልጭልጭ ቁስ የሰማዕታቱን ደም አላረክስም። ከሞት፣ ከአሩሲ አክራሪ የወሀቢይ እስላሞች የተረፉትን የተዋሕዶ ልጆች እኮ ኮሮና እያሰጋቸው ነው። ይሄው የመናፈሻ ገንቢ መንግሥት እኮ ነው ተቀምጦ ያሳረዳቸው። ሽመልስ አብዲሳ እኮ አሁንም ደንታው አይደለም። እናም በመናፈሻማ ማዕተቤን አልበጥስም። በዚህና በሌሎች መሰል አጀንዳዎች ላይ ወደ በኋላ፣ በተለመደው ሰዓት በተለመደው የዩቲዩብ ቻናሌ ብቅ እላለሁ። አቋሜንም እገልጻለሁ። ቃሌንም አስመዘግባለሁ። በሚመሰገነው አመስግኜ በሚወቀሰው እወቅሳለሁ። እንጂ እንዳንተ እንደመንጋው በመናፈሻ አበባ የሰማዕታቱን ደም አልለውጥም። አጀንዳዬንም አልቀይርም።
• ማስታወሻ | ማስጠንቀቂያም ፦ “ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት”  የሚል ስም ይዛችሁ፣ በካድሬ ቆዳ ተጠቅልላችሁ መልካችሁን በሜካፕ ወደ ተዋሕዶነት ቀይራችሁ፣ የጭቃ ውስጥ እሾህ ሆናችሁ፣ በታከለ ኡማ ቀለብ ሰፋሪነት፣ የይሁዳን ካራክተር ይዛችሁ፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ደም ለመነገድ የተነሣችሁ ወፍራም አርዮሶች ብትጠነቀቁ ይሻላችኋል። ተናግሬአለሁ።
•••
በተለይ አቶ ሙሉቀን የተባልክ አስብቶ አራጅ፣ የመስከረም 4ቱን ሰልፍ አስቀርተህ አሁን እንዲህ እንድንታረድ፣ እንድንቃጠል ያስደረከን ከንቱ የሆንክ ሰው ተጠንቀቅ። ከዚህ ነውረኛና  ጴጥሮሳውያን ብሎ በጠላት ካርታ ከሚንቀሳቀስ ዘጥዛጣ ጋር አብራችሁ የምታዘጠዝጡ የራሳችን የምንላችሁ ሰዎችም ሁሉ ተጠንቀቁ። ዲን ዳንኤል ክብረትም በስምህ እየነገዱ ነውና መላ በላቸው። ተናግሬአለሁ። ደላሎች ተፋቱን።
•••
እናንት የካርታ ደላሎች ተጠንቀቁ፣ እናንት የታከለ ቡችሎች ተጠንቀቁ። እናንት አስመሳዮች ተጠንቀቁ። ዝም ስንል ሞኝ አንምሰላችሁ። እስስቶች። ማኅበረ ቅዱሳን ከእነዚህ ኮተቶች ጋር ያለህን ጉዳይ አቁም። ይዘውህ ገደል ይገባሉና ተጠንቀቅ። ለተፈናቀሉት የሰማዕታት ቤተሰቦች ተብሎ የተሰበሰበው ገንዘብ ላይ ለመከመር ያሰፈሰፋችሁ ጆፌ አሞሮች ሥነሥርዓት ያዙ። እናንት የሙዳይ ምጽዋት አይጦች ተጠንቀቁ። ይሄ የደም ገንዘብ ነው። ነቀርሳ ነው የሚሆንባችሁ ተጠንቀቁ። እናንት ነፍሰ በላዎች፣ ከአራጅ እኩል የምትቆጠሩ አውሬዎች ተጠንቀቁ። ስማችሁን ሳልጠራው አስቡበት። በተለይ ጴጥሮሳውያን የተባልክ ጆከራም አደብ ግዛ።
•••
ይሄንንም በሰፊው እመጣበታለሁና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ። እነዚህ ከሃዲዎች፣ በታከለ ኡማ ኮንዲሚንየም ሃይማኖታቸውን አሳልፈው የሰጡ ይሁዳዎች እነማን እንደሆኑ በስም ዝርዝር ከእነ ፎቶአቸው አስቀምጣለሁ። ቀልድ የለም።
ጠላትማ ጠላት ምንጊዜም ጠላት ነው፣
አስቀድሞ …… አሾክሻኪውን ነው። አከተመ።
•••
ሻሎም
Filed in: Amharic