>

የደኅንነት ዋስትናዬን ማስጠበቅ ያልቻለ መንግሥት ለምኔ? (ከሽግዬ ነብሮ- ኢጆሌ ባሌ)

የደኅንነት ዋስትናዬን ማስጠበቅ ያልቻለ መንግሥት ለምኔ?

ከሽግዬ ነብሮ

ኢጆሌ ባሌ


  “ዳኛውም ዝንጀሮ

   ፍርድ ቤቱም ገደል

 ከየት ላይ ተቁሞ ይነገራል በደል”

 

በሀገሪቱ ሊፈጠሩ የሚችሉ የፀጥታ ችግሮችን አስቀድሞ መተንበይ ወይም (forecast) ማድረግ፣ የሚወሰዱ ጥንቃቄዎችንና አስከፊ ክስተቶች ካጋጠሙ ሊወሰድ የሚገባውን እርምጃ ለፖሊሲ አማካሪዎችና ለመንግሥት ማሳወቅ የአንድ ሀገር የደኅንነት (intelligence) መሥሪያ ቤት ቀዳሚ ተግባር ነው።

ይህ ሳይደረግ በመቅረቱና በሌሎች ምክንያቶች የአርቲስት ሀጫሉን ህልፈት ሰበብ አድርጎ ሆኖም ግን አስቀድሞ በደንብ በታቀደና በተዘጋጀ መልኩ በኢትዮጵያ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የዘር ማጥፋትና(genocide) የዘር ማፅዳት(ethnic cleansing) ተካሂዷል።

የዜጎችን እልቂት በተመለከተ ከሳምንታት በኋላ በሌላ ጉዳይ ላይ በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ያሉት ኮሎኔል አብይ አህመድ ዓይናቸውን በጨው አጥበውና ፍርጥም ብለው መቶ ምናምን ሰው በሚያሳፍር ሁኔታ ሞቷል፤ እኛ ግን 9500 ሰው ነው ያሰርነው። በአንዳድ አጥፊዎች ምክንያት ብሔርን መፈረጅ አይጠቅመንም፤ ትናንሽ ነገር ባየን ቁጥር ወ.ዘ.ተ በማለት አቃለው የሕዝቡን ሀዘን አጣጥለውታል።

በሊባኖስ በተፈጠረው የፈንጅ አደጋ አንካሳ ዶሮ ሳትቀድመኝ ብለው የሀዘን መግለጫ ለመስጠት  ከዓለም መንግሥታት ቀዳሚ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር፣ በሀገራቸው ስለታረዱት ወገኖቻችን እንደተራ ረብሻና የግለሰቦች የእርስ በርስ ፀብ አድርገው ያዩት የአጥቂዎቹን ቡድን ፈርተው ወይስ ወገንተኝነት ይዟቸው? የእሳቸው መንግሥት አመነም አላመነም ኦሮሚያ ውስጥ በኦሮሞ ፅንፈኞች የስም ዝርዝር ተይዞ ቤት ለቤት እየተኬደ አማራ፣ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮችና (ኦሮሞና የሌላ ብሔረሰብ ተወላጆችን ይጨምራል) ሀብታም ነጋዴዎችን ኢላማ ያደረገ የዘር ጭፍጨፋና የንብረት ማውደም ተካሂዷል። ከአንድ ቤት አምስት የቤተሰብ አባላት አማራ በመሆናቸው ብቻ በአሰቃቂ ሁኔታ ታርደዋል። ገዳዮቹ አስከሬን አናስነሳም በማለታቸው ለቀናት አስከሬናቸው ሜዳ ላይ ተጥሎ ሳይቀበሩ ሰንብቷል። በኋላም በመከላከያ ሠራዊት ታጅቦ ለመቅበር ሲሞከር አማራ ከእኛ ክልል አይቀበርም በሚል የለየለት ጥላቻ ምክንያት በደህና ቀን አስቀድመው ባሠሩት መቃብር እንዳይቀበሩ በመከልከላቸው የተቀበሩት ሌላ ቦታ ተጓጉዘው ጓደኛቸው ለራሳቸው ባዘጋጁት  መቃብር ነው። የሰው ልጅ እንደቦረንቲቻ እየታረደ እጁ ተገንጥሎ እንደዋንጫ እየተዘፈነበት፣ የዘጠኝ ወር ነፍሰጡር አማራና ክርስቲያን እዚህ አይወለድም ተብላ ባለቤቷና ሕፃናት ልጆች እንዲያዩ ተደርጎ ስትታረድ፣ የሰው አካል በሜንጫና ገጀራ ተቆራርጦ ለጅብ ሲሰጥ፣ እየገደሉና ንብረት እያወደሙ “አላህ ዋአክባር” እያሉ ገዳዮች ሲጮሁና ሲፎክሩ ሕዝብን ለመከላከል ምንም ዓይነት እርምጃ አለመውሰዱና የተፈጸመውን ጥፋት አቃሎ ማቅረብ “ምን አይታችሁ ከዚህ የበለጠ ገና ይጠብቃችኋል?” ክማለት ውጪ ሌላ ምን ይባላል።

