ሟቹና ረዳት አልባው ወገኔ ስማኝ:- በጉምዝ ወገንህ ላይ እጅህን እንዳታነሳ…!!!
ዘመድኩን በቀለ
ዐማራ ሆይ ጠላትህ ከጉያህ ስር ነው። ጠላትህ እጅና እግርህን አሳስሮ በማኅበር የሚያስደፍርህ የአንተው ጉድ ነው!
* ጠላትህ በስምህ ውክልናውን ይዞ ሚኒልክ ቤተ መንግሥት የመሸገው ሆዳም የአእምሮ ዘገምተኛው ዐማራ ነው። አዎ ጠላትህ እሱ ነው። ነግሬሃለሁ እንዲህች ብለህ በጉምዝ ላይ እጅህን እንዳታነሣ።
* እናም ወዳጄ የኦነግ-ብልጽግናንና የህወሓትን ምክር ሰምተህ በጉምዞች ላይ እጅህን እንዳታነሣ። ከቀስት አልፎ በመትረየስ የሚረሽንህ ጉምዝ እንደሌለም እወቅ…
•••
የሀገሪቱን የመከላከያ ሠራዊት ጭምር በገሀድ የሚረፈርፍ፣ ያውም ከግብጽ ጦር ይመጣብናል ብሎ አፈቅቤው ልበ ጩቤው የሚደሰኩርበት የህዳሴው ግድብ ባለበት ስፍራ ላይ ይሄን የመሰለ የዘር ማጽዳት ተግባር በቀን በብርሃን በድፍረት የሚፈጽም ተራ ሽፍታ የለም። ሽፍታ ቤት፣ ህንጻ የሚደረምስ መሣሪያም የለውም። ይሄ ከማእከላዊው መንግሥት የተላከ፣ የሚደገፍም ልዩ ኃይል የሚፈጽመው ነው። ይሄ አሁን እንኳ የት እንዳለ ከማይታወቀው ከለማ መገርሳ ግምጃ ቤት በወጣ መሣሪያ የተደራጀ፣ የሽመልስ አብዲሳን የዐማራ ማጽዳት፣ የዐብይ አህመድን አባገዳነት ባነገበ ቅልብ የሰለጠነ ጦር የሚፈጽመው ነው። ጎጃምን የኦሮሚያ አካል ለማድረግ፣ የህዳሴውን ግድብ ለመቆጣጠር፣ ከዚያም ታላቂቱን ኦሮሚያን ለመፍጠር ዐቢይ አጠገበ ካለው ከአማካሪው ከኦቦ ሌንጮ ለታ አዕምሮ የሚወጣ ክፉ ሃሳብ ነው። እናም ወዳጄ ዐማራ ይሄ ይሄ የትግሬ ተስፋፊዎች የጀመሩትን የኦሮሞ ተስፋፊዎች ዐማራን ከኦሮሚያም ከቤኒሻንጉልም፣ ከአዲስ አበባና ከመላ ሀገሪቱ አፈናቅሎ፣ አስጨንቆ ልክ እንደ ኩርዶች ሀገር አልባ ለማድረግ ከመፈለግ የመጣ ቀሽም የፖለቲካዊ ሴራ ነው። እናም ወዳጄ ገዳይህ ጉምዝ አይደለም። ይሄንን ጠንቅቀህ እወቅ። ተረዳም።
•••

•••
የዐማራ ክልል በኦሮሞ ወታደሮች ተተክቷል። ለተቃውሞ እንኳ ሰልፍ መውጣት አትችልም። ያለ ርህራሄ ይረሽኑሃል። ሐረር ላይ ዐማራው መስፍንን ገድለው አስከሬኑን በከተማዋ ሲጎትቱ ያስዋሉት እኮ ዐማራው ደንግጦ ሀረርጌን ለቅቆ እንዲወጣላቸው ነበር። በአሩሲ፣ በባሌና በጅማም የዐቢይ፣ ሽመልስና ለማ ጦር ያን ሁሉ ውድመት የፈፀመው አንተ ደንግጠህ ስፍራህን ርስትህንም እንድትለቅ በማሰብ ጭምር ነው። እናም ርስትህንም አትልቀቅ፣ ብልህ ነህና፣ የሚያመዛዝን ልቦናም አለህና፣ ጠላትክንም አሳምረህ ታውቀዋለህና በምስኪኖቹ ጉምዞች ላይ እንዲህች ብለህ የበቀል እርምጃን ለመውሰድ እጅህን እንዳታነሣ። ነገር ግን እደግመዋለሁ ጠላትህን በደንብ ለይተህ እወቀው።
•••
ዛሬ መታረድክን፣ በጅምላ መረሸንክን፣ የዘር ማጥፋት እንደተፈጸመብህ እያዩ፣ እንዳላዩ፣ እየሰሙ፣ እንዳልሰሙ የሆኑትን ሁሉ መዝግበህ ያዛቸው። አሁን አንተ በቁጣ ተነሣስተህ ለበቀል ጉምዞች ላይ ብትነሣ ወዲያውኑ ነው እነ ዐቢይ አህመድ፣ እነ ኢዜማ፣ እነ ኢቲቪና ፋና፣ ዋልታም ጭምር ዐማራ ጉምዞችን ፈጀ ብለው በእንግሊዝኛ ጭምር ዜና የሚሠሩብህ። አሁን መታረድክን ፤ የእናት ማህጸን እየተዘነጠለ ጽንስህ ሳይቀር ሜዳ ላይ ተጥሎ ሰልፊ ይነሱበታል። በአንጻሩ ብልጽግና በችግኝ ተከላ፣ በብር ቅየራ ለያረሳሱህ የሚፈልጉት አንተ እርምጃ መውሰድ ብትጀምር ወዲያው ነው ፕሮፓጋንዳ የሚሠሩብህ።
