>

በሬ ያላሰውን ሳይሆን ያኮላሸውን ይወዳል...!!!' (ታዬ ቦጋለ አረጋ)

በሬ ያላሰውን ሳይሆን ያኮላሸውን ይወዳል…!!!’

ታዬ ቦጋለ አረጋ

 

…ከሌለ ምን ያስበረግጋቸዋል?
እዚህ ሀገር ያለው የአእምሮ እድገት መቀንጨር ያሳስበኛል።
1. “አማራ የለም” እያለ፦ አማራ ነህ እያለ ወገኑን ያሳድዳል።
2. “አማራ የለም” እያለ፦ አማራውን ሊያጠፋ ማኒፌስቶ ይቀርፃል።
3. “አማራ የለም” እያለ፦ ወያኔና ኦነግ ጠፍጥፈው በአስተሳሰባቸው ልክ በቀረፁት ህገመንግሥት ሳይቀር “የአማራ ብሔራዊ ክልል” አቋቁመዋል።
4. ከኢትዮጵያ ህዝብ ቢያንስ ሲሦው “አማራ ነኝ” እያለ፦ አማራነቱን ይክዳሉ።
ታላቁን የሀገር አድባር፦  ‘የለህም’ ሊሉትም ይቅመደመዳሉ።
(የጅምላ ጭፍጨፋ ዝግጅት አንዱ ገፅ ይሄ ነው።)
5. አማራ ራሱን ሲገልፅ፦
“ጎጃሜ ጎንደሬ ሸዌ ወሎዬ ነኝ” ይልሀልና “የለም” ይሉሀል። ኦሮሞው “ቦረና ነኝ”፣  “ጉጂ ነኝ”፣ ሸዋ ነኝ፣ ወለጋ ነኝ”… አይል ይመስል።
6. “በአማርኛ ቋንቋ አትነጋገሩ” እያሉ፦ “አማራን ከመጥላት ጋር አይያያዝም” ይሉሀል።
እደግመዋለሁ፦ “አማራ ነህ” ካልከኝ፤ ባምር ብዋብ ምን ይከፋኛል? ምንስ ይጎድልብኛል?
ደግሞስ ማንነቴን የሚነሳኝና የሚሰጠኝ ማነው?
ምን አዲስ ቴክኖሎጂ ፈልስፈህ፤ የትኛውን የሞራል ደረጃ ይዘህ ነው፦ ዘር ልትቆጥር የምትንደፋደፈው?!
ለማንኛውም፦ በኢሬቻ ወቅት የማስታውሰው አንድ ልዩ ህያው መልእክት ሁሌም በአእምሮዬ ያቃጭላል፦ “የፈሰሰው የኦሮሞ ደም ደሜ ነው!”ይህ ቃል ብቻ አይደለም፤ አማራው ጀርባውን ሳይሆን ግንባሩን ለጥይት ሰጥቶልኝ በመስዋዕትነት አብሮነት የተረጋገጠ ነው።’በሬ ያላሰውን ሳይሆን ያኮላሸውን ይወዳል’ አሉ።  ታየ ደግሞ ውለታ ከደም አይተናነስብኝም። ከምንም በላይ ኢትዮጵያዊ ነኝና ሁልጊዜም ከተገፉ ጋር እቆማለሁ!
ከዛፍ አልተላጥሁም መነሻና መገኛ አለኝ። በአስተሳሰብ ደረጃ አማራም ኦሮሞም ሶማሊም አፋርም ጉራጌም ሲዳማም ወላይታም… ሁሉንም የሆንኩ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ሁሉም ቢነካ ያመኛል። እናት ሀገሬ ኢትዮጵያ ብትነካ፦ ከሁሉም ጋር እጅ ለእጅ ተያይዤ ሀገሬን ከጠላት ለመታደግ አብሬ እወድቃለሁ። ዛሬም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመላው ዓለም ያለ ጭምር ወገኔ ነው። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ነኝ።
Filed in: Amharic