በኦሮሚያ ደን ውስጥ ይፈራ የነበረው አውሬ ነበር። አሁን ግን ደኑ ተመንጥሮ፣ እንስሳው ጠፍቶ፣ የኦሮሞ ጀሀዲስትና ፅንፈኛ ተፈጥሮ በኦሮሚያ ከተሞች እንደሰው በሁለት እግሩ የሚሄድ ሆኖም ግን የሰው ሰብዕናን ያልተላበሰ ሰው መሳይ ጨካኝ አውሬ ሆኗል የሚፈራው።

የሀዘን ቀን ታውጆ፣ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ፣ ማቅ ለብሰን ሀዘን መቀመጥ የሚገባ አሁን ካልሆነ መቼና ምን  ሲፈፀም ነው? በእርግጥ አሰቃቂው የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈፀመው ኦሮሚያ ውስጥ በፅንፈኛ ኦሮሞዎች ቢሆንም የኦሮሞን ሕዝብ በምንም ዓይነት ሊወክል አይችልም። ምክንያቱም ቁጥራቸው በቀላሉ የማይገመት የኦሮሞ እናቶችና አባቶች የእስልምናም ሆነ የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች ወገናችውን ከባሰ እልቂት እንዳተረፉና ባደረጉት መከላከልም እራሳቸው የአራዊቶቹ ሰለባ እንደሆኑ አፅንኦት ሊሰጠው ይገባል። ይህ ማለት ግን አንዳንዶች ሊያድበሰብሱትና ሊክዱት እንደሚሞክሩት የዘር ፍጅት (Genocide) አልተፈፀመም ማለት አይደለም። 

ዱላና ገጀራ ይዞ የወጣውንና ሰውን እንደከብት በአሰቃቂ ሁኔታ ያረደውን አይቶ እንዳላየ ከማለፍም በላይ በፖሊስ እንዲታጀብ ሲደረግ፣ በወላይታ ባዶ እጁን በወጣው ሰላማዊ ሕዝብ ላይ ግን የፀጥታ አስከባሪዎች ጥይት ተኩሰው እሰከ 41 የሚደርሱ ዜጎች ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ አድርሰዋል። ሀገር አስተዳድራለሁ የሚል መንግሥት እንዲህ ዓይነቱን ዓይን ያወጣ መድልዖ ሲፈፅም ሕዝብ በመንግሥት ላይ ያለውን ዕምነት በእጅጉ ይሸረሽራል። 

“All animals are equal, but some

 Animals are more equal than others”

    Animal Farm

   George Orwell

ድርጊቱ በውጭና በውስጥ በሚገኙ አክራሪ የብሔርና የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ጂሀዲስቶች የተፈፀመ ስለሆነ መንግሥት በሀገሪቱ genocide and ethnic cleansing እንደተፈፀመ አምኖ ፅንፈኞችን በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በሕግ ሊፋረዳቸው ይገባል። ፖሊሶች ጥፋት በተፈፀመባቸው አዲስ አበባን ጨምሮ በቦታው እያሉ ከበላይ አካል አጥፊዎችን “አትንኳቸው” ተብልው ጥፋት እንደተፈፀመ ከራሳቸው ከፖሊሶቹ መረጃ ስለአለ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ይህ ትዕዛዝ ከየት እንደመጣ ምርመራ ሊካሄድበት ይገባል። በቦሌ መንገድ የሕንፃዎች መስታዎት ሲረግፍ ፖሊሶች በቦታው ነበሩ። ህፃን ልጅ ያዘለች ሳትቀር ድንጋይ ስትወረውር ነበር። አጥፊዎችን ያሠማራቸው አካል አበል እንደቆረጠላቸው ታውቋል። 

በኢትዮጵያ ያለው ችግር ሀገሪቷ በፈደራል ሥርዓት መመራቷ ሳይሆን፣ የምትከተለው ነገድን መሠረት አድርጎ የተዋቀረው ፌደራላዊ አደረጃጀት ነው። ሀገሪቱ በዘጠኝ የነገድ ክልሎች ተከፋፍላ አንዱ ነገድ በሌላው ነገድ ጥርጣሬና ጥላቻ እንዲኖረው ተደርጎ በህዋሓት ዘረኛና የሌቦች ቡድን ታስቦበት የተቀመረ ከቅኝ ገዢዎች የተወሰደ (divide and rule) ከፋፍለህ ግዛ ነው።