መሞትክን፣ መገደልክን፣ መታረድክን አወድሰው ራስህን መከላከልህን እንደ ወንጀል ቆጥረው ባለጊዜዎቹ ቁማር ነው የሚጫወቱብህ። እናም ወዳጄ የኦነግ-ብልጽግናንና የህወሓትን ምክር ሰምተህ በጉምዞች ላይ እጅህን እንዳታነሣ። ከቀስት አልፎ በመትረየስ የሚረሽንህ ጉምዝ እንደሌለም እወቅ።
•••
ትናንት መቀሌ ላይ የህወሓትን የጨበራ ምርጫ ማሸነፍ በማስመልከት ለድጋፍ የወጡ ሰልፈኞች ለዐማራ ማዘናቸው የሚያሳይ ባነር ይዘው አደባባይ ሲወጡ ባየሁ ጊዜም ሳቄን ነው መቆጣጠር የተሳነኝ። አይ ህወሓት እግዚአብሔር ይይልሽ። የቤኒሻንጉል ክልል የሚል አርቴፍሻል ክልል ሠርታ ጎጃምን በገዛ መሬቱ ላይ ማሳረዷን ረስታ አሁን ደግሞ ለዐማራ ሞት አዛኝ መስላ በአደባባይ ትታያለች። የእጅሽን አትጪ። በአፋር የጀመረሽ አድዋ ድረስ ይዝለቅልሽ። የፈጠርሽው እባብ እንደሆነ ይኸው ዘንዶ ሆኖ ሁልሽንም በየተራ መዋጡ እንደሁ አይቀርም። ይኸው ትናንት ሩቅ የሚመስልሽ የነበረው የዐማራ ሞት በአብአላ ላይ በአፋር ፖሊስ ተመስሎ 3 የትግሬ ኦርቶዶክሳውያንን ረሽኗል የሚል ዜና እየሰማን ነው። እናም ወዳጄ ትግሬ ሆይ የዐማራ ሞት ብቻ መስሎህ ስትደንስ ሞቱ ለአንተም እንደማይቀርልህ እወቅልኝማ። አዳሜ እና ሄዋኔ ሆይ አዛኜን አይቀርልሽም።
•••
ኢልማን አባ ገዳዎቹ እንደሆነ ልማት ላይ ናቸው። የወንዝ ዳር ልማት ላይ ናቸው። ሆዳም ዐማራውን ይዘው ልማት ላይ ናቸው። ዳንኤል ክብረትን እያሳዩ ኦርቶዶክሱን፣ ገዱ አንዳርጋቸውንና ደመቀ መኮንን ሀሰንን እያሳዩ ወለዬውን፣ እነ ላቀ አያሌውንና ተመስገን ጥሩነህን እያሳዩ ጎጃሜውን፣ እነ አገኘሁ ተሻገርን እያሳዩ ጎንደሬውን፣ እነ ዳግማዊትን እያሳዩ አዲስአበቤውን ሸዋውን በየተራ ያርዱታል። ያጸዱታል። ዐማራና ኦርቶዶክስን ከኢትዮጵያ እያጸዱ እነሱ ልማት ላይ ናቸው። ጊዜ የሰጠው ቅል ደግሞ አደገኛ ነው። ድንጋይ ይሰብራል። ኦኦ አደገኛ ነው። እናም ዐማራ ሆይ እንደ አባቶችህ ጥበበኛ ሁን። እንደ እርግብ የዋሕ፣ እንደ እባብ ብልህ ሁን። አትቸኩል፣ አትጣደፍ፣ ሀዘንህን በውስጥህ አምቀህ ቅድሚያ የቤት ሥራህን ጨርስ። ችግርህን ነቅሰህ አውጥተህ ገምግም። ዛፎቹ እያለቁ፣ እየተመነጠሩ ያሉት፣ ዛፎቹ ዐማሮች እየተቆረጡ ያሉት እውነት እውነት እልሃለሁ በምሳሩ በዐቢይ አማካኝነት ነው? በምሳሯ በህወሓት አማካኝነት ነው፣ በኦነግና በኦነግ ሸኔ አማካኝነት ነውን? የዛፎቹ ዐማሮች አስቆራጭ ደግሞ ከዛፎቹ ዐማሮች ወገን የሆነው ጠማማው እንጨት፣ በድኑ ብአዴን ነው። መጥረቢያ እኮ ያለጠማማ እጀታ ብቻውን ዋጋ የለውም። አቅምም የለውም። እና መጀመሪያ በቀደመው ባህልህ መሰረት ቅድሚያ የቤትህን ችግር ፍታ። መጀመሪያ ቤትህን አስተካክል። ከዚያ ቀሪው ዕዳው ገብስ ነው።
