>

የህወሃት ጉልበቷ ገንዘቧ ብቻ አይደለም ሞታም የማይሞተው የአንበሳ ልቧ እንጅ... (መስከረም አበራ)

የህወሃት ጉልበቷ ገንዘቧ ብቻ አይደለም ሞታም የማይሞተው የአንበሳ ልቧ እንጅ…

መስከረም አበራ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስት ለሚያደርጋቸው እርምጃዎች ስሜት አልባ መሆን ጀምሬያለሁ። ለምን ቢባል መንግስት የሚመራን ወደ ዲሞክራሲ አልመስል እያለኝ ስለመጣ ነው። አሁን የተያዘው መንገድ ወደ ዲሞክራሲ መምራት ቀርቶ ሃገር የሚያሰነብትም አይመስለኝም በበኩሌ።
 በዘመናዊው ዓለም ደግሞ ሃገር በእኩልነት ላይ ብቻ ትቆማለች። እኛ የቆምነው ግን የአድሎ መደብር በሆነው የዘውግ ዓለም ነው። ስለዚህ መንግስት የሚያደርገውነገር ሁሉ ብቸኛ ዘውጋዊ አምባገነንነቱን ለማፅናት ይመስለኝ ይዟልና አሮጌው የዘውጌ አምባገነን በሌላው ግልገል አምባገነን ዘውጌ መሸነፉ ለዲሞክራሲ ምፅዓት የሚያመጣው ነገር አይታየኝም። እናም   አዲሱ በብዙ ገቨር የተለበጠ ዘውጌ የድሮውን ግልፅ ዘውጌ ለማዳከም ገንዘብ መቀየሩ እኔ ለምመኘው ዲሞክራሲ ምን ያግዘዋል ብዬ ልደሰት?
 ይልቅስ ገንዘብ መቀየሩ በዶላር በዩውሮ በፈረንጅ ሃገር ባንክ የተቀመጠውን የድሮውን ዘውጌ ሃብት ፍንክች ያደርገዋል ወይ፣የህወሃት ሃብትስ በጥሬ ገንዘብ የሚቀመጥ ነው በባህር ማዶ እንደ ስቶክ ማርኬት አክሲዎን፣የሞል፣ የቤት ግንባታዎች ባለ ግዝፈት የሚቀመጥ ነው የሚለውን ቻሌንጅ ለአዲሱ ዘውጌ ባቀርብ እወዳለሁ
 ቆቋ ህወሃት ገንዘቧን ሁሉ  በእንስራ አስራ አክሱም ሆቴል ጓሮ ከቀበረች ነው የገንዘብ ለውጡ የሚጎዳት። በነገራችን ላይ የህወሃት ጉልበቷ ገንዘቧ ብቻ አይደለም ሞታም የማይሞተው የአንበሳ ልቧ እንጅ
 የሆነው ሆኖ ኦህዴድ/ብልፅግና ተሳክቶለት በኢኮኖሚ warfare ህወሃትን በማሽመድመዱ እደሰት ዘንድ ኦህዴድ/ብልፅግና ከህወሃት ተሽሎ ሊታየኝ ይገባ ነበር። ተሽሎ ስላልታየኝ የብር ለውጡ ከዛሬ ሁለት አመቱ የወንበር ለውጡ የተለየ አይደለም……
Filed in: Amharic