ሁሉም የሀገሪቱ ነገዶች ሳይመክሩበትና ሳይቀበሉት በሕወሓት ለሕዝብ መከፋፈያነት ተረቅቆ በተለጣፊና አድርባዮች አዳማቂነት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተጫነውና የችግሮች ሁሉ ምንጭ የሆነው ሕገ መንግሥት እሰካልተቀየረ ድረስ፣ እንድ እርምጃ ወደፊት፣ ሁለት  እርምጃ ወደኋላ ነው የሚሆነው። “የዓሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ” ይባል የለ።

አንዱ ክልል ሌላውን ክልል በባላንጣነት የሚያይበት ሀገር ምንም ያህል የልማት ሥራ ቢሠራም ክልሉንም ሆነ መላ ሀገሪቱን ወደፊት የሚያራምድ ሊሆን አይችልም። መዘዙ ነገድን ከነገድ በፖለቲካ፤ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ኑሮ ከማናቆር ይልቅ የሚያመጣው ሠላምና ብልፅግና የለም። ብሔራዊ መግባባትና አንድነት እሰከሌለ ድረስ እርሰ በርስ አናቋሪ የዘር ፖለቲካ ተሸክሜ ሀገር እመራለሁ፤ ኢኮኖሚ አሳድጌ የድሃው ሕዝቤን ኑሮ እቀይራለሁ ማለት ዘበት ከመሆኑም ሌላ ታጥቦ ጭቃ መሆኑን ከሰሞኑ ያየነው ፍጅትና የንብረት ውድመት ጥሩ ምሳሌ ሊሆን ይገባል።

የታሰበው ምርጫ እንኳን ይደረግ ቢባል ፉክክሩ የሀሳብ ሳይሆን የሚጠላሉ ነገዶች ውጊያ ይሆንና መልኩን የቀየረ ጦርነት ነው የሚሆነው። ተፎካካሪውም ሆነ መራጩ በአዕምሮው ይዞ የሚመጣው ጭንቅላቱ ውስጥ የተሰነቆረውን ጎሠኝነት እንጅ መልካም አስተዳደርና የሀገር ልማት የሚመጣበትን መንገድ በማሰብ አይሆንም።

አሁን የሚታየው የዘር ማጥፋትም ከሩዋንዳው የዘር ዕልቂት የተመሳሰለ የነገዶች መከፋፈልና መጠላላት ውጤት ነው። በሥልጣን ላይ የነበረው ሕወሓት የራሱ ነገድ ተወላጆች ሁሉን ተቆጣጥረው ሲያደርሱ የነበረውን በደል አይተናል። በአንፃሩ ወያኔ ከተባረረ በኋላ ሥልጣኑን የተቆጣጠረው ነገድ በተራው ሁሉን “ኬኛ” በሚል አይጠግቤ የፖለቲካ ፍልስፍናው ኢኮኖሚውንና የፀጥታውን ክፍል ተቆጣጥሮታል። ለምሳሌ ያህል የአዲስ አበባን የፖሊስ ኃይል በራሱ ሰዎች ሞልቶ ሕግ ከማስከበር ይልቅ የአዲስ አበባን ወጣት በየምክንያቱ ሲቀጠቅጥ ይውላል። ቀደም ሲል የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በተመለከተ የተጋተው የተዛባና መርዛማ ትርክት ስላለ ሰንደቅ ዓላማውን የያዘ ካየ ንዴቱ ገንፍሎ ሲወጣበት ይስተዋላል። ይህም በመስቀል በዓል አከባበርና በቅርቡ በተደረገው የአባይ ግድብ ሙሌት የድጋፍ ሰልፍ ላይ በገሐድ ታይቷል። አዲስ አበባን የራሱ ብቻ ለማድረግ በከንቲባው አማካኝነት ቦታ ይስጣል፤ ሌላው የሠራውን ኮንዶሚኒየም ለወገኖቹ ያከፋፍላል።

ዘር ማጥፋት (genocide) ታስቦበት በተጠና መልኩ አንድን ሕብረተሰብ በጎሳው፣ በብሔሩ፣  በዘሩ ወይም በሀይማኖቱ ለይቶ ማጥፋት ነው። ለዚህም በዓለም ላይ የተከሰቱ እልቂቶች (Holocausts)፣  የአርመኖች፣ የቀይ ሕንድ አሜሪካኖች፣ የካምቦዲያና የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋዎች ናቸው።