•••

•••
ህንጻ የሚንድ መሣሪያ ጉምዝ አይታጠቅም። በመደደዳ ዐማራንና አገውን ብቻ መርጦ አይረሽንም። ጉምዝ ይሄን አያደርግም። ተመስገን ጥሩነህ ሸልሞ የላከውን ጠርጥር። ለሻሸመኔ፣ አሩሲ፣ ሐረርጌና ባሌ ጅማው የአማራ ጭፍጨፋ ሽመልስ አብዲሳን፣ ለቤኒሻንጉል ጉምዙ ደግሞ የጉምዙን መሪ ካባ ሸልሞ በደንብ ጨፍጭፉት ብሎ የላከውን ጎጃሜውን የዐቢይ አሽከር ተመስገን ጥሩነህን ጠርጥር። ይሄን ለማወቅ ከፈለግክ ደግሞ ይሄ ሁሉ ዐማራ ታርዶ የዐቢይ አህመድን የሸገር ፓርክ ወሬን ልብ ብለህ ተመልከተው። የአዳነች አቤቤን የሊጥ ማቡካት ዜና ተመልከተው። በቤኒሻንጉል ጉምዝ የዐማራ ጭፍጨፋ ዜና አንተን ጠምደውህ እነሱ ሌላ ሥራ ላይ ናቸው። ለብልጽግና ሞትህ ጉዳዩ አይደለም። ዐማራን ማጽዳት ለህወሓትም ለዐቢይም የጋራ ግባቸው ነው። ኦርቶዶክስን ማፅዳትም እንዲሁ የጋራ ግባቸው ነው።
•••
መከላከያ ውስጥ ከጠላት ወገን ሳይሆን ከወገን ጦር በተተኮሰ ጥይት ተመትተው የሚወድቁ ይበዛሉ አሉ። ሟች የኢትዮጵያ ወታደሮች በአብዛኛው ከጀርባቸው ነው የሚመቱት አሉ። የተመቱት በሙሉ ደግሞ ያው የፈረደበት ዐማራና ኦርቶዶክስ ባለማዕተብ የሆኑ ብሔር ብሔረሰቦች መሆናቸውም ይነገራል። ከመከላከያ ሠራዊትም ውስጥ በእንዲህ መልኩ እየተቀነሱም ነው ተብሏል።
•••
ብአዴን ሬሳ ይቆጥራል። ዐማራ ይሞታል። ኦህዴድኦነግ ዐማራን ይገድላል፣ ይረሽናል፣ ያስረሽናል። እንደ ተአምር የሚቆጠረው ደግሞ ዐማራን ጣልያንም፣ ደርግም፣ ህወሓትም፣ ኦነግኦህዴድም፣ ሸአቢያም ረሽነው፣ መርፌ ወግተው፣ አሳድደው፣ አፈናቅለው፣ በእሳት አቃጥለውት፣ ንብረቱን ወርሰው፣ ምንም ሊጨርሱት አለመቻላቸው ነው። ወዳጄ ከአምላኩ ዘንድ ቃልኪዳን ያለውን ህዝብ እንዴት ልታጠፋው ትችላህ? ትለፋለህ፣ ትደክማለህ እንጂ ዐማራን ማጥፋት አትችልም። መንግሥቱ ኃይለማርያም ብሎ ብሎ ያቃተውን፣ መለስ ዜናዊ ብሎ ብሎ ያቃተውን፣ የዐቢይ አህመድ መድከም ነው የሚገርመኝ።
•••
እናም ዐማራ ሆይ በቅማንትም፣ በጉምዝም፣ በሌላውም ወገንህ ላይ እጅህን አታንሣ። ይልቅ በእነዚህ ወገኖችህና ከወንድሞችህ ጀርባ ተጭነው የሚወጉህን አጋንንቶች በተሎ እወቅባቸው። ሴራቸውንም አፍርስባቸው። አሁን ደግሞ መቼ ይሆን የሚረሽኑህ? በየትኛው ክልል የሚገኙ ዐማሮችን ይሆን የሚያጸዱት? አይ አብይ አሕመድ የሥራህን ይስጥህ። የሥራህን በዓይንህ እያየህ በእጅህ አግኘው።
•••
ማስታወሻ | ~ ዛሬም እንደተለመደው እንደወትሮው በተለመደው ሰዓት በ ፡https://www.youtube.com/c/ ZemedkunBekele የዩቲዩብ ቻናሌ ላይ በሰዓቱ እንገናኝ። ነጭነጯን እናወራለን። እንመክራለን። አዳዲስ ዜናዎቹም ይኖሩኛል። የብሩ ነገር መቋጫ አላገኘም፣ ሊቀጳጳሱ መስመር ስተዋል፣ ጴጥሮሳውያን ይተነፍሳል። ጠብቁኝ።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
መስከረም 7/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።