>
5:28 pm - Wednesday October 9, 7568

እስክንድር ነጋ በፍርድ ቤት የተናገረው ! (ይድነቃቸው ከበደ)

እስክንድር ነጋ በፍርድ ቤት የተናገረው !

ይድነቃቸው ከበደ

* የእነ እስክንድር ነጋ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል!
” ጊዜው የምርጫ አመት ነው ።በምርጫ መሳተፍ እንፈልጋለን ፤ ጉዳያችን እረጅም ጊዜ
ሳይፈጅ በአጭሩ እንዲያልቅ ፍ/ቤቱን እጠይቃለሁ ።
” ከዚህ ልቦለድ ክስ ነፃ እንደምንወጣ ጥርጥር የለኝም። የሚጠብቀን ህዝብ አለ፤ በሕዝብ መመዘን እንፈልጋለን ።”
ያለ ሲሆን ፤ ከዚህ ቀደም ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ አልተፈጸመም ያለውን አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ፦
” ባለቤት እና ልጄ ውጪ ሃገር ስለሚገኙ በስልክ እዳናግራቸው ይህ ፍርድ ቤት ለማረሚያ ቤት ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ፤ ማረሚያ ቤቱ ይህን ትዕዛዝ አልፈጸመም ። አሁንም ቤተሰቤን እንዳገኘ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ይስጥልኝ ” በማለት አቤቱታ አቅርቧል ።
 
የእነ እስክንድር ነጋ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል!
ዛሬ መስከረም 19 /2013 እነ እስክንድር ስንታየሁ፣ አስቴር እና አስካል  ከፍተኛው  ፍርድ ቤት የጠዋት ችሎት ይቀርባሉ።
 ቀጠሮው ፣  ዐቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ያቀረበውን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ በመስጠቱ ነው እና በዋስትና ጥያቄያቸው ላይ ውሳኔ ለመስጠት ሲሆን ለእነ እስክንድር ዋስትናውን ውድቅ አድርጎታል።
Filed in: Amharic