በሀገራችንም በጋምቤላ የአኝዋኮች አልቂት፣ በወልቃይት፣ በአሶሳ፣ በአርባጉጉ፣ በበደኖ፣ በምሥራቅ ወለጋ፣ በአርሲ፣ ባሌና ቤኒሻንጉል አማራዎች፣ በጌዲዮ የጌዲዮ ተወላጆች፣ በቡራዩ ጋሞዎች ተመርጠው የዘር ፍጅት ተፈፅሞባቸዋል። ሆኖም ግን ይህንን እልቂት (Genocide) እውቅና ሰጥቶ የእርምት እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ማዳፈንና መካድ በመመረጡ ዕልቂቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መጥቷል።

የሕወሓት የትምህርት ሥርዓት በመላ ሀገሪቱ የተነደፈውና የተተገበረው ኢትዮጵያን ወደፊት ሊያራምድ በሚችለው በሂሳብና በሳይንስ ትኩረት አድርጎ ሳይሆን፣ በጎሳ ፖለቲካ ላይ አፅንኦት ሰጥቶ ነው። ሰለሆነም ነው በዩኒቨርሲቲና በከፍተኛ ተቋማት በየጊዜው ብጥብጥ እየተነሳ ሀገር ሲረበሽ የሚከርመው። መንጋ ለመሆን እውቀት አይጠይቅም። ቄሮ የተባለው መንጋ የተደራጀው ለዚህ ነው። በውጭ ያሉና ወደሀገር የገቡ ፅንፈኞች የሌላውን ነገድ ተወላጆች ባዕዳንና “alien” ሰፋሪዎች settlers “Ethiopia out of Oromia” እያሉ ወገን ሲያስጨርሱና ንብረት እንዲወድም ሲያደርጉ ይውላሉ።

 “You can’t go back and change the beginning, but you can start where you are and change the ending.”                            

Clive Staples Lewis

 

ታሪክን በጭንቅላት፣ የወደፊቱን በእጅ ይዞ መጓዝ ካልሆነ ግን ማን መጤ፣ ማን ሠፋሪ እንደሆነ ለመመሥከር ብዙ የተዘከረበት ነው። እዚህ ላይ ማንሳቱ እነሱን መሆን ሰለሆነ ለጊዜው መተው ቢሻልም፣ በውሸት ትርክት ተወልደው በውሸት ትርክት ያደጉት ደናቁርት ሲያበዙት ግን አንዳንድ ሐቅ ሊነገራቸው ይገባል። 

Much of their history is selective mythology. They forget that in historical terms the Oromos are one of the newest peoples in Ethiopia. Europeans in North America and Whites in South Africa have occupied their territories longer than Oromos in the most regions of Ethiopia.

                                                  Paul Henze

                                                   Former C.I A Station Chief for Ethiopia

አቦይ ስብሀት ነጋና ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ብዙ የሚመሳሰል ነገር አላቸው:: ሁለቱም ዩኒቨርሲቲ ገብተው ወጥተዋል፤ ሉንጎዎች ቢሆኑም ጠባብ ብሔረተኝነት ያጠቃቸዋል፤ “በውሻ ሆድ ቅቤ አያድርም” እንደሚባለው ያሰቡትንና የሰሙትን በየቦታው ይዘረግፉታል። የሁለቱ ልዩነት አቦይ ስብሀት ተንኮለኛ ፖለቲከኛ ሲሆኑ አቦ ሺመልስ ግን ሞፎ መሆናቸው ነው። ግለሰቡ ለዶ/ር አብይ የክቡር ዘበኛነት ወይም ለትራፊክ ፖሊስነት እንጂ ለፖለቲካ የሚሆኑ አይደሉም። ተክለ ሰውነታቸውም ለዚህ የሚመረጥ ነው። ሁለቱም የሚጋሩት ግን “Politics have no relation to morals” የሚለውን የNiccolo Machiavelli አስተምህሮ  ነው።

ቃሊቻ፣ ቦረንቲቻና ኢሬቻ የባዕድ አምልኮ መግለጫዎች ናቸው። የኢሬቻ በዓል በደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ሆራ ሀይቅ ከጥንት ጀምሮ ሲከበር የነበረ ነው። ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን የሌላውም ነገድ አባላት የተወሰኑ ችግር ያለባቸው መፍትሔ እናገኝበታለን ብለው ሌላውም እንደመዝናኛ (day out) ይታደሙበታል።

