>

እየደረሰ ላለው ጫና እና መግፋት የኦርቶዶክሳውያን አፀፋ ፖለቲካዊ መሆን አለበት...!!! (የፍልስፍና መምህርና ጸሀፊ ብሩህ አለምነህ )

እየደረሰ ላለው ጫና እና መግፋት የኦርቶዶክሳውያን አፀፋ ፖለቲካዊ መሆን አለበት…!!!

 
የመቀሌ ዩንቨርስቲ የፍልስፍና መምህርና ጸሀፊ ብሩህ አለምነህ 

እኔ በግል አቋሜ ኢአማኒ ብሆንም ለኦርቶዶክስ ቤ/ክ ሃይማኖታዊ በዓላቷና  ቅርሶቿ ግን ቀናኢ ነኝ። የፖለቲካ ለውጡን ተከትሎ በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ላይ እየደረሰ ያለው መከራና ዓይን ያወጣ አድልኦ በጣም እያንገበገበኝ ነው።
ልክ አምና በ2012 እንዳደረጉት ዘንድሮም የኦርቶዶክስ ቤ/ክ የአደባባይ በዓላት ላይ እንቅፋትና ክልከላ እያደረጉ ነው። እኛ ስለ Secularism እና Pluralism መርህ እንዲከበር እየወተወትን፣ ለካስ ለውጡን ተከትሎ ከላይ እስከታች ሥልጣን ላይ የተሰገሰገው ፀረ Secularism እና ፀረ ኦርቶዶክስ የሆነ የፕሮቴስታንት ስብስብ ነው።
ሰሞኑን በኦሮሚያና በደቡብ ክልል ከተሞች የመስቀል በዓል በአደባባይ እንዳይከበር እየተደረገ ያለውን የባለ ሥልጣናት ክልከላና ቢሮክራሲ ስመለከት ከአንድ አመት በፊት ሚኪ አምሓራ «በጠ/ሚ አብይ ካቢኔ ውስጥ ስንት ኦርቶዶክስና ፕሮቴስታንት እንዳሉ ብታውቁ፣ ሆን ተብሎ ኦርቶዶክሳውያንን ከመንግስት ከፍተኛ ኃላፊነት ለማግለል የተሰራ ሥራ መኖሩን ትደርሱበታላችሁ» ያለው ፅሁፍ ትዝ አለኝ።
“”””
የጠ/ሚ አብይ መንግስታዊ መዋቅር የ Secularism መርህ ማስጠበቅ ስላልቻለና መርሁንም በተደጋጋሚም እየጣሰና የኦርቶዶክስ ቤ/ክንን ድንበር እያለፈ እየተነኮሳት ስለሆነ የኦርቶዶክሳውያንም አፀፋ ፖለቲካዊ መሆን አለበት። በመሆኑም፣ መጪውን ምርጫ በተመለከተ ኦርቶዶክሳውያን አንድ የጋራ አቋም ላይ መድረስ አለባቸው። ይሄውም ተቀናጅተው ጠ/ሚ አብይ ለሚመራው የብልፅግና ፓርቲ ድምፃቸውን መንፈግ አለባቸው። ኦርቶዶክሳውያን ያላቸውን ሃይማኖታዊ መዋቅር ለዚህ የህልውና ጉዳይ መጠቀም አለባቸው። ሆኖም ግን፣ ይሄንን የማያደርጉ ከሆነና ብልፅግና ምርጫውን የሚያሸንፍ ከሆነ ቤተ ክርስትያኗ ራሷን በራሷ ለማጥፋት እንደወሰነች ይቆጠራል።
Filed in: Amharic