የኅልውና አደጋ የተጋረጠበትን የአማራን ጉዳይ ከኦነጋውያን ጋር በማቡካት በንጹሀን ደም መሸቀጥ ነው!
አቻምየለህ ታምሩ
አማራ ለተጋረጠበት የኅልውና አደጋ አለማቀፋዊ የእርቅና እውነት አፈላላጊ ኮሚሽን እንዲቋቋም በማድረግ እንጂ ከኦነጋውያን ጋር በማቡካት ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አይቻልም!
ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ በአማራ ላይ የዘር ማጥፋትን በፕሮግራማቸው ላይ ጽፈው ፖለቲካቸው ያደረጉ፤ «ፖለቲካ ማለት አማራ መግደል ነው» እያሉ የነገዳቸውን አባላት ያሰለጠኑ፤ በተግባርም ባለፉት አርባ ስድስት ዓመታት የኢትዮጵያን ምድር የአማራ እናቶች፣ የአማራ ሕጻናት፣ የአማራ አርሶ አደሮችና የአማራ ሽማግሌ መታረጃ ቄራ ያደረጉ ነፍሰ በላ የጦር ወንጀለኛና አሸባሪ ድርጅቶች ናቸው።
ከእነዚህ የአማራ ቀንደኛ ባለደሞች፣ የጦር ወንጀለኞችና የአማራን ዘር ማጥፋት ፖለቲካቸው ካደረጉ አሸባሪ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስብ ድርጅት ቢኖር በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት የፈጸሙትን የጦር ወንጀለኞቹን እነ ኦነግና ወያኔን ከደሙ ነጻ እያደረጋቸው መሆኑን ሊያውቅ ይገባል። ሲጀመር ኦሮምያ ክልል በሚባለው የኢትዮጵያ ክፍል ኦሮሞ ባልሆኑ ዜጎች ላይ እየተካሄደ ያለው ፍጅት በዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ድጋፍ፤ ጃዋር መሐመድ በሚያሰማራው የጥላቻ መንጋና በኦነግ ጥምር ግብረ ኃይል የሚፈጸም የዘር ማጥፋት እንጂ ግጭትም ሆነ ሁከት አይደለም።
ይህን በዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ሙሉ ድጋፍ፤ ጃዋር በሚያሰማራቸው መንጋዎች ፈጻሚነትና በኦነግ የርዕዮተ ዓለም ጡንታ እየተካሄደ ያለን የዘርና የሃይማኖት ፍጅት ሊያስቆምና ሊጠየቅበትም የሚችለው አካል ቢኖር የወንጀሉ ፈጻሚዎች እነ ዐቢይ አሕመድ፣ ጃዋር መሐመድና የመንፈስ አባታቸው የሆነው ኦነጋዊው ኃይል ብቻ ነው።
በአገዛዙ ልሳን በዜና ሲነገር እንደሰማነው በዐቢይ አሕመድ አነሳሽነት በአማራና በኦሮሞ ፓርቲዎች መካከል ለወራት ሲካሄድ ነበር የተባለ ውይይትና ምክክር በዛሬው እለት የጋራ የፖለቲካ አቋምና ስምምነት ሰነድ በመፈራረም ተጠናቋል። የጋራ የፖለቲካ አቋም ተያዘባቸው የተባሉት፤
1. በሁለቱ ክልሎች [አማራና ኦሮምያ የሚባሉትን ክልሎች መሆኑ ነው] የሚኖሩ “ሕዝቦችን” ደኅንነት ማስጠበቅና መብታቸውን ማስከበር፤
2. ባገራችን በሁሉም አካባቢዎች ሰላምና ጸጥታ፤ ሕግና ፍትሕ ማስፈን፤