የፕሮቴስታንት ሀይማኖት ተከታይ የሆኑት የፈጣሪ ስምና ምስጋና ከንግግራቸው የማይጠፋው ዶ/ር አብይ አህመድ ለኦሮሞ እንደ አንድ የድል ቀን በመቁጠር በእሳቸው መመሪያ በዓሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት የመስቀል በዓል በሚከበርበት ቦታ ላይ አርቴፊሻል ኩሬ ፈጥረው እንዲከበር ማስደረጋቸውን የኦሮሚያው ፕሬዝዳንት ነግረውናል። በእነጀዋር መሐመድና ሌሎች ፅንፈኞች ተከበው መድረክ ላይ ጎላ ብልው የታዩት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳም በስሜት ሰክረው የሚከተለውን ተናግረዋል “ሆድ ያባውን የስሜት ስካር ያወጣል” ቢባልስ።

“የኦሮሞ ሕዝብ እዚህ ነው የተሰበረው፤ እዚህ ነው ውርደቱ የጀመረው፤ እዚህ ነው ቅስሙ የተሰበረው፤ እነቱፉ ሙና እና ሌሎችን የነፍጠኛው ስርዓት እዚህ  ነበር የሰበሯቸው። ዛሬ የሰበረንን ከስሩ ነቅለን፣ ኦሮሞ በተዋረደበት ቦታ ኢሬቻ ተከብሯል፤ ኦሮሞ እንኳን አሸነፍክ”::

በዚህ የጥላቻ ንግግር ምንም ያልተባሉት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ከወራት በፊት ደግሞ የቅርብ የኦሮሞ ባለሥልጣኖችንና ባለሃብቶችን በሚስጥር ሰብስበው የብልፅግና ፓርቲን ፍኖተ ካርታና የተከናወኑ  ሥራቸውን በአደባባይ ዘርግፈውታል። ኦቦ ሽመልስ ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ ነበር ያሉት፦

“በሕጋዊም ሆነ በሕገወጥ መንገድ የኦሮሞ ተወላጆችን መታወቂያ በመስጠት የአዲስ አበባ ነዋሪ ማድረግና ዲሞግራፊውን መቀየር፣” 

ኢንጂነር ታከለ ኡማ መታወቂያ በመስጠት፣ ማዘጋጃ ቤት በመቅጠር፣ መሬት በማደል፣ በሌሎች ገንዘብ የተሠሩ የኮንዶሙኒየም ቤቶችን በማከፋፈል የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ሲያደርጉ፤ የገቢዋች ሚኒሰትር የነበሩት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ደግሞ ሥራ በማስያዝ የዲሞግራፊው ለውጥ አሳልጠዋል። በተጨማሪም በመገናኛ አካባቢ በሕዝብ መዋጮ የተሠሩ የኮንዴሚኒየም ቤቶች ከሕግ ውጭ ለገቢዎች ሚኒስቴር ሠራተኞች እንዲታደሉ አድርገዋል።

 

ወይዘሮ አዳነች ለጃዋር OMN 58 ሚሊዮን ብር ከመንግሥት ካዝና ዘግነው በሕገወጥነት ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በረሀብ አለንጋ እየተገረፈ የሀገሪቱ ሃብት ለጥጋበኛና ዘረኛ በበረክት የሚሰጠበት ሀገር ሆኗል። “አውራ ዶሮ በሰው ስጥ ሚስቱን ይጋብዛል።” በአቃቤሕግነት ተመድበው መቀመጫቸው በቅጡ ወንበር ሳይዝ በቅርቡ በነበረው የቄሮዎች ረብሻ የአዲስ አበባ ወጣቶች ኦሮሞ አይገዛንም ብለው ብጥብጥ ፈጠሩ በሚል ቅጥፈት እነ እስክንድር ነጋን በሃሰት ወንጅልዋል። “አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ።” እንግዲህ እኝህ ሴት ናቸው የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ሆነው የተሾሙት። በእሳቸው የሥልጣን ዘመን የአዲስ አበባ ከተማ ከመቼውም በበለጠና በከፋ ሁኔታ በዘር መድልኦ ሥር እንደምትወድቅ አስቀድሞ ለመናገር ነብይ መሆን አያስፈልግም። አባባላቸው በጥቅሉ ሲታይ አሁን በአዲስ አበባ ያለውን ሕዝብ አንፈልግም በራሳችን በኦሮሞ ነገድ ቀስ እያልን እየቀየርን ነው ለማለት ነው።

“ሊሎች እህት ከተሞችን በማሳደግ አራት አምስት የፈደራል ከተሞችን በመመሥረት የአዲስ አበባን ተፈላጊነት ማጥፋት”፣ 

የእህት ከተሞች ማደግና መመሥረት ባይከፋም ጥያቄው እነዚህን ከተሞች ለመመሥረት የታሰበው የት ነው የሚለው ነው። መቼም ከኬኛ ፖለቲከኞች ባህሪይ አኳያ አብዛኛው ከኦሮሚያ ውጭ ይሆናል ብሎ ማሰብ ያስቸገራል። አዲስ አበባ አስፈላጊነቷ የሚጠፋውስ ለምንድነው? ሰው በገዛ ሀገሩ ላይ ምቀኛ ይሆናል?

