>
5:28 pm - Friday October 10, 0977

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ20 በላይ ንፁኃን ተገድለዋል...!!! (ታዘብ አራጋው - አ.ብ.መ.ድ)

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ20 በላይ ንፁኃን ተገድለዋል…!!!

ታዘብ አራጋው – አ.ብ.መ.ድ

ትናንት 6 አማራዎች በባሶ ሊበን ዛሬ 14 አማራዎች በመተከል ታርደው አድረዋል!
 * ያልታወቁ ኃይሎች በሚል ሽፋን  አማራን እያጸዱ ያሉት የኦሮሙማ አቀንቃኝ የኦህዴድ ባለስልጣናት ናቸው
 
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትናንት ሌሊት በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የንፁኃን ሕይወት አልፏል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ደንገዝ ቀበሌ ትናንት መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም ሌሊት 10፡00 ገደማ ማንነታቸው ያልታወቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ የንፁኃን ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአብመድ ተናግረዋል፡፡
የደንገዝ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ ደምለው በንገዝ ለአብመድ በስልክ እንዳረጋገጡትም በአካባቢው ጥቃት ተፈጽሟል፤ ከ20 በላይ ንፁኃንም ተገድለዋል፡፡ ችግሩ እንደሚፈጠር ስጋት እንደነበራቸው ያመላከቱት የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ ጥቃቱ ሌሊት ላይ የተፈጠረ በመሆኑ ለመከላከል እና አጥፊዎቹን ለመከታተል እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡
የዳንጉር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ደሳለኝ እንድሪስ ከጥቃቱ በኋላ በአካባቢው የተለየ እንቅስቃሴ አለመኖሩን ገልፀው የፀጥታ አካላት ወደ አካባቢው ተንቀሳቅሰው ችግሩን እያጣሩ መሆኑን ለአብመድ ተናግረዋል፡፡ “ችግሩ የተፈጠረበት አካባቢ የደኅንነት ስጋት እንዳለበት ቀደሞ መረጃ ስለደረሰን ወደ አካባቢው ሰዎች እንዳይሄዱ ነግረናል፤ ነገር ግን ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች በምን መንገድ ተመልሰው እንደሄዱ ዕውቅና የለንም” ነው ያሉት፡፡
 ዝርዝር ጉዳዩን እያጣራን ነው፤ የጥቃቱን መጠን፣ የጥቃት አድራሾችን ማንነትና መሰል ጉዳዮችን መረጃዎችን አጣርቶ ለማድረስ አብመድ ጥረት እያደረግን ነው፡፡
ከዚህ ቀደም በወንበራ እና ቡለን አካባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮች ተሳትፈዋል በተባሉ አምስት ሽፍታዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡ በተጨማሪም የፀጥታ ኃይሉ 20 ተጠርጣሪዎችን ከሦስት የጦር መሳሪያ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡ በአጠቃላይ በዞኑ እስካሁን 391 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
Filed in: Amharic