3. ከየቦታው ያላግባብ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቅያቸውና ኑራቸው እንዲመለሱ ማድረግ፤
የሚሉት ናቸው።
ይታያችሁ! እነዚህ በአማራና በኦሮሞ ፓርቲዎች የጋራ ስምምነት ተደርሶባቸው የጋራ አቋም ተያዘባቸው የተባሉት ነጥቦች ሁሉ መንግሥት ነኝ የሚል አካል የሚሰራቸው፤ የመንግሥትነት ግዴታዎችቹና የእለት ተእለት ተግባሮች እንጂ ተቃዋሚ ፓርቲ ነኝ የሚል ድርጅት ስራዎች አይደሉም። ነው ወይንስ የስምምነቱ ፈራሚዎች ሳንሰማ የጥምር ሽግግር መንግሥት ከዐቢይ አሕመድ ፓርቲ ጋር መሰረቱ? ይህ ካልሆነ በስተቀር የመንግሥት ብቻ ተግባራት የሆኑትን የሕዝብ ደኅንነትን ማስጠበቅ፣ ሰላምና ጸጥታ፤ ሕግና ፍትሕ ማስፈን፤ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቅያቸው መመለስና ማቋቋም የመለሱ ተግባሮችን ታንክና ባንክ የሌለው፤ የመንግሥት አካል ያልሆነ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ በጋራ ለመፈጸም እንዴት ብሎ ይስማማል? ሌላው ቢቀን የሕዝብን ደኅንነት ለማስጠበቅና መብት ለማስከበር፤ ሰላምና ጸጥታ፤ ሕግና ፍትሕ ለማስፈን የተስማማ ተቃዋሚ ፓርቲ ነገ ሕዝብ ሲገደልና ሲፈናቀል እኔም አብሬ ተጣያቂ እደረጋለሁ ብሎ እንዴት ስለራሱ ተጠያቂነት አያስብም? አንድ ማኅበር ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራንና ውልክና የሚመለከት ስምምነት የሚደረገው ከመንግሥት ጋር እንጂ ከፖለቲካ ፓርቲ ጋር አለመሆኑን ሳያውቅ እንዴት የፖለቲካ ፓርቲ ይሆናል? ሕገ መንግሥት ማሻሻል የሚለው ነገርስ ቢሆን? ሕገ መንግሥት ተብዮውኮ አይደለም በሁለቱ ክልል ተብዮ ፓርቲዎች ስምምነት ቀርቶ የዘጠኙ ክልል ተብዮ ፓርቲዎች ተስማምተውበት የአንድ ክልል ተብዮ ፓርቲ እንኳን ከተቃወመው መሻሻል እንዳይችል ተደርጎ የተሰራ ዶግማ ነው። አንድ ፓርቲ ይህንን ላያውቅ ይችል ይሆናል። የገረመንኝ የማያውቅ ፓርቲ የዞረበትን ነገር ካላወቀ ለማወቅ አለመጠየቁ ነው።
ከምንም በላይ የገረመኝ በአሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ሙሉ ድጋፍ፤ ጃዋር በሚያሰማራቸው መንጋዎች ፈጻሚነትና በኦነግ የርዕዮተ ዓለም ጡንታ በተካሄደው ፍጅቱ እጁ የሌለበት አካል እጁ ያለበት ይመስል ከነ ኦነግ ጋር «በጋራ በመስራት ግጭቱን ለማስቆም ተስማምተናል» ማለቱ ራሱን እየወነጀለ፤ በፍጅቱ እጁ እንዳለበት እያረጋገጠ፤ በቄሮ በግፍ የታረዱ ግፉአንንም በፍጅት ሳይሆን አብረው በፈጠሩት ግጭት እንደሞቱ እየመሰከረና ሁለት ጊዜ እየገደላቸው መሆኑን አለመገንዘቡ ነው።