“ለኦሮሞ ነጋዴዎች ሁኔታዎችን በማመቻቸት በአዲስ አበባ ውስጥ ቁጥራቸውን መጨመር”፣

በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች በአህያና በጀርባቸው እየተሽከሙ ሩቅ መንገድ ለሚጓዙ ወገኖች ድካም ማቅለያ ቢሠራ ሌሎችም ከፍተኛ የሆኑና አነስተኛ ነጋዴዎች በአዲስ አበባም ሆኑ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች በንግድና በሌሎች ሥራዎች ቢሰማሩ እሰየው ነው እንጅ ምድነው ችግሩ? ጥያቄዋ ያለችው ግን ቁጥራቸውን መጨመር የምትለዋ ላይ ነው። ይህች ለምን አሰፈለገች? አዲስ አበባ “ኬኛና” ኦሮሙማን ለማስፈፀም ካልሆነ በስተቀር።

“አማራ ቁልቁል እየሄደ ነው እየሞተ ነው ማለትም አማርኛ ቋንቋን እየገደልን ነው፤ 56 ሺህ የኦሮሞ አስተማሪዎችን ኦሮምኛን ለማስፋፋት አዲስ አበባ አስገብተነናል”።

ሽሜ እዚህ ላይ ልክ ናቸው፤ አማራ በእሳቸው ነገድ እየተገደለ ቁጥሩ መቀነሱ የማያጠራጥር ነው። ከዚያ ላይ ደግሞ የውሸት ሕዝብ ቆጠራ ታክሎበት። ቋንቋው እየሞተ ነው ያሉት ግን እየሞከራችሁ ነው እንጅ እንደዚህ በቀላሉ የሚሞት አይደለም። አማርኛ የሀገሪቱ ዋንኛ ብሔራዊ ቋንቋ መሆኑ ወደዳችሁም ጠላችሁ ይቀጥላል። የራሱ ፊደልና ስነፅሑፍ ታሪክ ያለው በአውሮፓ፣ አሜሪካ ዩኒቨርስቲዎችና በኮሌጅ ደረጃ ለቋንቋ ትምህርትነት ብቅ እያለና እያቆጠቆጠ ነው። አፍሪካውያንም እንደራሳቸው ቋንቋ ለማድረግ እየታገሉለት ነው። ኦሮምኛ እንደ አንድ ብሔራዊ ቋንቋ ይወሰድ ቢባልም ሌላውን ጨፍልቆ ሊሆን አይችልም። ነፃይቱንና የአፍሪካ ብሎም የጥቁር ሕዝብ የነፃነት ምልክት የሆነችውን ኢትዮጵያን በአውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎች በቅኝ  የተገዛች ይመስል በላቲን ፊደል እየተጠቀሙ ማቅራራቱ እጅግ አሳፋሪ ነው። ይህ ድርጊት በአንድ ወቅት ጳውሎስ ኞኞ የትኛውን ዘፈን ትመርጣለህ ሲባል “አሥር ላሌጉማ ቢጨመቅ አንድ ሞናሊዛዬ ነሽ አይወጣውም” እንዳለው ነው።

“ግድቡ ባለበት ቤንሻንጉል ቁጥራችን 37% ደርሷል።”

ግድቡ የተሠራው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም እስከሆነ ድረስ ቁጥራችሁን እዚህ ቦታ ላይ ማበራከት ለምንስ አሰፈለገ? ስትራቴጃችሁ የወያኔን የትግል ዓላማ በመከተል የኦሮሚያ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክን ለመመሠረት ከሆነ፣ አባይ የሚመነጨው በግዮን የአማራ ግዛት እስከሆነ ጊዜ ድረስ ግድቡ ያለበትን ቦታ (እንደ ወያኔ ወልቃይት ራያ) ብትቆጣጠሩ እንኳን ካለ አባይ ወንዝ የከብት በረት ታደርጉት ይሆናል እንጅ ፋይዳ የለውም። ብዙ አርቃችሁ አስባችሁ ከሆነ፣ “እዚያም ቤት እሣት አለ የሚለውን” ብሂል አብሮ ማገናዘቡ አዋቂነት ነው። (ከዚህ እኩይ እሳቤያችሁ ተነስተን ቁጥሩን ለመቀነስ ሲባል ከወያኔ ጋር በማበር አማራውን በቤኒሻንጉል በሀገሬው ሕዝብ በቀስት የምታስጨርሱት እናንተ ትሆኑ ይሆን ብለን ብናስብ ይፈረድብን ይሆን?)

