>

መከራ መስቀሉ ቀጥሏል!!! (ብርሀኑ ተክለያሬድ)

መከራ መስቀሉ ቀጥሏል!!!

ብርሀኑ ተክለያሬድ

 

ብልጽግና መስቀሉን ዳግም በቆሻሻ ክምር ለመዋጥ አማኙንም ለማጥፋት ታጥቆ ተነስቷል!
 
ክልከላ// እስር:-
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ከአዳማ ደብረ ዘይት እና ሞጆ ከንቲባዎች ጋር ሲወያዩ የዋሉ ቢሆንም በመጨረሻም መስቀልን በአደባባይ አታከብሩም ቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ አክብሩ በሚል ቀጭን መንግስታዊ ትእዛዝ ነገሩ ተደምድሟል። ሁሉም ቦታ አባቶች ሳይስማሙ የወጡ ሲሆን የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሚከተለኝ ይከተለኝ እንጂ ብቻየንም ቢሆን ወጥቼ አከብራለሁ ብለዋል።
በሌላ በኩል አሸዋ ሜዳ የታጠቅ ገብርኤል አገልጋዮች የሆኑት፦ካሳሁን ደሳለኝና ታደለ ፀጋዬ ገፈርሳ ኖኖ 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ አሸዋ ሜዳ ታስረዋል። ሁለቱም አገልጋዮች የደብሩን ቦታ ባለጊዜዎች ሲወስዱት ለሕግ ያቀረቡ  ጠንካራ ምእመናን ናቸው።
ብልጽግና መስቀሉን ዳግም በቆሻሻ ክምር ለመዋጥ አማኙንም ለማጥፋት ታጥቆ ተነስቷል!
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ቀድሞም ጠላቶች በሆኑ መስቀሉን በቆሻሻ ክምር እንዲዋጥ በማድረግ ለረጅም ዘመናት እንዲቆይ አድርገዋል።
ዛሬም የእነዚህ ውላጆች ጊዜና ወቅትን ጠብቀው መስቀሉን በቆሽሽ አስተሳሰባቸው ዳግም ሊቀብሩት ሩጫቸውን ጀምረዋል።
ይህንንም ተግባር በሆሳዕና ከተማ ቀድሞ የመስቀል ደመራ ይከበርበት የነበረበውን ቦታ በመንጠቅና ተገቢ መልስ ባለመስጠት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ የሆኑትን ምእመናን እንዲሸምቀቁ በማድርግ በሃይማኖታቸው እንዳይጸኑ በምግባራቸው እንዳይቀኑ በማድረግ የተሽናፊነት ስነ ልቦና እንዲሰርጽባቸው በማድረግ የጥፋት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ ይገኛሉ።
ሆኖ በተለያዩ አካባቢ የሚገኙ አንዳንድ የመንግስት ሹማምንት ተብዬዎች ጊዜያዊ ስልጣናቸውን በምጠቀም የተላላኪ ስራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ። እነዚህ ጊዜያዊ ሹማምንት ቀድሞም ከታሪክ የመማር ልምድም ሆነ ፍላጎት ስለሌላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆንን በሙሉ በሆሳዕና ከተማ ሹማምንት የተነፈገውን የመስቀል ደመራ ማክበሪያ ስፍ በህብረት በመሆን ማስከበር ይገባል።
በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ በሊቀ ጳጳስ በምትተዳደር ሀገረ ስብከት የሊቀ ጳጳሱን ተገቢ የሆነ ጥያቄን ለመመለስ ፍቃደኛ ያልሆነ ሹማምንት የቅድስት ቤተ ክርስቲያኒቱን መልስ ለመመለስ ፍቃደኛ አለመሆኑን ማሳያ ነው።
ተገቢ የሆነን ጥያቄ ለመመለስ ፍቃደኛ የማይሆንን ምንኛውንም የመንግስት ሹማምንት ምእመናን ያላቸውን ድምጽ ለማይሰማቸው ሹማምንት እንዳይሰጡ፣ የቤተ ክርስቲያንን ድምጽ ማሰማት ለማይፈልጉ ሚዲያዎች በሯን መዝጋት፣ የራሷን ድምጽ በራሷ ልጆች እንዲሰማ ማድረግ ይገባል። ይህም የሚሆነው በኅብረት በመቆም ነው።
በሆሳዕና የመስቀል ደመራ በአል የማይከበር ከሆነ በመስቀል አደባባይ የመስቀል ደመራ አለተከበረም ማለት ነው። በሆሳዕና የሚከበረው የደመራ በአል በመስቀል አደባባይ ከሚከበረው በአል በሁሉም ነገር እኩል ነው።
ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል አይደለም- ፍትሕ!!
Filed in: Amharic