>

"ከመስከረም 25 በኋላ በፌዴራል መንግስት የሚወጡ ህጎች እና የሚሰጡ ውሳኔዎች በትግራይ ላይ ተቀባይነት የላቸውም!!!" (የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ አስመላሽ ወልደ ስላሴ)

“ከመስከረም 25 በኋላ በፌዴራል መንግስት የሚወጡ ህጎች እና የሚሰጡ ውሳኔዎች በትግራይ ላይ ተቀባይነት የላቸውም!!!”

የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ አስመላሽ ወልደ ስላሴ

 አቶ አስመላሽ   ዛሬ (ሰኞ) ምሽት ከትግራይ ቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ ከመስከረም 25 በኋላ በፌዴራል መንግስት የሚወጡ ህጎች እና የሚሰጡ ውሳኔዎች በትግራይ ላይ ተቀባይነት የላቸውም ሲሉ ተናገሩ።
አቶ አስመላሽ አክለውም ” …  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመሳሰሉት ከመስከረም 25 በኋላ ህጋዊነታቸው ስለሚያበቃ በእነዚህ ውክልና አይኖረንም።
በኢትዮጵያ ይካሄዳል የተባለው ምርጫ ህገወጥና ቅቡልነት የሌለው ነው። ብልፅግና በስልጣን ላይ እያለ የሚደረገው ምርጫ ህገወጥ ነው።
አሁን ሀገሪቱ በከፍተኛ ችግር ላይ ስለምትገኝ ሁሉም ፓርቲዎችን ያካተተ የብሄራዊ ሸንጎ መመስረት አለበት።
ብሄራዊ ሸንጎ ሳይመሰረት በሀገሪቱ ለሚደረገው ምርጫ ትግራይ በምርጫው እንደማትሳተፍም ማሳወቅ ያስፈልጋል። ብሄራዊ ሸንጎው ብሄራዊ መግባባትና እርቅን የሚያረጋግጥ መሆን አለበት።” በማለት ተናግረዋል።
የፌደራል መንግሥቱ ከቀናት በፊት ከመሥከረም 25 በኋላ መንግሥት የለም ብለው ችግር ለመፍጠር በሚፈልጉ ኃይሎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ለመወሰድ ተዘጋጅተናል የሚል መግለጫ በመከላከያ ሚኒስትር በኩል ማስተላለፉ የሚታወስ ነው።
Filed in: Amharic