እጅግ አሳዛኙ መንግሥት የለሽ የኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
እግዚአብሔር ያሳያቹህ!
ከሳምንት በፊት ሳውዲ ዓረቢያ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም አምባሳደር ለኢሳት በሰጠው ምላሽ “በኢሰብአዊ አያያዝ የተያዙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሳውዲ ዓረቢያ ውስጥ የሉም!” ብሎ ሸምጥጦ ክዶ ነበረ!!!
የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ ግን ትናንት ባደረገው ስሜት የሚነካ ውይይት በበርካታ ሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እጅግ አሰቃቂ በሆነ ኢሰብአዊ አያያዝ ያለ ምግብና ውኃ በሳውዲ ዓረቢያ የማቆያ ካምፖች እንደሚገኙ አጋልጦ የአውሮፓ ኅብረት በሳውዲ ዓረቢያ ላይ አግባብነት ያለው አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ በጉዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥቶ በጥልቀት ተወያየ!!!
እጅግ አያሳዝንም??? ወገኖቻችን የሚያስብላቸው፣ የሚቆምላቸው፣ የሚቆረቆርላቸው መንግሥት ከማጣታቸው በተጨማሪ የሀገርንና የዜጎችን መብት፣ ደኅንነትና ጥቅም እንዲያስጠብቅ እንዲከታተል እዚያ የተቀመጠው አምባሳደር ግን ወንጀሉን ለሚፈጽመው ለሳውዲ ዓረቢያ መንግሥት ጠበቃ ሆኖ የተፈጸመውንና እየተፈጸመ ያለውን ዓለማቀፋዊ ወንጀል ሸምጥጦ ክዶ ሳውዲ ዓረቢያን ተጠያቂ እንዳትሆን፣ እጅግ በሚዘገንን ኢሰብአዊ አያያዝ የተያዙ ወገኖቻችንም ማንም ሳይደርስላቸው እንዲያልቁ ሲሟሟት የአውሮፓ ኅብረት ግን ይሄንን ያህል ተጨንቆ ጉዳየ ብሎ ሲይዘውና ሲንገበገብበት ማየት እጅግ አይገርምም??? እጅግ አያሳዝንም???