“ኦሮሚያ ከሌሎች ክልሎች በበለጠ በኢኮኖሚ እያደገች ነው”

የኦሮሚያ ማደግ፣ ሕዝቧ ከድህነት መላቀቅ፣ የኢትዮጵያ የልማት ዕድገት ስለሆነ የምሥራች ነው። ሆኖም ከሌሎች ክልሎች የበለጠ መባሉ ያኔ ትናንትና “ትግራይ ልትሰምጥ ነው” እንደተባለው ከሆነ ችግር አለው። ከሌሎች ክልሎች እየተዘረፈና በአድሎዐዊነት ከሆነ በማንኛውም ጊዜ ጥያቄ የሚያስነሳና ተቃውሞን የሚያስክትል ነው “ብድር እያለብህ ውፍረት መጨመር አበዳሪውን መናቅ ነው” ይባል የለ?

“ሕወሓት ኢሕአዲግን ሲመሠርት በትረ ሥልጣኑን ለመቆጣጠር ነው፤ እኛም ብልጽግናን የመሠረትነው ለራሳችን ስንል ነው። ከአሁን በኋላ ብልፅግናን መምራት ያለበት ኦሮሞ ነው፤ አለበለዚያም ኦሮሞ የፈቀደለት ብቻ ነው”።

ኢትዮጵያን እነማን እያሸከረከሯት እንደሆነ መላው ሕዝብ የሚያውቀውና የሚናገረው ነው። እናንተም አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንደተባለው ነው እንጅ በደንብ ሰምታችኋል። ያልገባችሁ ነገር ቢኖር ካሁን በኋላ ኢትዮጵያን በአንድ ነገድ የበላይነት አስተዳድራለሁ ብሎ አይታሰብም፤ Ethnocracy  አብቅቶለታልና።

“ብዙሐንን አናሳ እያደርግን ነው”፣ 

ኦሮሚያ ውስጥ የሌላ ነገድ ተወላጅ በማስፈጀት ከወያኔ ጋርም ተለጣፊ በነበራችሁበት ጊዜ ለአማራ እናቶች የወሊድ ማምከኛ በመስጠት ቁጥር እየቀነሳችሁ ነው።

“ድንበር የማካለሉ አዋጅ ወጥቷል፤ ለስሙ ነው እንጅ ይፀድቃል”,

 “እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል” አለች አሉ አይጥ። በኦሮሙማ ርዕዮተዓለማችሁ ታላቋን ኦሮሚያን የመመሠረት ዕቅድ መሆኑ ነው? አንድ የረሳችሁት ትልቅ ነገር ቢኖር ከብዙ ክልሎች ጋር ይኼ ለከት የለሽ ተስፋፊነታችሁ/ወራሪነታችሁ በጠላትንት እንድትታዩ ማድረጉን ነው። በድንበር ማካለል ስም ግዛት ማስፋፋት ካሰባችሁ ያ የዱሮው (የ16ኛውና የ17ኛው ክፍለ ዘመን) የተስፋፊነት/የወራሪነት ዘመን ስላበቃለት እናንተንም ሆነ ሌላውን ለሌላ ዕልቂት እየጋበዛችሁ ነው።

“ፖለቲካ ቁማር ነው ቁማሩን በልተነዋል” 

ይችን የኮረጁዋት ከጌታዎ ጀዋር መሐመድ  መሆኑ ነው። ሆኖም ግን ሚስጠሩ ሳይገባዎት በግልብነት ኮረጁትና ተረጎሙት እንጅ አባባሉ፦ “politics is the arts of the truth” ነው ጠለቅ ብሎ ለተረዳው።

“አባይን ተሻግረን ባሕር ዳር ድረስ ሄደን የቻልነውን አሳምነን ያልቻልነውን አደናግረን ተመልሰናል፣”

ያሳመናችሁትና ያዞራችሁበት ተለጣፊውን እንጅ የአማራውን ሕዝብ ስላልሆነ ብዙ ባትዝናኑ ጥሩ ነው። ጉዳዩ ከተነሳ ዘንድ ኦሮማራ ብላችሁ ሄዳችሁ ለአማራው አመራር መተላለቅ ቅድመ ሁኔታ አዘጋጅተን መጥተናል ለማለት ይሆን?

