>

መንግስት ተሸብሮ ጀግና ይመስላል! (እንግዳ ታደሰ)

መንግስት ተሸብሮ ጀግና ይመስላል!

እንግዳ ታደሰ

የፍቼውና የጎሃ ጽዮኑ የአውቶቡስ እገታ የሚቀናበረው በመንግስት ነው። ይህ ምንም የማያጠራጥር ድርጊት ነው። አላማው! በዚህች አገር ብልጽግና ከሌለ ! ቄሮ ይበላችኋል፣ ሰልፋችሁን ከኛ ጋር አስተካክሉ ጨዋታ ነው። ቄሮም ሆነ ፎሌ ! መንግስታዊ አደረጃጀት ያለው አካል ነው። ሽመልስን ለዚህ ዋቢ ማድረግ ይቻላል!
 
* አምባ ገነናዊ ስርአትን ነቅለን የዘረኛ አገዛዝ ስርአትን  ተክለናል ስልህ – አማራ ሱሉልታን ለማለፍ አልተፈቀደለትም ! ምን ማሟላት እንዳለበትም አልተነገረውም ! መኪኖች  ተመልሰው ደጀን ለመቆም ተገደዋል ።
 
 የሶስተኛው ዓለም መንግሥት ባላንጣዎቼ’ ናቸው ያላቸውን የህልም ቅዠቶቹን ሲቻለው በፍራክሽን መልክ አጣፍቶ፣ወይ አጋጭቶ፣አሊያም ራሱ ሽብር ሰርቶ ሃገረ መንግስቱን ያጸናል።
ትህነግ’ #ከመቐሌ፥ዳውድ ኢብሳ #ከጉለሌ፣እንደ ድሮ ልጅነታችን የሰኔ 30 ዛቻ ! ወዮልህ ከመስከረም 25-30 ሲሉት መንግስታችን ተረብሾ አንዴ በብርሃኑ ጁላ!አንዴ በፌዴራል ፖሊስ ዱላ’ እያስፈራራ ነው። እንደ እስራኤል ኮማንዶዎችም፣አዳራሽ ገንጥለው ሲያከሽፉ ወታደሮቹን ዛሬ በቲቪ ሲያሳየን ነው የዋለው።
ይህ መንግስት እንዴት ፖለቲካውን ሰሞኑን እንደሚያሸብረው የኔን ምልከታ ከተፈቀደልኝ ላቅርብ። *በኦርቶዶክስ አባቶች መሃል የመጣበትን ምርር ያለ ተቃውሞ ለመከፋፈል፣አቡነ መርቆርዮስን ከቤተ መንግስት በማስመጣት፣ስጦታ ሰጡኝ በሚል የመከፋፈል ዘዴ፣ ከአቡነ ማትያስ ጋር አጋጭቶ ትርፍ ለማግኘት አሲሯል። ህወሃትን ለማናደድ እና አቡነ ማትያስን የጭዳ ዶሮ አድርጎ አማራውን ኦርቶዶክስ ከጎኑ ለማሰለፍ  ሞክሯል።
*አስር ወራት ያስተኛውን “#ኦሮ_አማራ” የተባለ እንቅስቃሴ!ትላንት አስነስቶ የፖለቲካ ትርፍ ሊያገኝበት እየጣረ ነው። ላስረዳ! ይህችን መስከረም 30′ የምትባል ቀንን በመፍራት – ድንገት እነኝህም እንዳይዘምቱብኝ በሚል ብልጠት ኃይል ቅነሳን ለማስፈን፣አብን፥ኦነግን በሁለት በመክፈል፥ኦፌኮን እንዲሁ በሁለት ከፍሎ የፊርማ ጨዋታ አድርጓል።
“አብንን” በሚመለከት ከወፈ-ሰማዩ ደጋፊዎቹ ለመነጠል የሚያደርገው ጥረት እንደሆነ ግልጽ ነው። አብን ግን ለዚያ ሽወዳው የተመቻቸ አልሆነለትም። እንደ አንድ በሳል የፖለቲካ ተዋናይ ሥራውን ብብልሃት እንደሚወጣ ርግጠኛ ነኝ።
የፍቼውና የጎሃ ጽዮኑ የአውቶቡስ እገታ የሚቀናበረው በመንግስት ነው። ይህ ምንም የማያጠራጥር ድርጊት ነው። አላማው! በዚህች አገር ብልጽግና ከሌለ ! ቄሮ ይበላችኋል፣ ሰልፋችሁን ከኛ ጋር አስተካክሉ ጨዋታ ነው። ቄሮም ሆነ ፎሌ ! መንግስታዊ አደረጃጀት ያለው አካል ነው። ሽመልስን ለዚህ ዋቢ ማድረግ ይቻላል። ከቤተ መንግስቱ አፍንጫ ስር ያለች #ጎሀጥዮን እና #ፍቼ ለዶክተር አብይ አፍንጫ ሩቅ አይደሉም። ሁሉም መንግስታዊ ጨዋታ ነው።
Filed in: Amharic