>

ሃረርጌ፣ ባሌና አርሲ ሙሉ በሙሉ  በመከላከያ ስር መሆን አለባቸው!!! (ግርማ ካሳ)

ሃረርጌ፣ ባሌና አርሲ ሙሉ በሙሉ  በመከላከያ ስር መሆን አለባቸው!!!

ግርማ ካሳ

በድረዳዋ፣ አወዳይ፣ አሰበ ተፈሪና ሻሸመኔ ቢያንስ ከ8 እስከ 13 ያሉ ተቃዋውሞ ለማሰመት የወጡ የሞቱ ሲሆን በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል! የሞቾች ቁጥር ከዚያ በላይ ሊሆን ይችላል!?!
 
* በሌሎች ማሀብረሰባት ላይ የደረሰ የሰው ሕይወት መጥፋት፣ ወይንም የንብረት ውድመት ስለመኖሩ እስከአሁን የተዘገበ ነገር የለም!
 
12/12/12  በሚል ልክ ያኔ ኢጂቶዎ 11/11/11  ብለው ተቃውሞ ጠርተው እንደነበረ ፣ ጽንፈኞች  ለአምስተኛ  ጊዜ ተቃውሞ ጠርተው ነበር፡፡ በዙኛው ተቃውሞ የነ አቶ ለማና ጠይባ ሁሴን መባረርና፣ እንዲሁም “ጃዋር ታሟል”   የሚለው የሰዉን ስሜት ቀስቅሶ ለተቃውሞ ያስነሳል የሚል ግመት ነበራቸው፡፡ ይሄ ተቃውሞ እንደማይሳካ አስቀደመነ ብዙዎቻችን ተናግረን ነበር፡፡
ያኔም ቢሆን የኦሮሞ ፕሮቲርስት ተብሎ ይጠራ የነበረው ብዙ ተቃውሚዎችን በተለያዩ ቦታዎች ማድረግ የቻለው ፣ የኦህዴድን መዋቅር ይጠቀሙ ስለበረ፣ የኦሮሞ ክልል ታችኛው አመራሮችና ፖሊሶች የተቃውሞ አካል ስለነበሩ፣ ለተቃዋሚዎችም  የሕግ ከለላ ያደረጉ ስለነበረ  ነው፡፡
እነ ጃዋር እሰር ቤት ባይሆኑም፣  ተቃውሞዉን ጠርተዉት ቢሆን ኖሮም የሚለወጥ ነገር አይኖርም ነበር፡፡ ያኔም የነጃዋር ኃይል የመንግስት መዋቅር መያዛቸው ነበር፡፡
የኦሮሞ ክልል 21 ዞኖች ነው ያሉት፡፡ ከነዚህ ዞኖች የተወሰኑ ተቃውሞዎች የታዩት በ4 ዞኖች ብቻ ነው፡፡ ምስራቅና ምእራብ አህረጌ፣ ምእራብ አርሲና ባሌ፡፡ በነዚህም ዞኖች በሁሉም ቦታ ሳይሆን በተወሰኑ ወረዳውችና ቀበሌዎች ብቻ ነው፡፡ 90% የኦሮሞ ማህበረሰብ የሚኖርባቸው አካባቢዎች ዜጎች በስላም እየኖሩ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እጅግ በጣም ጥቂት የነጃዋር ተከታይ የኦሮሞ ጽንፈኞች ፣ በኦሮሞ ስም ቢነግዱም፣ 95% ኦሮሞዉን በጭራሽ የማይወክሉ መሆናቸው ይሄ አንዱ ማሳያ ነው፡፡
በምአራብ ኦሮሚያ ከአሰበ ተፈሪ ውጭ ያሉ ጽንፈኞች ወደ አሰበ ተፈቲ መጥተው ተቃውሞ ለማሰማት ሞክረው ነበር፡፡ በዚያ ዜጎችን ከነዚህ ጽንፈኛ ተቃዋሚዎች ለመጠበቀ በተደረገ ሙከራ 2 ተቃዋሚዎች የተገደሉ ሲሆን 11 የሚሆኑ ቆስለዋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታም በድሬዳዋ ከተማ 2 ተገድለዋል፡፡ በአወዳይ የነበረ ሁኔታ ትንሽ የከፋ ነበር፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ቢያንስ 3  ተቃዋሚዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ብዙዎች ቆስለዋል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የቀረቡ አንድ የከተማዋ ነዋሪ ቢያንስ 8 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል፡፡ አወዳይ ከዚህ በፊት በኦሮሞ ጽፈኞች በአንድ ቀን ከ65 በላይ ሶማሌዎች የታረዱባት ከተማ ናት፡፡
በሃረር ፣ በባሌና በምእራብ አርሲ በአንዳንድ ቦታዎች ተቃውሞ የነበረ ቢሆንም በቀላሉ በቁጥጥር ስር ለማድረግ ተችሏል፡፡ በሻሸመኔ ተቃውሞ ለመቀስቀስ ተሞክሮ መከላከያ ወዲያው ተቆጣጥሮታል፡፡ አንድ ተቃዋሚም ተገድሏል፡፡
በአጠቃላይ በድረዳዋ፣ አወዳይ፣ አሰበ ተፈሪና ሻሸመኔ ቢያንስ ከ8 እስከ 13 ያሉ ተቃዋውሞ ለማሰመት የወጡ የሞቱ ሲሆን በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ቢያንስ ነው ያልኩት፡፡ የሞቾች ቁጥር ከዚያ በላይ ሊሆን ይችላል፡፡
በሌሎች ማሀብረሰባት ላይ የደረሰ የሰው ሕይወት መጥፋት፣ ወይንም የንብረት ውድመት ስለመኖሩ እስከአሁን የተዘገበ ነገር የለም፡፡
አሁንም መንግስት በተለይም ሃረርጌ፣ ባሌና አርሲ ላይ ትልቅ ትኩረት በመስጠት፣ በአንድ በኩል አካባቢው ሙሉ ለሙሉ በመከላከያ ስር እንዲሆን በማድረግ በአስተማማኝ ሁኔታ ሰላምንና መረጋጋት እንዲሰፍን ማድረግ አለበት፡፡
ይ ብቻ በቂ አይደለም፣ በሌላ በኩል በዚያ ለሚኖረው እጅግ በጣም ብዙ ስራ ፈት ወጣት፣  ተስፋ የሚሰጥ፣ በአካባቢው ስራን የሚፈጥር እቅድ አውጥቶ መንቀሳቀስ መጀመር አለበት፡፡
Filed in: Amharic