ከአቶ ሽመልስ ስትራተጂ መረዳት የሚቻለው ኢሕአዲግ የሕወሓት ፈረስ እንደነበረ ሁሉ ብልፅግና የኦህዴድ ፈረስ መሆኑን ነው። የአቶ ሽመልስ የኦሮሚያ ክልል በእነጀዋርና በቀለ ገርባ የተቀመረለትን ስትራቴጂ በመተግበር ላይ እንደሆነ በግልፅ ተቀምጧል። ይህንን ጠቅላይ ሚኒስትሩና ሌሎች ይጋሩታል? የሚፈተሽ ይሆናል።

“ንኢ ንኢ ጉባኤ ቃና ድመት፣

     እስመ ተከውነኪ ልበ ተማሪ ወተት”

      (ጉባኤ ቃና ድመት ሆይ ነይ ነይ 

የተማሪ ልብ ወተት ሆኖልሻልና።)

      መምህሩ ለመቀኘት በተቸገረው ተማሪያቸው ላይ የቋጠሩት ቅኔ ነው።

የኦሮሚያ ብልፅግና አባይን ተሻግሮ ባሕር ዳር ድረስ ሄዶ ሞሳ ለተጫወተባቸው ምስኪን የብአዴን አመራሮች ቢሆን በሚል የቀረበ ነው።

አማራው ለኢትዮጵያ ሉዐላዊነትና ለሕዝቧ አብሮነት ሲባል እስከመቼ እየተዋረደና እይተጨፈጨፈ እንደሚኖር ግራ የሚያጋባ ነው። የሌላው ነገድ፣ ጉራጌው፣ ጌደዎው ወ.ዘ.ተ ተጠቂ ከመሆን ባያመልጥም፣ በተለይ አማራው ላይ ነፍጠኛ እየተባለ የሚደረገው የዘር ማጥፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ አሰቃቂነቱ እየጨመረ እንጅ እየቀነሰ አልሔደም።

በመንግሥት በኩል መፈናቀልና ጭፍጨፋ ባጋጠመ ጊዜ ሁሉ አለባብሶ ማለፍ እንጅ በተጨባጭ የሕዝቡን ደህንነት የማስጠበቅ ሀላፊነት ሲወሰድ አይታይም። በሙስናና በዘመድ አዝማድ ወገንተኝነት ተግቢውን ፍርድ ሳያገኙ የሚለቀቁ ዘጠኝ ሺህ  በቁጥጥር ሥር አውለናል ማለቱ ቁጥር ከማወጅ የሚያልፍ አይደለም። በቅርቡ የተደረጉ ጭፍጨፋዎች መጣራትም ሆነ ፍርድ ሊሰጥባቸው የሚገባው በልዩ ሁኔታ ለዚህ ተብሎ በተሰየመ ገለልተኛ አጣሪ ቡድንና ልዩ ፍ/ቤቶች ሊሆን ይገባል። በሰው ሕይወት ማጥፋት ላይ የተሰማሩ ታስረው መቀለብ ሳይሆን ባጠፉት ልክ ለሌላው ጀሌ አስተማሪ በሆነ መልኩ ፍርዳቸውን ማግኘት አለባቸው።

 “Nobody can give you freedom, nobody can give you equality or justice or anything, if you are a man you take it.” 

Malcom X

ተጠቂው ሕብረተሰብ የሚናገርለትና የሚቆምለት አጥቷል። ቤተ ክህነትም በቀድሞ የወያኔ አደረጃጀት በትግራይ ተወላጆች የተተበተበችና ምንም ለወጥ ያልተደረገባት ስለሆነች ከምዕመናኑ ነዋይ እንጅ ለምዕመናኑ ጥላ ሆና ድምፅ ስታሰማ አትታይም።

“The darkest places in hell are reserved for those who maintain their neutrality in times of moral crisis.”

 Dante Alighieri

የአማራው ብልፅግና ፓርቲ ለውጥ የሚያመጣ ሳይሆን እንደዱሮው ለሌላ አለቃ አሽከር ከመሆን ባሻገር እወክለዋለሁ የሚለው ሕዝብ ለምን ተነካ ብሎ ድምፁን ሲያሰማ አይስተዋልም። አዴፓ የአማራውን ሕዝብ ያድናል ብሎ ማሰብ ሰይጣን መስቀል ይዞ ያሳልማል እንደማለት ነው። ስለሆነም ሕዝቡ ምን ያህል አደጋ እንደተጋረጠበት እንደገና እራሱን ፈትሾ በመረዳት በመንደር መለያየቱን አሽቀንጥሮ ጥሎ በአንድነት በመቆም ራሱን አድኖ ሀገሩን ለመታደግ ቆርጦ መነሳት ይኖርበታል።

ሽመል ያለህ ብረት ግዛ፣

ብረት ያለህ ጥይት ግዛ፣

በጀሃዲስቶች ካራ ተቆራርጠህ ሳታልቅ እንደዋዛ።

 

ጽሑፌ ለትችት ክፍት ነው።

shegeyen@gmail.com

Filed in: Amharic