>

የጅቦችና የአህዮች ድርድር...!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

የጅቦችና የአህዮች ድርድር…!!!

ቬሮኒካ መላኩ

በአለፉት 25 አመታት የህውሃት የአገዛዝ ዘመን ውስጥ ድርጅቱ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ የሚመዛት ካርድ አለች ። ይች ካርድ ” ድርድር “ትባላለች ።
የወያኔን የድርድር የተለመደች ድራማ ስሰማ ሁሌ ትዝ የሚለኝ ቁም ነገር አዘል “የጅቦችና የአህዮች ” የድርድር ተረት ነበር፡፡
በአንድ አገር የሚኖሩ ጅቦችና አህዮች ሰላም ለመመስረት ተስማምተው በየጊዜው በችግርም በደስታም ወቅት ሊጠያየቁ ተግባብተው በጉርብትና መንፈስ አብረው ሊኖሩ ተነጋገሩ። ብዙም ውሎ ሳያድር ከጅቦቹ ዋሻ አንድ አሮጌ ጅብ የመሞቱን መርዶ አህዮቹ ይሰሙና ለቅሶ ለመድረስ ይሄዳሉ።
አረፍ እንዲሉ ከተጋበዙት እነዚህ ቂል እንስሳት ዘንድ አንደኛው ጅብ ይጠጋና በመሰረቱ የእዝን መስጠት እንደሚገባ ዳሩ ግን ይህ ደሞ ስለሚበዛ አህዮች የላይኛውን ከንፈራቸውን ብቻ እዲሰጡ ይጠይቃቸዋል።
መቸስ ምን ይደረግ አስተዛዛኞቹ አህዮች ጨዋታውን አልተረዱምና የላይኛው ለንጨጫቸውን ተገሽልጠው ተቀመጡ ።ሌላኛው ጅብ ደግሞ መጣና ያላችሁት ሀዘን ቤት ውስጥ ነው ። ኀዘን ቤት ውስጥ ደግሞ መገልፈጥ ትክክል አይሆንምና ዘመድ ሲሞት ስላፌዛችሁብን ትበላላችሁ ተባለና ሁሉም አህዮች የጅቦች ሲሳይ ሆኑ ይባላል።
በኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔና በተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚደረግ ድርድር የጅብና የአህያ ፣የተኩላና የፍየል ድርድር ነበር። ከዚያ አያልፍም ። ጅብና ተኩላ ያሸንፋሉ ፣ አህያና ፍየል ይሸነፋሉ ።
በቅርቡ የኢትዮጵያ ታሪክ የሃይለስላሴ እና ደርግ መንግስት ብንመለከት ተለጣፊ አልነበራቸውም። ወያኔ ራሱን የቻለ ህይወት የሌላቸው ተለጣፊ ድርጅቶች ነበሩት አሁንም አሉት። እነዚህ ድርጅቶች የሚስቡት ኦክስጅንና የሚያስወጡት ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ህውሃት የሚባል ነው፡፡
አሁንም ኦነግ መራሹ የኦህዴድ መንግስት እያደረገ ያለው የወያኔን የድርድር ካርድ መጠቀም ነው፡፡ አማራን ታሳርዳለህ ከዚያ ትደራደራለህ፡፡ ታሰድዳለህ ከዚያ የሰላም መድረክ ተከፈተ ትላለህ፡፡ ወዳጀ ድርድርም የሚያምርብህ መጀመሪያ የጠላትህን ለንጨጭ ስትገሸልጥለት ነው፡፡
Filed in: Amharic