>

ሰሚ አልባ ጩህት... !!! (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም)

ሰሚ አልባ ጩህት… !!!

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

አንድ ትውልድ ይወለዳል፤ በጊዜው እንደጊዜው ያድጋል፤ ያልፋል፤ በሌላ ትውልድ ይተካል፤ አዲሱም ትውልድ የተረከበውን ቅርስ ይዞ ይነሣና በራሱ ጥረት አዳዲስ ሥራዎችን ሠርቶ ይጨምርበትና ያድጋል፤ አዲስ ነገርን ትቶ ያልፋል፤ የቀደመው ትውልድ ተፈጥሮና ኑሮው ከሚያስገድደው በላይ ለሚቀጥለው ትውልድ መስዋእት መሆን አይችልም፤ አይጠበቅበትምም፤ በምጽዋትና በሞግዚት አስተዳደር የሚኖር ትውልድ ሊሚቀጥለው ትውልድ የሚያስተላልፈው ዕዳ ብቻ ነው፤ ዕዳን በውርስ ተሸክሞ የሚፈጠር ትውልድ ያለምርኩዝ መንቀሳቀስ አይችልም፤ ምርኩዝ ሊሆኑት የሚችሉት እነዚያው የዕዳው ባለቤቶች ናቸው፤ ስለዚህም ከዕዳና ከምጽዋት አዙሪት አይወጣም፤ ይህንን በትክክል መረዳት የፈለገ የኪዩባን የሸንኮራ አገዳ ታሪክና የአሜሪካንን ኩባንያዎች ታሪክ ያጥና፤ ለካስትሮና ጓደኞቹ መሸፈት ምክንያቱን ታገኛላችሁ፤ የኪዩባ መሬት የአሜሪካኖች የሸንኮራ አገዳ ማምረቻ ሆነ፤ ኪዩባውያን የሸንኮራ አገዳ ቆራጮች ሆኑ፤ የኪዩባ ከተሞች የኪዩባ ሴቶች የአሜሪካኖች መዝናኛዎች የእረፍት ቀን ማሳለፊያዎች ሆኑ፤ … ሌላም ሌላም በርካታ ግፎች… እኒያ የበዙ ግፎች ካስትሮና ጓደኞቹን አስነሱ….
…ወደ ጓዳችን ስናይ ሴቶቻችንን ለመደፈር ለግድያ ተላልፈው ተሰጥተዋል!
– ስንገደል የሚከላከልልን ሀይል የለም!
– ቤቶቻችን ሲፈርሱና የሰው ልጅ በየመንገዱ በፕላስቲክ እየተጠለለ ሲኖር አቤት የሚባልበት የለም!
– ልጃገረዶች ታፍነው ተወስደው ወላጆች ሲጨነቁ አለሁላችሁ የሚል የለም!
– መሬቱንም ቤቱንም በገበሬ ስም ካድሬው ሲቀራመተው አቤት የሚባልበት የለም
– ጥቂት ወሮ-በሎች መቀሌ መሽገው የትግራይን ሕዘብ መያዣ አድርገው ሲያሰቃዩ አለሁላችሁ የሚላቸው የለም!
Filed in: Amharic