ፍጅቱን ግጭት፤ እጁ የሌለበትን ፍጅት እጁ ያለበት ግጭት አድርጎ በማቅረብ የማይቆጣጠረውን ኦነጋዊ የጥላቻ መንጋ ፍጅት ለማስቆም «በጋራ በመስራት ግጭቱን ለማስቆም ተስማምቻለሁ» የሚል የፖለቲካ ድርጅት ቢኖር ነገር አለሙ የተምታታበት ብቻ ነው። ባጭሩ የአማራ ድርጅት ሆኖ ከፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ ጋር በጋራ ለመስራት የሚስማማ ቢኖር ፖለቲካ ሳይሆን ወንጀል እየሰራ መሆኑን ማወቅ አለበት።
ለአማራ ሕዝብ ቆመናል የሚል ድርጅት በተለይ ቁማር በላን ከተባለ በኋላ “ኦሮአማራ” የሚለው ነገር ቁማር መሆኑ ሊገባቸው በተገባ ነበር። “ኦሮማራ” የሚባለው ቀልድ የነዐቢይ አሕመድ መጫዎቻ ሆኗል። ከኦነጋውያን ጋር “ውል፣ ስምምነት፣ አብሮ መስራት” እያሉ እነሱን ከፈጸሙት አለማቀፍ ወንጀል ነጻ ማድረግ፤ ከዐቢይ አሕመድ ጋር “ኦሮማራ” እያሉ መጃጃል የነሱ መጫዎቻ መሆን ነው። ብልጡ ዐቢይ አሕመድ “ኦሮማራ” በማለት የሚመዘው ካርድ፤ “ውል፣ ስምምነት፣ አብሮ መስራት” እያለ የሚጫወተው ቁማር ኦሮሙማውን ያሰበውን ያህል እየሰለቀጠ አላስኬደው ሲል ዛሬ ለቁማር መጫዎቻነት ያጫቸውን የአማራ ፓርቲዎች ነገ ዘብጥያ አውርዶ የሽብር ከስ ይመሰርትባቸዋል። ይህንን የሚጠራጠር ካለ እስካዚያው ብርታቱን ይስጠው እንጅ ወደሜዳው እየዘለቅን ስለሆነ ስንደርስበት ያየዋል።
የአማራም ሆነ የኢትዮጵያ ችግር ዘላቂ መፍትሔ የሚገኘው የኦሮሞ የገዢ መደብ ኢትዮጵያን ከወረረ በኋላ፣ የተፈጸመውን ግፍ ፣ የዘር ማጥፋት፣ ርስት መንቀልና እና ጥፋት የሚመረምር፤ ውሳኔውና ግኝቱ አስገዳጅ የሆነ አለማቀፋዊ የእርቅና እውነት አፈላላጊ ኮሚሽን በማቋቋም ባለፉት አራት መቶ አመታት ወንጀል የፈጸመው ቢኖር እንዲክስ፣ የሌላውን ቅድመ አያት አጽመ ርስት የያዘውን ማንኛውንም መሬት ቢኖር ወደ ትክክለኛው ባለቤቶች እንዲመለስ ለሚበይነው አለማቀፋዊው የኮሚሽኑ ውሳኔ መገዛት የግድ የሚል ስምምነት ውስጥ በመግባት እንጂ የኦነጋውያን ቁማር መጫዎቻ በመሆን አይደለም።
አብንም ለአማራ የቆመ ከሆነ ከኦነጋውያን ጋር ማቡካቱን ትቶ ከነሱ ጋር የሚደረግ ድርድርም ሆነ ስምምነት የፖለቲካ መጃጃል እንጂ የትም የማያደርስ መሆኑን በመገንዘብ ፖለቲካውን ግኝቱ አስገዳጅ የሆነ አለማቀፋዊ የእርቅና እውነት አፈላላጊ ኮሚሽን እንዲቋቋም ማድረግ አለበት። ይህም የሚሆነው ሁሉን አካታች በሆነ ድርድር እንጂ ከተካኑ ቁማርተኞች ጋር በሚደረግ መጃጃል አለመሆኑን ማወቅ አለበት።
ከዚህ በፊት “በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የቀረበ ምክረ ሐሳብ” በሚል ርዕስ [Link: https://www.facebook.com/ achamyeleh.tamiru.3/posts/ 3365947300093862 ] ያቀረብሁትን ምክረ ሀሳብ ለተጨማሪ ግንዛቤ ማንበብ ይቻላል።