>

መጨረሻችሁን እስክናውቅ ዝም አንልም!!! (ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ)

መጨረሻችሁን እስክናውቅ ዝም አንልም!!!

ጋዜጠኛ መአዛ መሀመድ

በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ያሰናዳነውን ውይይት በፖሊስ እንዲከለከል አድርጓል።  በድጋሜ ላለመከልከሉ ዋስትና ባይኖርም የተማሪዎችን መጨረሻ ሳናውቅ ዝም ማለት አይታሰብም…
ከደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ ደብዛቸው የጠፋው 17 ተማሪዎች የመጨረሻ ሁኔታ ሳይታወቅ 300 ቀናት አለፉ። ዛሬ ላይ የእነዚህ  የተማሪዎች ጉዳይ የቤተሰቦቻቸው ብቻ ሆኗል። መንግስት እረስቷቸዋል። ጉዳዩን እልባት የመስጠት ፍላጎትም አይታይበትም። የተማሪዎች ጉዳይ እንዳይነሳ ለሚዲያ ትዕዛዝ እንደተላለፈም እየተነገረ ነው። በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ያሰናዳነውን ውይይት በፖሊስ እንዲከለከል አድርጓል። በእርግጥ የመንግስት ችላ ማለት የሚገርም አይደለም። ለስልጣኑ እንጅ ለዜጎች ደህንነት ግድ የሚለው ማንግስት አልታደልንም።
ድጋሜ ላለመከልከሉ ዋስትና ባይኖርም የተማሪዎችን መጨረሻ ሳናውቅ ዝም ማለት የለብንም በማለት እስከዛሬዋ እለት ደብዛቸው የጠፉትን ተማሪዎችን ለማሰብና ለማስታወስ ብሎም የሚመለከታቸውን አካላት ለማሳሰብ ማክሰኞ መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም  3:00 ላይ በማግኖሊያ ሆቴል የፓናል ውይይት ተዘጋጅቷል። በኮሮና ምክንያት ብዙ ሰው ማካተት ባለመቻላችን  ይቅርታ እየጠየቅ በእለቱ በያላችሁበት ሁናችሁ መንግስት የሚጠበቅበት እንዲወጣ በማህበራዊ ሚዲያ ጫና እንድናደርግ እጠይቃችኋለሁ። የሚዲያ ተቋማት በቦታው ተገኝታችሁ የሚዲያ ሽፋን የመስጠት ሙያዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
Filed in: Amharic