>

"ጉዳዩ የበዓል ማክበሪያ ጋት ቦታ መጠየቅ አይደለም፤  እንደ ሰውና ዜጋ የአገር ባለቤት መሆንና አለመሆን ጉዳይ ነው!!!" (ብፁዕ አባታችን አቡነ ሕሪያቆስ)

 

“ጉዳዩ የበዓል ማክበሪያ ጋት ቦታ መጠየቅ አይደለም፤  እንደ ሰውና ዜጋ የአገር ባለቤት መሆንና አለመሆን ጉዳይ ነው!!!”

ብፁዕ አባታችን አቡነ ሕሪያቆስ
ፋንታሁን ዋቂ
የተወደዳችሁ የኦሳዕና ኦርቶዶክሳዊያን ሆይ
መገፋታችን ምንጩ ከቀበሌ፣ ከወረዳ ከዞንና ከክልል አይደለም። ወይንም የአንድ የአካባቢ ባለሥልጣን ችግር ፈጣሪነትና ክፋት አይደለም።
የኦርቶዶክሳዊያን ለጥቃት ዒላማ መደረግ የ60ዎቹ የኮሚኒስት ረዕዮት የወለዳቸው ከሰብአዊ ማንነታቸው ተለይተው ቁሰአካላዊነት ቁስ ያደረጋቸው ፖለቲከኞች የክርስትና ጠላትነት ትክል ነው።
ይህ ተክል በአርመን ኦርቶዶክስ እልቂት በሚታወቀው  የቱርክ ድጋፍ፣ የመርዝ ጢስ ነስንሶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሶችን ለማጥፋት ጣሊያንን የለቀቁብን  የአውሮፓ ዘረኛ ቅኝ ገዥዎች አማካሪነት እየተመከሩና የርእዮተ ዓለም ድጋፍ እያደጉ፣ በጀርመን ሚሽነሪዎች፣ በቫቲካን የፋሽት ባራኪዎች ወዘተ ጥምር የስሁት ትምህርት መስኖነት  ለምልሞ ፀረ ክርስትና ዘረኛ ፍሬው ጎምርቶ፣ የአገር ሕግና ሥርዓት ለመሆን በመብቃቱ ነው። ስለዚህ የጥቃቱ ምንጭ የአገር ፖለቲካ ዋና መመሪያ ሆኗል።
ጥቃቱ አገራዊ ሆኗል።
መፍትሔው የበዓል ማክበሪያ ጋት ቦታ መጠየቅ አይደለገም። ጉዳዩ እንደ ሰውና ዜጋ የአገር ባለቤት መሆንና አለመሆን ጉዳይ ነው።
የዚህ ሁለገብ ጥቃት መድኀኒቱ ከሥላሴ ልጅነት ያገኘ ክርስቲያን ሁሉ ከዘረኝነት ደዌ ተላቆ በአንድነት በመቆም የዘረኞችና የፀረ ኦርቶዶክስ እምነቶች ፖለቲካን መቃወም ነው።
እግዚአብሔር ስም የሚያምን ሁሉ ከዘረኝነትና ከውጭ ገብ የተውሶ እምነትና ፖለቲካ ራሱን ነፃ ያውጣ። አባቶችንም ይህን ደዌ ተሸክመው የሚያሰራጩትን አውግዘው ይለዩ።
የመስቀል በዓልንና ጥምቀትን በሚመለከት ከአደባባይ ታቅበን በስግደት÷ በፆም፣ በለዘን በቅፅረ ቤተክርስቲያን ማሳለፍ ይጠቅማል።
*     *     *
 
ዘንድሮ ከሆሳዕና ምእመናን ጋር ለማዘን የአደባባይ በዓላትን ሙሉ በሙሉ በቅፅረ ቤተክርስቲያን በመወሰን እድንተባበር ቅዱስ ሲኖዶስ ይዘዘን!!!
አገሩ የኛም መሆኑ፣ መንግሥትም ኢትዮጵያዊ መሆኑ እስኪረጋገጥ በዓላትን ሁሉ ወደ ምሕላ ሥርዓት በመቀየር በመላው ዓለም አብረን ብንቆምስ?
መፈናቀል፣ መገደል፣ አምልኮ ሥርዓታችንን ማስታጎል ሥራው የሆነ መንግሥት ውክልናው ለማን እንደሆነ ግልጽ እየሆነና ኦርቶዶክሳዊያንን ከጥልቅ እንቅልፍ አስነስቶ የአገራቸው ባለቤት እስኪሆኑ ድረስ አደንዳውን ወደ ተራ የቦታና የምልክት ጉዳይ ማድረግ እጅግ ጎጅ ነው።
የአድዋን እዳ በጣሊያን ተገብቶ እንዲያወራርድ፣ በአህመድ ግራኝ በኩል ባሪያ ሊያደርገን ሞክሮ በ15  ዓመት የከሸፈውን የቱርክ ጅሀድ ለመካካስ፣ በወንጌል የተሸነፈውን አምልኮ ባዕድ  የሠይጣን ጠበቃ ሆኖ ለመመለስ ከሆነ፤ ከ60ዎቹ አብዮተኞች የክስና ጥቃት የምንወጣው ስለ እያንዳንዷ  ሜዳና አደባባይ  መነጋገር  ብቻ አይደለም።
መዋቅራዊ መፍተሔ መፈለግ አለብን።
በዘር ተደራጅተው ቤተክርስቲያናችንን በመንደር ተካፍለው፣ ጣዖት አስመልከው፣ እንደ እንስሳ ሊገዙን ይሻሉ። ለፍተወታቸው ከእውነተኛው  ሕያው የወይን ግንድ ክርስቶስ  በቋንቋና በሐሰተኛ ትርክታቸው ቆራርጠው ሊያደርቁን እየተጉ ነውና ዘረኝነትን ኢምቢኝ ብለን በሕይወት እንኑር።
 ጥምቀትና መስቀልን በምሕላና በፆም እናሳልፍ። የአደባባይ በዓላት በመላው ኢትዮጵያ ሳንወጣ በየቤተመቅደሳችን እንጩኽ።
Filed in: Amharic