>

የእስክንድር ምስል ያለበት ቲሸርት የለበሱ ሰዎች በፖሊስ ታስረዋል...!!! (ታምሩ ብርሀኑ)

የእስክንድር ምስል ያለበት ቲሸርት የለበሱ ሰዎች በፖሊስ ታስረዋል…!!!

ታምሩ ብርሀኑ

* የባለቤቱን የችሎት ውሎ ለመከታተል የሔደውን የአስቴር ስዩም ባልም ለእስር ተዳርጓል!?! 
ዛሬ የእነእስክንድርን ችሎት ለመከታተል ከመጡት ደጋፊዎች መካከል የነእስክንድር ፎቶ ያለበትን ቲሸርት ለብሳችኋል በሚል ወደ እስር ቤት ተወሰደዋል። የትኛው እስር ቤት እንዳሉ ማወቅ አልቻልንም። በፖሊስ ከተወሰዱት መሀል የነጻነት ታጋዮዋ የአስቴር ስዩም ባለቤት አቶ በለጠ እና የድርጅታችን ሪፖርተር አቶ ወግደረስ ጤናው ይገኙበታል። ተከታትለን ሁኔታውን እናሳውቃለን።
ባልደራስ
የአስቴር ስዩብ ባለቤት አቶ በለጠ በበዓሉ ዋዜማ ለክብር ሬዲዮ ቃለ መጠይቅ ሰጥቶ ስለ ባለቤቱ የቀድሞ እና የአሁን የፖለቲካ እስረኝነት አብራርቶ ነበር። በአሁኑ ወቅት እናት እና አባት የስድስት ዓመት ልጃቸውን ትተው እስር ቤት ናቸው ነው።በዚህ ቃለ መጠይቅ ስድስተኛ ዓመቱን የዕንቁጣጣች ዕለት ስለሚያከብረው ልጃቸው ተናግሮ ነበር።
በሌላ ዜና

አቶ ልደቱ አያሌው በ100 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ወስኗል!!!

ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ መገደሉን ተከትሎ ሁከት በማስነሳት እና በሌሎች ጉዳዮች ተጠርጥረው በአስር ላይ የነበሩት አቶ ልደቱ ዛሬ በቢሾፍቱ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
የአቶ ልደቱ አያሌው ጠበቃ አቶ አዲሱ ጌታነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ፍርድ ቤቱ በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
በዓይኔአበባ ሻንበል
ምንጭ:-ሸገር ኤፍ ኤም
Filed in: Amharic